>
5:13 pm - Saturday April 20, 5748

ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ሀብታሙ አያሌው ታሰረ

ዳዊት ሰለሞን [ጋዜጠኛ]

Habtamu Ayalew

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ የሆነውና በቅርቡ ሐገርና ፖለቲካ የሚል መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው ዛሬ ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ እንደወጣ ቦሌ ፍላሚንጎ አካባቢ በፖሊሶች ተይዞ መወሰዱን የአይን እማኞች ይፋ አድርገዋል፡፡


ሐብታሙ በምን ምክንያት በፖሊሶች እንደተያዘና ወዴት እንደተወሰደ የአይን እማኞቹ ባያረጋግጡም የፓርቲው አመራሮች በአሁኑ ሰዓት ፍላሚንጎ አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣብያ በማምራት ጉዳዩን ለማጣራት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

 

 የሺዋስ አሰፋ ማዕከላዊ ሲወሰድ ሐብታሙ አያሌው ያለበት አልታወቀም


Yeshiwassew Alemuየሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ ብዛት ያላቸው ፌደራል ፖሊሶች፣የደህንነት አባላትና ፖሊሶች መኖሪያ ቤቱን በመክበብና ወደ ውስጥ በመግባት ከያዙት በኋላ ቤቱን በመበርበር ለጊዜው ያልታወቁ ንብረቶችን በመያዝ ከየሺዋስ ጋር ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መውሰዳቸውታውቋል፡፡

ቤት ፈታሾቹ የየሺዋስን ቤት በሚበረብሩበት ወቅት የየሺዋስን ባለቤት ጭምር ወደ ውስጥ እንዳትገባ ማድረጋቸው አግራሞትን ፈጥሯል፡፡

በዚሁ ዕለት ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት በማምራት ላይ የነበረው አቶ ሐብታሙ አያሌው ቦሌ ደምበል አካባቢ እንደደረሰ ብዛት ያላቸው የደህንነት አባላት በፌደራል ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ሐብታሙን ይዘውት ሄደዋል፡፡የአንድነት አመራሮች ወደ ተጠቀሰው ቦታ በማምራት ድርጊቱ ሲፈጸም ከተመለከቱ ሰዎች የሐብታሙ መያዝን አረጋግጠዋል፡፡እስካሁን ድረስ ግን ሐብታሙን ይዣለሁ ያለ አካል አልተገኘም፡፡

 

 

 

 

 

Filed in: Amharic