>

ሰበር መረጃ! ብአዴን ሁሉንም የቀድሞ አመራሮች ጠራርጎ ሊያስወጣ ነው!! (ሙሉቀን ተስፋው)

ሰበር መረጃ! ብአዴን ሁሉንም የቀድሞ አመራሮች ጠራርጎ ሊያስወጣ ነው!!
ሙሉቀን ተስፋው
ከብአዴን ያገኘኛቸው ምንጮች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የቀድሞዎቹ የኢሕዲን መሥራቾችና በአብዛኛው አመለካከታቸው ከአማራ ሕዝብ ፍላጎት ጋር የሚቃረኑ የቀድሞ ታጋዮች ሙሉ በሙሉ ተጠራርገው ይወጣሉ ተብሏል፡፡
በጎራ ተከፋፍለው በመነታረክ ላይ የሚገኙት የብአዴን አመራሮች እነ በረከት ስምዖንን፣ ከበደ ጫኔን፣ ኅላዊ ዮሴፍን፣ አዲሱ ለገሠን፣ …. ሙሉ በሙሉ እንደሚያስወግድ ታውቋል፡፡ በሥራ አስፈጻሚና በማዕከላዊ ኮሚቴነት የተካተቱት ሁሉም የቀድሞ አመራሮች በጡሬታ ወይም በግዴታ ይሰናበታሉ ተብሏል፡፡
Filed in: Amharic