>

ከቄሮዎች ለኢትዮጵያ ወጣቶች የተላለፈ መግለጫ!!!

ከቄሮዎች ለኢትዮጵያ ወጣቶች የተላለፈ
መግለጫ!!!
ዘሚካኤል ጆርጅ
በመጀመሪያ ለተገኘዉ ድል ለኛ ለኢትዮጵያኖች እንኳን ደስ አለን ማለት እንፈልጋለን::
ሁለት ነገር ለማለት ነዉ ይህን መግለጫ እንዲወጣ የተፈለገዉ፡፡
1ኛዉ. ትግላችንን እናስተባብር!!!
እኛኦሮሞ ቄሮዎች ከአማራ ፋኖዎች ጋር በመሆን የነበረዉ ስርዓትን ለመጣል የብዙ ወንድሞቻችንን ህይወት እና የአካል መጉደል ተቋቁመን ለዚህ በቅተናል፡፡
ስለሆነም የተጀመረዉ ለዉጥ እና ተስፋ ሰጪ ጉዳዮች ለመደገፍ እና የፈረሰዉን ግንብ ፍርስራሽ ለመጥረግ ከማንም በላይ ትልቁ ሀላፊነት የኛ
ስለሆነ መድረግ የሚጠበቅብንን እንደ ሚከተለዉ አስቀምጠናል የኦሮሞ ቄሮዎች ትግል ትናንት በኦሮሚያ ዉስጥ ተግዶ የነበረ ነበር አሁን ግን ወደ ታላቅ ሀገር ለአፍሪካ ኩራት የሆነች ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እንድትመራ ለማድረግ ነዉ ትግላችን ለማለት እንፈልጋለን፡፡
ስለሆነም ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ የቄሮ ብቻ ትግል ፋይዳ አይኖረዉም፡፡
ስለሆነም ከ ፋኖዎች፣ዘርማዎች እናም ከሁሉም የኢትዮጵያ ወጣቶች ጋር በመደመር አንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድርጅት እንዲቋቋም እንፈልጋለን፡፡
ይህንንም ዶ/ር አብይ እንደሚያግዘን ባለ ሙሉ ተስፋዎች ነን፡፡
ድርጅቱ ከየብሔረሰቦችን አንድነት ወደ አስተማማኝ ደረጃ እንደምያደርስ እና የኢትዮጵያ ፖሎቲካ ዉስጥ ትልቅ ቦታ ይኖረዋል የሚል ሙሉ አምነት
አለን፡፡
2ኛዉ.ጀዋርን አብረን እንቀበለዉ!!! 
የጀዋር ሞሀመድን ወደ ኢትዮጵያ መግባት ተከትሎ እኛ ቄሮዎች ትልቅ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን ስለሆነም የኛ የቄሮዎች ደስታ ማለት
የፋኖዎችም ደስት ችምር ስለሆነ ጀዋርን አብረን እንቀበለዉ በማለት አንድነታችንን እናሳይ ስንል ትልቅ ክብር ይሰማናል ጀዋር ሞሀመድ ሀገሩስ
ገብቶ አንዱ የኢትዮጵያ ሀብት እንደሚሆን እናምናለን፡፡
ኢትዮጵያን እኛ ልጆቿ አለንላት!
አቢዮተኛው ጃዋር መሐመድ እሁድ አ.አ ይገባል!!!
ኤርሚያስ ቶኩማ
ጃዋር መሐመድ የተለየ ፖለቲከኛ ነው፤ ወያኔን እንዴት ማስጨነቅ እንደሚቻል ያውቅበታል፤ ሲያሻው በአንድ ፅሁፍ የኦሮሚያ ጎዳናዎችን ጭር ያደርጋቸዋል ለውጥ ሲታየው ደግሞ ሁሉም ህዝብ ከዶክተር አቢይን ጎን ይቆም ዘንድ አጋርነቱን ያሳያል።  የተወሰኑ ሰዎች የጃዋር እንቅስቃሴ ብዙም አይጥማቸውም፤ ገሚሶቹ ጎሰኛ ነው በማለት  ሲጠሉት የተቀሩት ግን ያለምክንያት ለየት ብሎ በመታየቱ ብቻ ይጠሉታል፤  በጃዋር  አመለካከት የማንስማማ ብንኖር እንኳን መቀበል ያለብን እርሱ ብቻውን ከፖለቲካ ድርጅትም በላይ ነው።
ይህ አብዮተኛ እሁድ ጠዋት ሸገር ይደርሳል ሰብሰብ ብለን በሃገራችን እየታየ ስላለው ለውጥ አስተዋጽኦ በማድረግህ እናመሰግንሃለን እንለዋለን።
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የአዲስ አበባ ቢሮ ይመረቃል!!!
ጥጋቡ ወልዴ
የድርጅቱ ዳሬክተር  ጃዋር መሐመድ በተገኙበት እሁድ በሚሊንየም አዳራሽ ይመረቃል። በምረቃ ስነ ስርዐቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግለዎችና ቄሮዎች ይገኛሉ ተብሏል።
OMN በዝግጅቱ 500 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ ያቀደ ሲሆን፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ድንኯኖች ዘርግተው ገቢ በማሰባሰብ ላይ ይገኛሉ።
ዛሬ #በሀረር ከተማ በተከናወነ የገቢ ማስገኛ ዝግጅት 6 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ የተገኘ ሲሆን፣ የዋና ዳሬክተሩ አቶ ጃዋር መሀመድ ምስል ለጨረታ ቀርቦ #1ሚሊየን ብር ተሽጧል።
Filed in: Amharic