>

"ለነጭ እባብ መርዝ መድሃኒት የለውም" ብላታ ሐጎስ - በዳንኤል በቀለ

“ለነጭ እባብ መርዝ መድሃኒት የለውም” ብላታ ሐጎስ
በዳንኤል በቀለ
እኒህ የኤርትራ ትልቅ ሰው ከአድዋ ድል ማግስት ያገራቸው የኤርትራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ሕዝብ በቅኝ ገዥዎች መርዝ ከተለያዩ በሁዋላ ተመልሰው መገናኘት እንዴት እንደሚከብዳቸው አስበው በቁጭት  ነበር ይህን የተናገሩት።
ከመቶ ምናምን አመት በሁዋላ መርዙን የሚያረክስ መሪ ኢትዮጵያ አፈራች።
ዓብይ አህመድ ለኢትዮጵያና ኤርትራ ችግር መፍትሄው ቅንነትና ፍቅር ነው ማለታቸው ትክክል ነው።
የመርዙ ማርከሻ ፍቅር ነው።
ኢትዮጵያኖች የኤርትራን ወደቦች ተመኝተው የኤርትራን ሕዝብ ካላፈቀሩና መብቱን ካላከበሩ የተጀመረው ሰላም አይዘልቅም።
ኤርትራውያኖች የኢትዮጵያን ሰፊ ገበያ፥ የስራ፥ የንግድና የቢዝነስ እድል ተመኝተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅም ካገለሉ ይሄ የተጀመረው ሰላም ባጭሩ ይቀጫል።
የሁለቱንም አገሮች ጥቅም የሚጠበቅበት ግንኙነት መመሥረት የመሪዎቹን እና ያማካራዎቻቸውን ጥበብና ማስተዋልን ይጠይቃል።
መሪዎቹ ይህን ካረጉ ሁለቱ አገሮች አንድ የሚሆኑበት ዘመን እሩቅ አደለም።
ኢሳያ አፈወርቂ እንዳሉት ድንበር ጉም ነው። ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አብረን የምንወድቅ፥ አብረን የምንነሳ አንድ ሕዝብ ነን።

ለጊዜው ደሞ ሁለትም ሕዝቦች ነን።  መርዙ ፈጽሞ እስኪረክስ..https://www.youtube.com/watch?v=83QidnZWpyo.

Filed in: Amharic