>
11:14 pm - Tuesday August 16, 2022

ህወሀቱ" የአማርኛ ክንፍ " ብአዴን የተባለ ሙትቻ ድርጅት ዛሬ የለም!!! (ቹቹ አለባቸው)

ህወሀቱ” የአማርኛ ክንፍ ” ብአዴን የተባለ ሙትቻ ድርጅት ዛሬ የለም!!!
ቹቹ አለባቸው
ይሄ የአረናዉ ሰዉየ :አይተ አብረሀ ደስታ ደግሞ ምን እያለ ነዉ?
ጉድ እኮ ነዉ: ህወሀት ይገለናል: አረናና ሰዉየዉ ደግሞ በሞታችን ላይ ይሳለቁብናል። አቶ አብረሀ ደስታ: አረና የተባለ የህወሀት የዉሸት ተቃዋሚ ድርጅት መሪ ነዉ አሉ። ታድያ ይሄ ሰዉየ: ህወሀት በራያ አማሮች ላይ ያካሄደዉን ጭፍጨፋ ተከትሎ የሰጠዉ አስተያየት በጣም ገራሚ ነዉ። ሰዉየዉ በህወሀት የተገደሉት አማሮች ጉዳይ አንዳች ነገር ሳያሳስበዉ: “በአማራና ተግራይ ክልሎች መካከል እየተፈጠረ ላለዉ ችግር: መንስኤዉ አዴፓ ነዉ” አይነት የተወላገደ ሀሳብ መሰንዘሩን በማህበራዊ ሚዲያ ተመለከትኩ። እኔም: የህወሀትን ግድያ: ከአረናዉ ሰዉየ አይዞህ ባይነት ጋር አስተሳስሬ ስመለከተዉ: ነገሩ “ግም ለግም:ተያይዞ ያዝግም” የሚለዉ አባባል ትዝ አለኝ።
ለሁሉም: ለሰዉየዉ ያልበሰለ ሀሳብ: መልስ ይሆነዉ ዘንድ:አቶ ንጉሱ ጥላሁን: በሚያምር ሁኔታ 16 ቁጥር ሚስማር ቸንክሮለታል። ሰዉየዉ መስሚያ የለዉም እንጅ። የህወሀትና አረና: መሰረታዊ ችግር አንድና ያዉ ነዉ: ይሄዉም  ለነሱ ሲታዘዝና: ራሱን መሆን ተስኖት የከረመዉ አይነት ብአዴን: የተባለ ድርጅት አማራ ክልል ዉስጥ እንዲኖር። ነገር ግን : ህወሀትና አረናዊያን ተስፋ አልቆረጡም እንጅ: የህወሀትን ፍላጎት ሲያስፈጽም የኖረዉ: ብአዴን አይነቱ ደካማ ድርጅት ዳግም ላይመለስ ተሸኝቷል። ነገር ግን ህወሀትና አረና ነገሩ “የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ” ሆኖባቸዉ እንጅ:  በአማራ ክልል የነሱ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ የኖረዉ ብአዴን ከነግሳንግሱ ተሸኝቷል።
 ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ: በህወሀትና አረና ዘንድ የምንታዘበዉ እዉነታ ቢኖር: የአዴፓ ነገር የከበዳቸዉ መሆኑን ነዉ። እዉነት ነዉ: አዴፓ: አጭር በማይባል ጊዜ ዉስጥ: ራሱን በመሆን: ለህወሀትና አረና መሰሎቹ ወበ- ከንቱወች: ከባድ የራስ ምታት መሆኑ አይቀርም:መሆንም ጀምሯል። በበለጠ ሁኔታ ደግሞ: አዴፓ በዉስጡ የቀሩትን ቅሪቶች እያስወገደ ሲሄድ: ለህወሀትና አረና ከባድ እራስ መርዘን እንደሚሆንባቸዉ ይጠበቃል። ይሄም ማለት ደግሞ: ህወሀት: በአማራ ምድር: የለመደዉን እንደ ቀዳሽ ቄስ ዘዉ ብሎ ገብቶ የማንጨቧረቅ እድሉ አከተመ ማለት ነዉ።
——//////—–
በአጠቃላይ: የአቶ ሰዉየዉ መግለጫ: የሚነግረን ነገር ቢኖር:  ” እህት” ድርጅት ህወሀትና የህወሀት  “ተቃዋሚ” ድርጅት አረና : አዴፓን ክፉኛ የፈሩት መሆኑን ነዉ። ለህወሀትና አረና: ዴሞክራሲያዊ: እንዲሁም: ለትግራይና አማራ ክልሎች ወዳጅነት የሚሰራ አማራዊ  ድርጅት ማለት: ልክ እንደ ኢህዴን/ብአዴን: የትግራይንና ህወሀትን ጥቅም : በአማራ ክልል ዉስጥ የሚያስጠብቅ: ለሁለቱ ህዝቦች መልካም ግንኙነት ሲል: የአማራን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄወች የማያነሳ: እነዚህን ጥያቄወች የሚያነሳ ታጋይ ቢኖር እንኳን: ጉዳዩ የአማራንና የትግራይን ህዝቦች አንድነት የሚጎዳ ድርጊት ፈጽመሀል:ብሎ ከድርጅቱ የሚያባርር ድርጅት ማለት ነዉ።
ነገር ግን ዛሬ ላይ: አማራ ክልል ዉስጥ: አዴፓ እንጅ:የነ ህወሀቱ” የአማርኛ ክንፍ ” ብአዴን የተባለ ሙትቻ ድርጅት የለም። ዛሬ ያለዉ ድርጅት:ለህወሀት አገልጋይ ሳይሆን: እራሱን ለመሆን ወስኖ ራሱን በመፈለግ ላይ ያለ አዴፓ ነዉ። አዴፓ በአቶ ንጉሱ በኩል የሰጠዉ መልስም: ይሄን እዉነታ አመላካች ይመስለኛል ።
እንግዲህ : እኛም ቢሆን አዴፓን: በሁለቱ አዝጎች ላይ የቸነከርከዉን 16 ቁጥር ምስማር: ወደ 24 ቁጥር ከፍ አድርገዉ እያልን:እነ አዝግን ደግም”ግም ለግም: ተያይዞ ያዘግም” የሚለዉን አማራዊ አባባል: ጥሩ አድርገዉ እንዲያጣጥሙት: የዛሬዉ ግብዠረችን ነዉ። ከዚህም በተጨማሪ: የለመደች ጦጣ ሁል ጊዜ ሽምጠጣ የሚለዉን አባባል: ደጋግማችሁ አጢኑት እንላለን።
Filed in: Amharic