” Authority forgets a dying ትግሬ ወያኔ “
ቬሮኒካ መላኩ
” Authority forgets a dying king ” ( ስልጣን እየሞተ ያለውን ንጉስ ከዳች ) ይላል ።
ልክ አሁን እኛ አገር ህውሃት እየሆነችው እንዳለው ማለት ነው። ” Authority forgets a dying TPLF ” ። ውይ ውይ እኔን ክንብል ያድርገኝ 🙂
…
የህውሃት ነገር ሃበሻ እንደሚለው ” ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል ” የሚሉት አይነት መሆኗ ግልፅ ሆኗል።
ይች ህውሃት የሚሏት ውሻ ከላይ ፀጉሯ ማጎፈር ብቻ ሳይሆን ሻይን ያደርጋል ውስጧን ስትከፍቷት ግን ምስጥ እንደ በላው ግንድ ተቦርቡራ አልቃለች ።
አብይ አህመድም የህውሃት ኢሚዩኒቲ መዳከሙን አውቆ በየቀኑ እንደ እባብ እየቀጠቀጠ ሞቷን እያፋጠነው ነው ።
…
አሁን ህውሃቶች ስልጣን ከእጃቸው መውደቅ ብቻ ሳይሆን ወድቆም መሰበሩንና እንክትክት ማለቱን አምነዋል። ብዙዎቹ የፖለቲካ ሞት እንደሞቱ ለራሳቸው አምነው ፍራሽ አንጥፈው ለቅሶ ተቀምጠዋል።
አሁን ሩጫው ስልጣኑን መልሶ መያዝ የሚል አይደለም። አሁን ሩጫው ነፍስን ለማዳን ማናቸውንም ሙከራ የሚደረግበት ጊዜ ነው።
…
አሁን ወያኔ የሆነው ሁሉ የሚጠየቅበት “የፍርድ ቀን” ( ዱምስዴይ) እየመጣ መሆኑ ግልፅ ነው።
የህውሃት መርከብ እየሰመጠች ከመሆኑ አንፃር የእኛ ስራ ከምትሰጥመው መርከብ ዘለው ሩጠው እንዳያመልጡን መጠበቅ ብቻ ነው ። ቱ ! ከአመለጡንማ ሞተናል ።
እስኪ አትሌት ገብረእግዚአብሄር ገብረማሪያም አዝሎቸው ይሮጥ እንደሆነ እናያለን ።
እንደ ፈረንሳይ አቢዮቱ ባስታይሌ እስር ቤት የፖለቲካ እስረኞቹን ሁሉ ነፃ ከተደረጉ በኋላ በምትካቸው እስር ቤቶቹ ባዶ እንዳይሆኑ እጃቸው በህዝብ ደም የቆሸሸ ፣ የባንክ አካውንታቸው በህዝብ ንብረት የሞላ በዝባዦች የሆኑትን ወያኔዎች እናጉርበታለን።