ኢትዮጵያውያን በስዑዲ እየተሰቃዩ ነው

saudi-ethio

 

በስዑዲ ዓረብያ “ዲዛን” በምትባል የደሴት ከተማ ፈጂም “ናዓም” በሚባል ወህኒቤት ኢትዮጵያውያን ታስረው እየተገረፉ፣ ተገርፈው እየቆሰሉ፣ ቆስለው እየታመሙ፣ ታመው ሳይታከሙ እየሞቱ፣ ሞተው በረኻ ላይ እየተጣሉ፣ ተጥለው የሚያስታውሳቸው አካል አጥተው፣ የሚጣበቅላቸው መንግስት ጠፍቶ በተስፋ መቁረጥ አፋፍ ላይ እንደተንጠለጠሉ ከእስረኞቹ ዛሬ ሌሊት የተገኘ መረጃ ይጠቁማል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊተባበራቸው አልቻለም። ሐበሻ በመሆናቸው ብቻ ነው የታሰሩት። ሓበሾች ደግሞ መንግስት የላቸውም። ከተመላሾች ጋር ፎቶ ሲነሱ የነበሩ ባለስልጣናት አሁን የት አሉ? ከሚኒስተሩ ጋር ፎቶ የተነሱ የስዑዲ ተመላሾችስ አሁን የት አሉ? ቃል የተገባላቸው ተተገበረ? በሀገራቸው ሰርተው እንዲኖሩ ሁኔታዎች ተመቻቹ? ወይስ ከፎቶ በኋላ የሚያስታውስ የለም?! ለማንኛውም ሚድያዎች እንዲተባበሯቸው ጥሪ አቅርበዋል። ከኣብርሃ ደስታ


Dr.Tewodros with migrants photo

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.