>
3:30 pm - Monday February 6, 2023

የዛሬዋ ቀን፤ ሰኔ አሰራ አራት ሁለት ሺህ ሶስት እንደ ኢትዮጵያችን ካላንደር፤ [ኣቤ ቶክቻው]

የዛሬዋ ቀን፤ ሰኔ አሰራ አራት ሁለት ሺህ ሶስት እንደ ኢትዮጵያችን ካላንደር፤
ደወለልኝ፤ ቴዲ ነው። ቴዲ ደሀንነቱ…
ሰማህ አይደል…
ምኑን…
ጓደኞችህ ተያዙ…
አዎ ሰምቻለሁ በጣም ያሳዝናል።
አትዘን ገና በዙ የሚቀሩ ሰላሉ አንድ ላይ ታዝናለህ… አሾፈ ማለት ነው… እኔ ግን የምር ጨንቆኛል፤ በጋዜጠኝነታቸው እና በጸሀፊነታቸው ብቻ የማውቃቸው ውብሸት ታዬ እና ርዮት አለሙ እንዲሁም ፖለቲከኛው ዘሪሁን ገበረእግዚአብሄር እና ሂሩት ክፍሌ ”መሰረተ ልማቶችን ሊያወድሙ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል” መባሉ ነገ እኔ ስያዝ ደግሞ ምን እባል ይሆን በሚል በጣም አስጭንቆኛል።
የዛን ጊዜ ደህነነቱ ቴዲ እኔ ዘንድ መምጣት ከጀመረ አንድ ወር አካባቢ ቢሆነው ነበር። እንደመጣ የተናገረኝ፤ ”ከመንግስት ጋር ተባብረህ መስራት አለብህ” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር ነበር። የመጀመሪያው ቀን ከመንግስት ጋር ተባብሮ መስራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም። ምናልባት አውራምባ ታይምስ ላይ መጻፍ ያቁምኩበት ጊዜ ስለነበረ አዲስ ዘመን ላይ አምድ ይሰጥህ ሊለኝ ነው ብዬ ለራሴ ኮምኬ ራሴን በሳቅ ገድዬው ነበር።
ኋላ ላይ ግን ከመንግስት ጋር ተባብሮ መሰራት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቴዲ በሂደት አብራራልኝ። እንደ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ እምነት እኛ (ማን ማን እንደሆንን ሲታሰሩ ነው የማውቀው እንጂ እነማን እንደሆንን አላውቅም) እና በነ ቴዲ ቢሮ እምነት እኛ መንግስትን በሃይል ለመናድ እና አንዳንድ ቦታዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ከሆነ ቦታ ትዕዛ እየተቀበልን ነው። ስለዚህ እኔ ይሄንን ሂደት ከስር ከስር ለቴዲ እየነገርኩ ”ጥቃቱ እንዳይፈጸም አናከሽፋለን” ማለት ነው…
ይሄ መረጃ የከሸፈ እና የተንሻፈፈ መረጃ መሆኑን ለቴዲ ደግሜ ደጋግሜ ነገርኩት። ሊሰማኝ አልቻለም።
እኔ ከማንም ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም። እንኳን ሌላው ቀርቶ አብረውኝ ከሚጽፉ ጋዜጠኞች ጋር የጠበቀ ጓደኝነት የለንም። አልኩት። መሰሚያ አለነበረውም…
ለምሳሌ፤ አለኝ አንድ ቀን…ጎተራ አካባቢ በርሱ ”ወያኔ” የተባለች መኪና ውስጥ ቁጭ ብለን ስናወራ… ”እዚህ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ላይ አፈንዳ ተብለህ ብትታዘዝ…” አለኝ።
የደነገጥኩት ድንጋጤ አይረሳኝም።
ኧረ ተሳስታችኋል እኔ እንዲህ ብለው የሚያዙኝ አይነት ሰው አይደለሁም። እንደዚህ አድርግ ብሎ የሚያዘኝም ማንም የለም። በዬ ለማስረዳት መከራዬን ሳይ ቴዲ ”ምሳሌውን እኮ ነው ያልኩህ…” አለኝ። ጨመረናም ”እንዲህ ብለው ካዘዙህ ወይም ሌላ ነገር ቀድመህ አሳውቀን ነው ያልኩህ” አለና ኮስተር አለ!
በስንተኛው ቀን እነ ርዮት አለሙ ወብሸት ታዬ ዘሪሁን ገበረ እግዚአበሄር እና ሂሩት ክፍሌ ታሰሩ። ደህነነቱ ቴዲ ገና ይቀራል ብሎኛል። ቀጣዩ ተረኛ ነህ በለኛ… ብዬ ብለው አንተማ አብረከን ለትሰራ ተሰማምተሃል… ማንም አይነካህም አለኝ።
እኔ ግን ያኔ ፈትህ ጋዜጣ ላይ በጻፍኩት ጨዋታ ‘ለመላው ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ ወዳጆቻችን በተለይም ለራሴ ”አይዞሽ ሙሽሪት አይበልሽ ከፋ ሁሉም ይገባል በየወረፋ” የሚል ዜማ መረጥኩ።
ጋዜጠኞቹ እና ፖለቲከኞቹ የታሰሩበት ምክንያት ሰሰማ ደግሞ በጣም ገራሚ ሆኖ አገኘሁት… ”መሰረተ ልማት አውታሮችን በተለይም የቴሌን ተቋም ሊያወድሙ ሲሉ በቁጥጥር ስር ዋሉ” ይላል። ይሄ ደህንነቱ ቴዲ ለኔ ምሳሌ ብሎ የነገረኝ ነው…
ከዛ በኋላ ስንቱ በምሳሌ ታሰረ… ማዕከላዊ፣ ቃሊቲ እና ቂሊጦ ይቁጥሩት
(ጠቅላላ ከደሀነነቱ ቴዲ ጋር የነበረንን ነገር በቅጡ የምናወጋበት ጊዜ ይኖረናል። ስለ ድሀነነቶቻችን አሰራር የሚነግረን ነገር አያጣውም…)

Filed in: Amharic