የጦርነቱ ክፍል ሁለት ምእራፍ ሁለት ቀጣዪ የጦርነት ምን ይመስላል???
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
📌 – የጦርነቱ ክፍል አንድ እንዴት ተጠናቀቀ??
የአፍሪካን ቀንድ ካርታ ቀያሪው ጦርነት የተጀመረው መስከረም 10 ቀን 2019 ከትግራይ መቀሌ በዘመነ ካሴ አንባቢነት የኢትዮጲያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና የሚባል ስብስብ ህልውናውን ባበሰረ ሁለተኛ ቀን ማክሰኞ መስክረም 12 ቀን 2019 ለሊት ላይ ህወሃት በአክሱምና በመቀሌ ያለውን አለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ በመቆጣጠጠና ጠባቂዎቹን በቁጥጥር ስር በማድረግ ለረቡእ መስከረም 13 ቀን ንጋት ላይ በራያ አላማጣ ሶሳት ግንባር እና በአፋር ግንባር ጦርነት በመክፈት አቢይ መራሹን የብልጽግናን እድገዛዝ ደምስሶ የመገርሰስ ዘመቻ ህወሃት ጀመረች።
ጦርነቱ ሰባት ታጣቂ ስብስቦችን የያዘው ትብብር ለህልውና በሰባቱም ድርጅቶቹ በአንድ ላይ ፣ በአንድ ግዜ በስድስቱ የኢትዮጲያ ክልል – ማለትም በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ሱማሊያ፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ባለው የአገዛዙ ሰራዊት ላይ ጦርነት ከፍቶ አገዛዙን መገርሰስ ሲሆብ የጦርነቱም ዋና አላማና ግብ :-
1ኛ- የብልጽግናን አገዛዝ መገርሰስ
2ኛ- የሽግግር መንግስት መመስረት
3ኛ- በሽግግር ወቅት በሚካሄድ ሕዝባዊ ውይይትና ህዝበ ውሳኔ
ሀ- የሀገረ ኢትዮጲያን ሉዓላዊ የግዛት አንድነት ለማስቀጠል ሕዝበ ውሳኔ ማካሄድ
ለ- የኦሮሞና የትግራይ ሕዝብ በተናጠል በሚያደርጉት ሕዝበ ውሳኔ ከኢትቶጲያ ጋር የመቀጠል እና ያለመቀጠል ሕዝበ ውሳኔን ማካሄድ
– የተከዜ ዘብና የራያ አላማጣን ዘብ ታጣቂን ትጥቅ አስፈትተው በመበተን የሰራዊቱን አዛዥና አመራርን በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ ማቅረብ …
4ኛ- የትግራይን እና የኦሮሚያን ሕዝብ የተናጥል ሕዝበ ውሳኔን የ”ትብብር ለህልውና” ሰብሳቢ ዘመነ ካሴ እውቅና ሰጪነት ተፈጻሚ የማድረግ እቅድ ፣ አላማና ግብ ይዘው ጦርነቱን እንደጀመሩ – እሁድ መስከረም 17 ቀን 2019. ም አራቱ የትብብሩ አመራሮች አማኑኤል አሰፋ፣ ሄኖክ አዲሴ፣ ጃል ጅሬኛና አብዱራህማን ሆነው በሰጡት የመጀመሪያና የመጨረሻ የትብብሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቋማቸውን በግልጽ አደባባይ ይፋ አድርገዋል።
ይህንን አላማቸውን ከግብ ለማድረስ የ”ትብብሩ” ሰባት አባላት በአንድ ላይ፣ በአንድ ግዜ እኩል በስድስቱም ክልል ጦርነት እንዲከፈት አደረጉ። የአገዛዙ ግዙፍ ታጣቂ ሰራዊት በሰሜን ወሎ ቤተአምሃራ ቆቦ ላይ ከ 200.000-250.000 ሺህ ሰራዊት ያከማቸበት ሁኔታ ግምገማ በማድረግ ጦርነቱን በባላይነት የሚያዘው ህወሃት ይህንን በቆቦ ላይ ያለውን ያገዛዙን ሰራዊት ከበባ አድርጎ መደምሰስ ማለት – ልክ በ1980 ሽሬ ላይ ግዙፉን የደርግ 604 ኮር መደምሰስ ማግሰት የትግራይ ክፍለ ሀገር የኢሰፓ ተጠሪ ለገሰ አስፋው ውሳኔ ሰጭነት የደርግ ሰራዊት የትግራይን ክፍለሀገር ሙሉ በሙሉ ጥሎ እንደወጣ ሁሉ ቆቦ ላይ ያለውን የአገዛዙን ሰራዊት መደምሰስ ማለት አራት ኪሎ ያለውን ብልጽግናን ማሸነፍ ማለት ነው በሚል ግምገማ በአጭር ቀናት ውስጥ አቢይ አህመድ ዛሬ ሰኞ መስከረም 25 ቀን 2019 የከፈተውን አዲስ ፓርላማ ከመክፈቱ በፊት ከስልጣን ይገረሰሳል በሚል እምነት ጦርነቱን ህወሃቶች ሊያውጁና ሊያቀጣጥሉት ቻሉ።
ጦርነቱ በተጀመረ ሶስትና አራት ቀናት በምስራቅ ጦር ግንባር በአፋር በኩል የህወሃትና የአፋሪ አጉጉሞ በጋራ ባደረጉት የማጥቃት ጦርነት በቀጠናው ያለውን የአገዛዙንና የአፋር ክልል ልዩ ኃይልን በመደምሰስ ሰፋ ያለ ግዛት መቆጣጠር የቻሉ ሲሆን በሰሜን ወሎ ቤተ አምሃራ በራያ አላማጣ፣ በዋግህምራና በቆቦ ወልዲያ ግንባር በሰሜን የህወሃትና የአገው ታጣቂዎች በአንድ ላይ ከታች በደቡብና በማእከላዊው ወሎ ቤተ አምሃራ በአፋብን ምንሊክ 1ኛ እዝ በኩል እጅግ መጠነ ሰፊ የማጥቃት እርምጃ በመክፈት ብርቱ ፍልሚያዎች የተካሄዱ ሲሆን በደቡብ በኩል በፋኖ በኩል ስኬታማ ዘመቻ በማድረግ ወሳኝ ስፍራ በመቆጣጠር ቆቦ ያለውን የአገዛዙን ሰራዊት ከደጀን ጋር እንዳይገናኝ የመቁረጥ ተግባር መፈጸም የቻሉ ቢሆንም በሰሜን በህወሃትና በአገው ታጣቂ በኩል ግን ከፍተኛ ዋጋ በመክፈል ወደ ቆቦ የሚያደርጉትን ግስጋሴ ለመግታት ተገደደ።
ቆቦ ላይ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ይህንን የመጀመሪያ ዙር ማእበል ታጣቂን እየተከላከለ ለቀናት ከቆየ በኃላ በአራተኛው ቀን መውሰድ በጀመረው መልሶ የማጥቃት እርምጃ ላለፉት አንድ አመት በህወሃት እጅ የነበሩትን ስድስቱን የራያ አላማጣን ወረዳዎችን – አላማጣ፣ ሰቆጣ፣ ምሆኒ፣ ኮረም፣ግራ ካሱ፣ ማይጨው በማስለቀቅ መልሶ ለመቆጣጠር የቻለ ሲሆን ህወሃት ከማይጨው በኃላ በምስራቅ አፋር ግንባር ያለውን ሰራዊታን እና በደቡብ ትግራይ ከሰሜን ወሎ ቤተ አምህራ ጋር በሚያዋስነው ተጎራባች ወረዳዎች ውስጥ ያለውን ሰራዊታን በማውጣት Orderly Retreat ሳይሆን From order to Disorder በሆነ ሁኔታ ሰራዊታ ፍርስርሱ ወጥቶ ወደ ሰሜን ትግራይ በማቅናት ዝርክርክ ብሎ መሸሽ በመጀመር መቀሌን እንካን ከከተማዋ ወጣ ብሎ ለመከላከል ቅንጣት ሳይሞክር ወደ ሰሜን አዲግራት በማቅናት የአገዛዙ ሰራዊት መቀሌ ከተማን ጨምሮ ደቡብ፣ ደቡብ ምእራብ፣ ምስራቅ እና ማእከላዊ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ቻለ።
ሽሽቱ የጠላትን የአገዛዙን ሰራዊት ወደ ውስጥ ስቦ የመምታ ስልታዊ ማፈግፈግ ሳይሆን አዲስ አበባን በሳምንት እድሜ ውስጥ እንያዛለን ለዚህ ደግሞ ቆቦ ላይ ያለውን ግዙፉን የአገዛዙን ጦር መደምሰስ አለብን በሚል የውጊያ እቅድ ወደ ቆቦ በገፍ የዘመተው የህወሃት ሰራዊት አከርካሪውን የሰበረ ብርቱ ምት ካረፈበት በኃላ በተፈጠረ ሽሽት – በወታደራዊ ሳይንስ Dominoes Effect ተብሎ የሚገለጸውና በአንድ የጦር ውጊያ የአንድ ኮር፣ የአንድ ክፍለ ጦር ወይም የአንድ ወሳኝ የጦር ግንባር ተመትቶ መፍረስ በአጠቃላይ ያለውን ሰራዊትና Eventually የሰራዊቱን ባለቤት የአገዛዙን መገርሰስ ያስከትለል የሚለው ፎርሙላ ነው ህወሃት ላይ የደረሰው እንጂ አንዳንድ ሆድ አደር ሴኩቱሬዎች ለማለት እንደሚሞክሩት ሽሽቱ ስልታዊ ማፈግፈግ ፈጽሞ አይደለም። ለምሳሌ ህወሃት ብልጽግና የሚሸነፈው አራት ኪሎ ላይ ሳይሆን ቆቦ ላይ ነው እያለች ስትገልጽ፣ ይህንን ቆቦ ላይ ያለውን ግዙፉን የአገዛዙን ሰራዊት መደምሰስና እንዲበተን ማድረግ ማለት በወታደራዊ ሳይንስ Dominoes Effect በሚባለው ህግ መስረት አጠቃላይ የአገዛዙ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በመፍረስ ሽሽት ውስጥ ስለሚገባ ወደ አዲስ አበባ የምናደርገው ጉዞ አጭርና ቀላል ይሆናል በሚል ስሌት ነበር። የሆነው ግን የተገላቢጦሽ በመሆን ቆቦ ላይ ያለውን የአገዛዙን ሰራዊት ለመደምሰስ ግዳጅ የተሰጠው የህወሃት ሰራዊት ተመትቶ አከርካሪው ሲሰበር የተረፈው የህወሃት ሰራዊት አዛዦቹን እየገደለ ለማስቆም በማያስችል ሁኔታ Disorderly ሆኖ ወደ ኃላ ይፈረጥጥ ጀመረ። አንዴ መሸሽ የጀመረን ሰራዊት ማስቆም እጅግ አዳጋች ከመሆኑም በላይ ፊት ለፊቱ ቆሞ ሊያስቆም የሚሞክረውን አዛዥ ግንባር ከማለት ወደ ኃላ የማይል ስለሆነ የግንባሩ መፍረስ እንደተሰማ ደብረጺዮን በብርሃን ፍጥነት – እየሸሸ ያለው የህወሃት ሰራዊት መቀሌ ከመድረሱ በፊት – ቀድሞ መቀሌን ለቆ በመውጣት ወደ አስማራ ተጉዞ ከአስመራ ሆኖ ባወጣው መግለጫ ህወሃት የመደበኛ ውጊያ Conventional War ትቶ የሽምቅ ጎሬላ ውጊያ የጀመረ መሆኑ በመግለጽ ወደ ትግራይ የገባው የአገዛዙ ጦር ይቀበራል እንጂ ከትግራይ አይወጣም ሲል አሳወቀ።
ዛሬ ሰኞ መስከረም 25 ቀን 2019 ላይ ሆነን የጦርነቱን ሁኔታ ስንገመግም ጦርነቱ ከተጀመረበት እለት አንስቶ ዛሬ የህወሃት ሰራዊት ከኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ከተሞች አዲግራት (ከዛለአንበሳ 37ኪ ሜ ርቀት ላይ ያለ) በአድዋ፣ አክሱም፣ኢሮብ፣ ባድመ፣ አሲምባ፣ ተምቤን ፣ ሽሬና መሰል የትግራይ ሰሜናዊ ቀጠና ላይ መልሶ የማሰባሰብ ሙከራ እያደረገ ያለበት ሁኔታ ሲሆን ይህም የጦርነቱ ምእራፍ አንድ ፍጻሜ ብለን እንገልጸዋለን።
የዚህ ጦርነት ምእራፍ አንድ (ክፍል አንድ ) ማለት ደብረጺዮን መራሹ የህወሃት ድርጅት ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን ለሊት ለረቡእ መስከረም 13 ቀን አጥቢያ ላይ በአጭር ቀናት ጦርነት ቆቦ ላይ ያለውን የአገዛዙን ሰራዊት ደምስሰን ወደ አዲስ አበባ በማቅናት የብልጽግናውን አገዛዝ እንገረስሳለን ተብሎ በጀመሩት ጦርነት የህወሃት ሰራዊት ተደምስሶ የተረፈው ወደ ሰሜን ትግራይ በመሸሽ የህወሃት አመራሮች ወደ ጎረቤት ኤርትራ የተሰደዱበትና መቀሌን ጨምሮ ከ55-60% ያህል የትግራይ ግዛት በአገዛዙና በTPF ታጣቂ ቁጥጥር ስር የገባበት ደረጃ ድረስ ያለውን የሚገልጽ ሲሆን የጦርነቱ ክፍል አንድ ተብሎ የሚገለጽ ሲሆን የዚህን ጦርነት ክፍል ሁለት እንደሚከተለው ይቀርባል።
📌 – የአፍሪካን ቀንድ ካርታ ቀያሪው የሰሜን ጦርነት ምእራፍ ሁለት ምን ይመስላል?.?
ጦርነቱን ለምንድነው የአፍሪካን ቀንድ ካርታ ቀያሪ እያልን የምንገልጽበትን ምክንያት ቀድመን እንግለጽ።
በዚህ ጦርነት አሸናፊው ማን ሆነ ማን የአፍሪካን ቀንድ ካርታ ይቀይራል ሲል በኢትዮ- ኤርትራ እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ላይ ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ጥናት እያደረገ ያለው ኖርዌያዊው ፕ/ር ሻትል ጦርነቱ በተጀመረ ማግስት የጦርነቱን ፍጻሜ እንደሚከተለው እስቀምጣል።
ይህ ጦርነት በመሸናነፍ ሳይሆን በድርድር ካልቆመ በስተቀር – በአንጻሩም ጦርነቱ ማን ሆነ ማን በአንዱ አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ከሆነ የአፍሪካን ቀንድ ካርታ ይቀይራል።
1ኛ- ጦርነቱን በአቢይ መራሹ የብልጽግናው አገዛዝ አሸናፊነት የሚደመደም ከሆነ የኢሳያስ አገዛዝ ተገርስሶ በምትኩ ለኢትዮጲያ ታማኝ የሆነ ፑፔት አስመራ ላይ እንዲቀመጥ በማድረግ አሰብን ወደ ኢትዮጲያ የማካተት ስራ ይፈጸማል። ይህም በአፍሪካ ቀንድ ካርታ ላይ ለውጥ ያመጣል።
2ኛ- ጦርነቱ በትብብር ኃይሎች አሸናፊነት የሚጠናቀቅም ከሆነ ኢትዮጲያን አዲስ የኦሮሚያ፣ የትግራይና የሱማሌ ክልሎችን መገንጠል ይፋ በማድረግ ኢትዮጲያን በሶስትና አራት አዳዲስ ሀገራት -እንደ ዩጎዝላቪያ የማድረግ ስራ ይፈጽማሉ በማለት ፕሮፌሰሩ ገልጻል።
የፕ/ር ሻትል ድምዳሜ ግምት ሳይሆን ሁለቱም ኃይሎች ማለትም የብልጽግናው አገዛዝና የህወሃት መራሹ ትብብር ለህልውና አላማና የሚታገሉለትን ግብ መስረት በማድረግ በማድረግ ስለሆነ ውሃ የሚያነሳ እይታ ሆኖ አግኘተነዋል።
የዚህ ጦርነት ምእራፍ ሁለት ከምእራፍ አንድ የጦርነት ሁኔታ በሶስት መሰረታዊ ነጥቦች ከምእራፍ ሁለት የጦርነቱ ክፍል የተለየ ሆኖ እናያለን።
📌 1ኛ- የህወሃት ታጣቂ በቀጣይ የሚያደርጉት ውጊያ በሽምቅ ውጊያ የመሆኑ
📌 2ኛ- የኤርትራ ሰራዊት የጦርነቱ አካል ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ የተፈጠረበት
📌 3ኛ- እሁድ መስከረም 24 ቀን 2019 በግብጽ ካይሮ የተሰባሰቡት የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኤርትራና የሱማሊያ መንግስታት ስብሰባና የጋራ ስምምነት ቢያንስ በዲፕሎማሲ፣ በመረጃ፣በሎጀስቲክስ ድጋፍ በማቅረብ ሊሳተፉ የሚችሉበት ሁኔታ የተፈጠረው በዚህ የጦርነቱ ምእራፍ ሁለት ክፍል ላይ ነው።
ህወሃት ከ 60-70% የሆነውን ተራውንና ተዋጊ ሰራዊታን እንደያዘች ይገመታል። ክፉኛ የተዋጋቺውና ዋጋ የከፈለቺው በወሎ ቤተአምሃራ፣ በራያ አላማጣ፣ ሰቆጣ፣ ዋግህምራና በቆቦ ግንባር መሆን Once በእነዚህ ግንባሮች የተዋጊ ሰራዊታ አከርካሪን የሰበረ ምት እንዳረፈባት በሁሉም ግንባር ያለው ሰራዊት ሽሽት ነው የጀመረው እንጂ በመልሶ ማጥቃት የአገዛዙን ሰራዊት ለመመከት አንዳችም ሙከራ አላደረገችም። በራያ፣ አላማጣ፣ ቆቦ፣ ዋግህምራ ግንባር ለደረሰባት ተስፋ አስቆራጭ ዱላ ውስጣዊ መረጃ አቀባይ ከሀዲ ክህደት ፈጽሞብኝ ነው በሚል በርካታ የጦር አዛዦች ላይ የርሸና እርምጃ ፈጽማለች። በእነዚህ ግንባሮች በትንሹ አምስት ያህል የህወሃት ኮሎኔሎች በአገዛዙ ሰራዊት የተደመሰሱ ሲሆን ለደረሰባት ሽንፈት ለአገዛዙ መረጃ በማቀበል ክህደት ፈጽመዋል ያለቻቸውን በደርዘን የሚቆጠሩ አመራሮች ላይ እርምጃ ወስዳለች። ይህ ሁኔታ የደቡብ ትግራይ ግንባር ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ፈርሶ ስርዓት አልባ በሆነ ሩጫ ሰራዊቱ ተንዶ ማስቆም በማይቻል ሁኔታ ወደ ሰሜን ለመሸሽ በቅታል።
የጦርነቱ ምእራፍ አንደ የማዘዣ ጣቢያ መቀሌ ሲሆን አሁን ግን የጦርነቱ ምእራፍ ሁለት የማዘዣ ጣቢያ የአድዋ ከተማ እንድትሆን የተመረጠች ሲሆን ከሁለት ቀን በፊት ቅዳሜና እሁድ መስክረም 23 እና 24 ቀን 2019 በአድዋ፣ በአክሱም፣ በአዲግራት፣ በተምቤን፣ሽሬ፣ በኢሮብ ከተሞች በፒክ አፕ ላይ በተጫነ ሞንታርቦ ውስጥ ለውስጥ እየዞሩ የክተት ጥሪ አዋጅ ሲያያተላልፉ የዋሉ ሲሆን ህወሃት ቅዳሜ መስከረም 23 ባወጣቺው መግለጫ
1ኛ- የትግራይ ሕዝብ እራሱን በራሱ ለመምራት እስከመገንጠል ሕገ መንግስታዊ መብቱን ለማስከበር ይታገላል።
2ኛ- ጦርነቱን በሽምቅ የጎሬላ ውጊያ እንቀጥላለን
3ኛ- በሀገር ውስጥ እና በዲያስፖራ ያለው የትግራይ ተወላጅ በሙሉ በመካከላችን ያለውን የሀሳብና የፖለቲካ ልዩነትን ወደጎን በማድረግ ያልተቃረጠ ድጋፍ እንድታደርጉ
4ኛ- እድሜው ለጦርነት የደረሰ ተጋሩ በሙሉ ወደ ትግል እንዲገባ የሚል የክተት ጥሪ አዋጅ አውጃለች።
የአድዋ ከተማን የቀጣይ የጦርነቱ ምእራፍ ሁለት የማዘዣ ጣቢያ በማድረግ እነ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) ተስፋዬ ባንዳ (ወዲ እምቤይቴ) ብርሃነ ነጋሽ (ወዱ መድህን ) እና ጌታቸው አሰፋ ወደ እሳመራ የተጋዙ ዲሲሆን ከእነሱ በታች ግን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በአደዋ ከተማ በመክተማቸው አገዛዙ ተከታታይ የድሮን ድብደባ almost daily basis, እያካሄደ ይገኛል።
የጽምዶ አባልና መስራች አንዱና ዋናው የሆነው የኤርትራው የሻእቢያው መንግስት እስካሁን ባለው የጦርነቱ ሂደት ላይ እንዳልተሳተፈ ቢታወቅም በቀጣይ በጦርነቱ ምእራፍ ሁለት የሻእቢያ ከህወሃት ጋር ሆኖ ለመዋጋት የሚያስችል ሁኔታን ሊፈጥር የሚችለው የአቢይ መራሹ አገዛዝ በኤርትራ ላይ የሚያካሂደው ፖሊሲ እጅግ ወሳኝ ሆኖ ነው የምናየው።
አሁን አሁን ማሰባሰብ በቻልነው መረጃ መሰረት የኤርትራ መንግስት እየፈረጠጠ ያለው የህወሃት ሰራዊት ድንበር አልፎ ወደ ኤርትራ እንዳይገባ ያገደ ሲሆን ወደ አስመራ እንዲገቡ ለአራቱ የህወሃት አመራሮች ደብረጺዮን፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሞንጆሪኖ እና ወዲ እምቤይቴ ብቻ ለይቶ እንደፈቀደ ነው ማወቅ የቻልነው።
ከዚህ አንጻር ቀጣዪ ምእራፍ ሁለት የጦርነቱ ገጽታ በተበታተነው የህወሃት ሰራዊት ሽምቅ ሽምቅ ውጊያ ከሰሜን አቅጣጫ ሊከፈት ይችላል የሚል ግምት ያለ ሲሆን የአሁኑን ሽምቅ ውጊያ ከባለፈው የ 2013-2015 ከነበረው የሽምቅ ውጊያ ለየት የሚያደርገው ከአቢይ መራሹ የብልጽግናው ሰራዊት ጎን ከTDF እራሱን ገንጥሎ የወጣው እና ከ20 በላይ ጄኔራሎችን በስሩ የያዘው በጄ/ል ወዲ አንጥሩ የሚመራው የTPF ሰራዊት መኖር ዛሬ ተበታትኖና በሰሜን የትግራይ ወረዳና አውራጃዎች ውስጥ እየተሰባሰበ ያለው የህወሃት ሰራዊት መልሶ ለሚከፍተው የሽምቅ ውጊያ ትልቅ ተግዳሮት እንደሚሆነው ሁኔታው ይገልጻል።
ሆኖም የ2013ቱ አይነት የተቀናጀ የሽምቅ ውጊያ ዳግም ዘንድሮ በ2019 ይታያል ብሎ ለመግለጽ የማያስደፍሩ በርካታ ነጥቦች ቢኖርም ዋናው ግን በ2013 ያለው ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና ንቅናቄ ዘንድሮ በእጅጉ ቀንሶ ያለበት ሁኔታን ነው መጥቀስ የሚቻለው።
የተበተነው የህወሃት አመራሮች በሻእቢያና በአማራ ፋኖ ላይ ባደረጉት ግምገማ ሁለቱ ኃይሎች በስምምነታችን መሰረት ግዴታቸውን አልተወጡም የሚል የቅሬታ ግምገማ አድርገዋል። የአማራ ፋኖ መዋጋት ባለበት ሙሉ አቅሙ አልተዋጋም፣ኤርትራም ሰራዊት አላከችም ያሉ ሲሆን በተለይ አሁን ሻእሺያ ከትግራይ የተላከውን ከፍተኛ ሀብትና ንብረት ተቀብሎ የህወሃትን ሰራዊት እና አመራር ወደ ኤርትራ ግዛት እንዳይገባ ቦርደር ዘግቶ አራቱን የህወሃት መሪዎችን ብቻ መቀበላቸው ታላቅ የመከዳት ስሜት በህወሃት ሰራዊት ላይ ሊፈጥር ችላል።
ምእራፍ ሁለት የጦርነቱ ገጽታ በሽምቅ ውጊያ የሚካሄድ በመሆኑ የተራዘመ ጊዜ እንደሚወስድ ይጠበቃል። ይህ ማለት አገዛዙ ወደ ትግራይ ክልል የሚልከው የተዋጊ ሰራዊት ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲሄድ የሚያደርግ ከመሆኑ አንጻር ለአማራ ፋኖ እጅግ ጠቃሚ እድል እንደሚፈጥር ከወዲሁ መግለጽ ይቻላል።
በቀጣዪ ጦርነት ምእራፍ ሁለት ውስጥ የአማራ ፋኖ ሊኖረው የሚችለውን እድልና አደጋን በተመለከተ በቀጣይ እራሱን በቻለ ለብቻው የማቀርበው ይሆናል። አበቃሁ።















