“ለውጡን እንቀበል!” – “ልንፋለመው ይገባል!” በሁለት ጽንፍ የቆመው የመቀሌው ዱለታ!!!
በፍቃዱ ሞረዳ

በተለምዶ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ማንኛዉንም በእጁ ያለዉን የመንግሥት ንብረት እንዲያሰረክብ ሲታዝ ሊከተል የሚችለዉ ነገር ማሰብ ይቻላል፡፡ በአነስተኛ ግምት ለሌላ ሹመት መታጨት ነዉ፡፡ አምባሳደር ዓይነት፡፡ በሰፊ ግምት ደግሞ ቂልንጦ መሄድና በሰፈሩት ቁና መሰፈር፡፡
ለማንኛዉም ሰዉዬዉ በእምብታቸዉ ከፀኑ የሚከተለዉ ነገር የኃይል እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹ እጅ ስጥ፤ አልሰጥም፡፡›› ከዚያም…ይለይለታል፡፡
የመቀሌዉ ዱለታም ‹‹ለዉጡን እንቀበል፣አብይን እንደግፍ››በሚለዉ ወጣት መሰል ቡድንና ‹‹ሰዉዬዉ (አብይ) በድርጅቱ ደንብና ሕግ ሳይሆን በሞቭ ፍላጎት እየተመራ ነዉና ልንፋለመዉ ይገባል›› የሚለዉ የእኔ ብጤ ገትጋታ በታደመበት መሀከል ዙሩ የከረረ ይመስላል፡፡ ‹‹ጊዜ ለመግዛትና እንደገና ለመጠናከር እንዲረዳን እነአብይን እንደግፍ›› ብሎ የሚለዉ ቡድን አምበል ጌታቸዉ ረዳ ሲሆን፣ በወዲያ ወገን ያሉት ደግሞ በአቶ ስብሃትና በስዩም የሚጦዙ ናቸዉ እያሉን ነዉ፡፡
ለስድብና ለዛቻ ይመቻቸዉ ዘንድ ‹‹ይጠራልን›› ያሉት የኢሕአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ስብሰባም በሊቀመንበሩ እምቢ ባይነት የተጨናገፈ ይመስላል፡፡ ጠሚዉ ‹‹ አይሆንም!›› ማለት መጀመራቸዉን አመልካች ሳይሆን አልቀረም፡፡
ትልቁ ዉሳኔ ግን የትግራይ ሕዝብ ነዉ፡፡ በአረጀዉ ሕወሓት ጭቆና ሥር መቆየት ፣አለያም ከአዲሱና ከጊዜዉ ሀቅ ጋር ቆሞ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር ለዉጡን መርዳት፡፡ ‹‹ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነዉ፡፡››
እኛ ግን ለዉጥ ደጋፊ ተጋሩዎች ‹‹አጁኻ!›› እንላለን፡፡