>

አብዲ ኢሌ፣ ኦሮሚያና የአብይ አህመድ ሪፎርም፦ 

 አብዲ ኢሌ፣ ኦሮሚያና የአብይ አህመድ ሪፎርም፦ 
THE CASE OF PANDORA BOX DILEMMA
አብዲ ኢሌ የፈጸምኩት በደል በእንትና ነው ብሎ ይቅር በሉኝ ካለ ይኸው ምራቁ አልደረቀም። 
– የሶማሌ ልዩ ኃይል በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ ሃረርጌ 3 የኢሮሚያ ፖሊስ፣ 1 የመከላከያ ሠራዊት አባል እና 1 ሲቪል በድምሩ 5 ሰዎችን ገድሎ 7 ክፉኛ አቁስሏል።
* አሁን በደረሰኝ ባላረጋገጥኩት መረጃ ከ100 በላይ ሰው ተገድለዋ
——-
ባለፉት ጊዜያት ተመሳሳይ ጥፋቶችን ሲያጠፋ ቆይቷል። የአብዲ ኢሌ ፖለቲካው ውስብስብ ነው። አሁን ግን ይቀጥል ይሆን? ኦህዴድ ግን ምን ያህል እወክላለሁ ለሚለው ሕዝብ ሊቆም ይችላል? አብይ አህመድ የኦሮሚያን ጉዳይ ችላ ብለውታል የሚባለው እንዴት ነው?
————
እስኪ ለኔ እስከሚገባኝ ድረስ በትንሹ ላውራ….
፩. አብዲ ኢሌ ከባድ የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ነው (at the cost of the lives of citizens). ፖንዶራ ቦክስ እከፍታለሁ የበለጠ ምስጢር ከማወጣ እስክትምሩኝ እና እስክትምሩን ጭፍጨፋዬን እቀጥላለሁ እያለ ነው። ምናልባት የመጨረሻ ካርዱን እየመዘዘ ነው። በነገራችን ላይ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ያጣላው ይህ ልዩ ኃይል ይፍረስ በማለቱ ነበር። በኋላ ላይ ከሌሎች ጄኔራሎች (ጄኔራል ሳሞራ የኑስ እና ጄኔራል አብረሃ ወልዳይ (ኩዋርተር) ጋር ተባብሮ ይህን ልዩ ኃይል በእጁ አስቀረው። አታ ጌታቸውና ጄነራሉም (ሳሞራ) በዚህ ምክንያት መቃቃራቸው አልቀረም። አሁም ለዚያ ነው እንግዲህ ግማሽ እውነትን የሚይወራው። ምናልባት ምናልባት ደግሞ እነዚያ ጄነራሎችም የመጨረሻ ካርዳቸውን እየመዘዙ ነው። ማን ያውቃል? አትርፉን እንትረፍ ወይ እንፈጃችኋለን ነው ነገሩ። መቼም ከትላንት ወዲያ የተጣላው አቶ ጌታቸው አሰፋ እንደገና አሁንም እያስገደደው አይመስለኝም።
————
በነገራችን ላይ አቶ ጌታቸው አሰፋ ግን አሁን እንኳን ውንጀላውን ለማስተባበል በግልጽ ለሕዝብ እጄ ንጹህ ነው ለምን አይልም? አቶ ጌታቸው ግን የማይታየው መንፈስ ነው እንዴ አለ Leta Kenei Aga ሲጨንቀው።
———-
እኔ ግን መንፈስ መኾኑን የምጠረጥረው አቶ በረከት ስምዖንን ነው፣ በአንዴ ብዙ ቦታ ይገኛል እየተባለ ነው (ኹኔትውን Omnipresence ይሉታል የነገረ መለኮት ምሁራን)።እኔ ጠረጠርኩ እንጂ በረከት ስምዖን Omnipresent ነው አላልኩም እንዳትወግሩኝ ፈሪሳውውያን በሕግ አምላክ። ለነገሩ ፈሪሳዊ ሕግም አምላክም አያውቅም።
—————-
፪. ኦሕዴድ የራሷን ቤት ንጽህና አታምንም…የአጋሮችዋን ቤትም እንዲሁ። የአብዲ ኡሌ ፓንዶራ ቦክስ ቢከፈት ኦህዴድና ስልታዊ አጋሯ ይተርፋሉ ወይ? ያ ቦክስ የነሱን “መክሊት” እንዳልያዘ ማን ያውቃል?
………………
በሌላ በኩል ደግሞ እውነተኛዋውን ጠላት (ከዚህ ጭፍጨፋ በስተጀርባ ያለውን ሥውር እጅ) ከገጠምኩ ባንተርፍስ የሚል ትንሽነት አለባት..መጸሓፉ ከአምላክ ጋር የሚዋጋ ይደቃል ይላል።ኦህዴድስ ከአፈጣሪዋ ጋር ጥሏ እስከመቼ ነው? ይህንን ያለመድቀቅ ነገር ፍርሃት ኦህዴድና ወንድም ጋሼዋ አሁንም የረሱት አይመስልም። በግዛታችን ለሚፈጠሩ ችግሮች ተጠያቂዎቹ እኛው እንጂ ፈጣሪያችን አይደለም…የቀድሞ አባቶችን አይሆንም እያሉ ተስምተዋል ኦህዴድና ወንድንሟ።
……………
አሁን ደግሞ የኦህዴድ አበሳዋ ብዙ ነው…ቄሮ ወደ ድርጅት እየመጣ አይደለም፤ ዝቅተኛውና መካከለኛው ካድሬ አሀንም መሃይሙ፣ ሌባው እና ባለዝቅተኛ አፈጻጸሙ ሪፎርምን መረዳትም ሆነ መምራት/መመራት የማይችለው ለጥቅም አዳሪ ስብስብ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ሃገርን የመምራት፣ ተቋማዊ ለውጥን የማካሄድና ሃገርን ወደ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ብልጽግና የማሸጋገር ፕሮጀክት እየመራች ነው። በኢሕአዴግ መርኅ እየሄደችም አይደለም። በዚህ ደግሞ ፈጣሪዋን ክፉኛ አስክፍታለች። ይህ ፈጣሪዋ ፈርጠም ያለ ነው። ስለዚህ በዚህ አቅሟ ፈጣሪዋን መግጠም ትችል ይሆን? የፈጣሪዋ የወደቁ መላዕክትስ በእጅ አዙር ቢላኩባት አበሳዋ አይከፋም ወይ? እንዳልተላኩባትም ማረጋገጫ የለም። ነቢይ አይደለሁ…የወደቁ መላዕክቱም፣ በሥልጣን ያሉትም እንዳይነግሩኝ እኔ የኦህዴድን ፈጣሪ አላመልክ…ማን ይነግረኛል። እንጃ ብቻ።
በነገራችን ላይ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ተቀናቃኞችዋም እረፍት እየነሱኣት ነው…ምርጫውን አስባችሁታል?…ምፅ ምፅ።
፫. ሪፎርሙ ዋጋ ያስክፍላል…በተለይ የመከላከያና የደኅንነት። ብዙ ጊዜ ሁለቱን በአንዴ ሪፎርም ማድረግ አይመከርም። የመዋቅር ለውጥ ብቻ ስላልሆነ። በመከላከያ ሳይንስ reindoctrination ይሉት ጣጣ አላቸው። ይህ እንግዲህ የስልጣን ሽግሽጉን፣ የቅጥርና ሥልጠና፣ የማላመድ ሥራውን እና ላኮረፉት የሞራል ጥገና ማድረግን ሳይጨምር ነው። ሎጂስትክ፣ የጦር መሳሪያ አቅርቦት፣ የሥልጠና እና ሌሎች ረዲኤት አጋዝ/አጋር የመቀየር ነገርም ይኖራል። አብይን ዋጋ እያስከፈለና ጽጥታን እያናጋው ያለ ነገር ሁለቱን በአንዴ መጀመሩ (ለመጀመር ማሳወቁ) ነው። ይሄ ችግር ይከሰታል…ሕዝብ ዋጋ ይከፍላል፣ ይሄ ፖለቲካ ነው…የመረቀዘ ሥርዓትን ለመቀየር መዳዳትም ነው….ሁለት ከባባድ ሴክተሮችን ከሌላ ብዙ ሴክተር ጋር በአንድ ጊዜ ሪፎርም ለማድረግ መሞከር…ከባድ ዋጋ የሚያስክፍል ፕሮጀክት ነው…..አንዳንዴም ጀብድነት ነው። የአብይስ ከአቅም በላይ መሸከም ወይስ የጀግንነት ድፍረት? እኔ አላውቅም…ባውቅ ምን አስደበቀኝ…ፖለቲከኛ አይደለሁምና። ግን እንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፤ ሃገር በአንድ ጊዜ ከአንባገነንነት ወደ ዴሞክራሲ እንደማትሻገር። በመሃል ኣናርኪ ይኖራል…ግድ ነው። በተለይ ደግሞ Silent coup d’etat ስታካሄድ ይብሳል። ሳይደፈርስ አይጠራም ይል የለ ጠቢቡ ሃገረ ሰብ?
……
በነገራችን ላይ ሪፎርም ከማድረግ በፊት ተቋማቱን (መከላከያውን እና ደኅንነቱን) መሉ በሙሉ መቆጣጠርም ግድ ይላል?
እሱንስ ትጠራጠራለህ የሚለኝ ሰው አይጠፋም…መልሴ ግን እንኳን የሰውን ችሎታ የአምላክን መኖር ተጠራጥሬ አውቃለሁ።
………
ዋናው ጥንቃቄ አሁን የሚታየው ይህ ተፈጥሮኣዊ የሽግግር ጊዜ ክስተት ነው አልሞት ባይ ተጋዳዩ እውነትም አስፈሪ ነገር የያዘ ፓንዶራ ሳጥን ይዞ እያስፈራራ ነው የሚለውን መለየት ነው። ለፖለቲከኛው እና ለውስጥ አዋቂው ንገሩልኝማ።
፬. መጨረሻ ግን የኔ ጥያቄ። በደቡብ ክልል የጸጥታ ችግር ሲኖር በፍጥነት በቴሌቪዥን የማረጋጋት መልዕክትን ያስተላለፈው በነጋታው በአውሮፕላን ሀዋሳ፣ ከዚያ ወላይታ ቀጥሎ ደግሞ ወልቂጤ የሄደው ትክክለኛ የአመራር ሥራን የሠራው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምነው ዝምታ መረጡ ሰሞኑን? (በነገራችን ላይ በዚሁ 3 ቀናት ብቻ ከ50 በላይ ሰዎች ሞተዋል)። ዝምታው ትክክል አይመስለኝም። የጤና መኾኑም ያሳስበኛል።
የክልሉ አመራርስ ፌስቡክ ላይ “Shira Diinaa” የምትለዋን mantra rant ከማድረግ ውጪ ዝም ጭጭ ብለዋል። ኦህዴድ ለራስሽ ስትዪ …..(ሊቀመንበሯ አብይ አህመድን ጨምሮ)። ህዝብ እንደሆነ መንግሥት ግልበጣን ተምሯልና ምሕረትሽ ከአሪያም አይመጣም። ፈጣሪሽ እንደኾነ ያንቺ እንጅ የሕዝብ አይደለምና እኛ እንዳንቺ አንፈራውም።
ግድያ ተፈጽሞ ምክንያቱን እና የገዳይ ማንነትን “እየመረመርን ነው ውጤቱን ጠብቁ” ብላችሁ የነገራችሁን እና እኛ የመዘገብናቸው ክስተቶች እንዳሉ አትርሱ። ጨለንቆ፣ አምቦ፣ ነቀምቴ፣ ሞያሌ…የትየለሌ። የሚያሳዝነው የሞያሌው “በስህተት” የተፈጸመው ግድያ ትጥቅ ፈቱ የተባሉት “ተሳስቶ ገዳዮች” በሕግ እንዳልተጠየቁ እናውቃለን። የጨለንቆውም እንደዚሁ። መዝግበናል ለማለት ነው።
…………
ኦሮሚያን የሚያስተዳድረው ድርጅት አቅሙ ከተወዳጅነቱ በታች ነው። ሕዝቡ በእውነትኛው አምላክ ምሕረትና በጥቂት ሰዎች ጥረት እንደሚደገፍ እናውቃለን። ኢትዮጵያም እንዲሁ። ፓንዶራ ቦክሱን የያዙ ክፉዎችም ሆነ የድርጅቶቹ ፈጣሪ መቸም አፈር ልሶ ለመነሳት ጊዜው አልረፈደም። አቅሙም አለው።
…………
ኦህዴድ ሆይ ምን ይሻልሻል?
የልጅ ምክር ትሰሚ እንደሆነ ሁለት ምክር ለግሼልሽ ነበር።
…………
~እና ምን ለማለት ነው? ፖለቲካሽን ከደማችን ዋጋ ጋር ተመን ውስጥ አታገቢ! ፓንዶራ ቦክስ ፍራቻ ሃገር አያስፈጁምና!
Filed in: Amharic