>
5:13 pm - Sunday April 19, 8714

"የእነዚህ አካላት ሴራ እነሱን በመቅበር የሚጠናቀቅ ይሆናል እንጂ ኦሮሚያን የግጭት ሜዳ ማድረግ አይሳካላቸውም"  የኦዴፓ መግለጫ

የእነዚህ አካላት ሴራ እነሱን በመቅበር የሚጠናቀቅ ይሆናል እንጂ ኦሮሚያን የግጭት ሜዳ ማድረግ አይሳካላቸውም” 
የኦዴፓ መግለጫ
OBN ህዳር 20 ፣ 2011  ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከመረራና እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ የተገኘውን ለውጥ ለመቀልበስ ስልጣንን ያለአግባብ ተጠቅመው ዘረፋ ሲያካሄዱ የነበሩና አሁን ጥቅሙ የቀረባቸው አካላት በተለያዩ ቦታዎች እሳትን በማቀጣጠልና የሰው ልጆች ላይ መፈፀም የሌለበት ወንጀል እንዲፈጸም፣ ዜጎች እንዲፈናቀሉና የክልላችን ሰላም እንዲናጋ እየሰሩ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
የእነዚህ አካላት ሴራ እነሱን በመቅበር የሚጠናቀቅ ይሆናል እንጂ ኦሮሚያን የግጭት ሜዳ ማድረግ አይሳካላቸውም ብሏል ፓርቲው በመግለጫው፡፡ እነዚህ አካላት የተጀመረው የህግ የባላይነትን የማስከበር ስራ እንዲስተጓጎል ሌተ ቀን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፣ እነዚህ ሌቦች የኦሮሞን የህዝብ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በማጋጨት እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በማጋጨት የጥፋት እጃቸውን እንደዘረጉ መግለጫው ያትታል፡፡
እንደ ፓርቲው መግለጫ፣ እነዚህ አካላት በቅርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የሱማሌ ወሰን አካባቢ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የግድያ እርምጃ ወስደዋል፣ ሰላማዊ ዜጎችንም አፈናቅለዋል፣የተቀናጀ ጦርነት በመክፈትም በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡
በዚህ በሰላማዊ ዜጎችና በኦሮሚያ ፖሊስ ላይ ለደረሰው አሳቀቂ ወንጀል ጥልቅ ሀዘን እንደተሰመው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው ገልጾ፣ በሌቦች፣ ዘራፊዎችና በሰው ልጆች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ላይ መውሰድ ከጀመርነው ሕጋዊ እርምጃ ወደኋላ አይመልሰንም ብሏል፡፡
በህዝባችን ላይ ይህንን ጉዳት ያደረሱ አካላት የገቡበት ጉድጓድ ገብተን ለሕግ እናቀርባቸዋለን፤ እንዲሁም እነዚህ አካላት ያላቸውን ኃይል በድጋሜ በማይጠገን መልኩ ሰብረን እንቀብረዋለን ብሏል የፓርቲ መዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው፡፡ ማንኛውም የሰበአዊ ጥሰት የፈፀሙ አካላት በሕግ የሚጠየቁ እንደሚሆኑ የማዕከላዊ ኮሚቴው መግለጫ ያስረዳል፡፡
Filed in: Amharic