(በፕሮፌሰር ሐብታሙ ተገኘ )
የአዲስ አበባ የጥንት ስም “በረራ” ነው፡፡በረራም ፣ የነገስታቱ ቀዳማዊ ዋና መቀመጫ ከተማ በመሆን ፣ ከአፄ ዳዊት ቀዳማዊ ዘመን ፣ (ከ1380-1413 ) ድረስ ፣ እንዲሁም በአፄ ልብን ድንግል ስርወ መንግስት ዘመን ፣ማለትም (ከ1408-1480) ፣ በረራ ከመቶ አመት በላይ አገልግላለች፡፡ በረራ ወረብ በሚባል አውራጃ ስር ትተዳደር እንደነበር ፣ የታሪክ መዛግብቶች ያስረዳሉ፡፡ ወረብ ታላላቅ አብያተክርስቲያኖች እና ቤተመንግስቶች የነበሩበት ፣ በጣም ሀብታም አውራጃ ነበር፡፡ በዚሁ ዘመን ፣ የግራኝ አህመድን ጦርነትን ከግራኝ ወታደሮች ጋር እየተዘዋወረ ሲዘግብ ፣ ወረብንና በረራን ያየው ፣ ሻሀብ አደዲን እብዱልቃዲር ፤ “ፉቱህ አል ሃበሽ” በተሰኘው መፀሐፉ ፣ “በረራን የሐበሾች ምድራዊ ገነት” ይላታል፡፡
የበረራን ታሪክ የፃፍነው ፣ አንዱን ነባር ፣ ሌላውን መጤ እና እንግዳ ለማድረግ አይደለም፡፡ ፅሑፉን ለማዘጋጀት የተፈለገው ፣ ስለ አዲስ አበባ የኋላ ታሪክ ያለውን የታሪክ ክፍተት ፣ በተወሰነ መልኩ ለመድፈን ያግዛል ፣ እንዱሁም ስለቦታው ታሪክ ኢትዮጵያዊያን ትክክለኛ መረጃና እውነት እንዲኖራቸው በማሰብ ነው፡፡ የዚህ ፅሑፍ ይዘት ፣ ያልነበረን ፣ ወይም ያልተነገረን አዲስ ታሪክ ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ ለዚህ ፅሑፍ የተጠቀምናቸው ማስረጃዎችም ፣ ከዚህ በፊት ስለ በረራ ታሪክ መፃፋቸው የታወቁ ምንጮች ናቸው፡፡ ይህ ፅሑፍ ሁለት አላማዎች አሉት፡፡ አንደኛው ፣ የበረራን ወይም የአዲስ አበባን የኋላ ታሪክ ባጭሩም ቢሆን ለመዳሰስ ነው፡፡ ሁለተኛው ስለ በረራ ፣ በኢትዮጵያዊያንም ሆኑ በውጪ አገር ፀሐፊዎች የተፃፉ ታሪኮችን ለአንባቢ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በተለይም ፣ የቦታው ተወላጆች ስለበረራ በሰጡት ምስክርነት ላይ የተፃፉትን ለማካተት ይሞክራል፡፡ የበረራን ታሪክ ያጠኑ ተመራማሪዎች ፤ ኦጂኤስ ክራውፎርድ ፣ ሪቻርድ ፓንክረስት እና ሀርትዌትግ ብሪትሪት ፣ ሳሙኤል ዎከር እና ማርኮ ቪጋኖ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ታዋቂው ጣሊያናዊ የካርታ ባለሞያ ፣ ፍራ ማውሮ ፣ በረራንና ባካባቢው ያሉ ከተሞች ፣ ወንዞች ፣ ተራሮች እና ገዳማት ፣ በ1450 አመተ ምህረት ባዘጋጀው የአለም ካርታ ፣ የቦታውን ተወላጆች በመጠየቅ አስፍሯቸዋል፡፡
የፍራ ማውሮ የአለም ካርታ ፣ በትክክለኛነቱ በአለም የተደነቀ ነው፡፡ ካርታው ፣ አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ጨምሮ አለምን ለማሰስ በዘመኑ ባደረጓቸው ጥረቶች ውስጥ ፣ ከፍተኛ ሚና ተጫውቶላቸዋል፡፡ ፍራማውሮ ለሳይንስ እውቀት እድገት ላደረገው አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ፣ የጨረቃ የተወሰኑ አካላት በስሙ ተሰይመውለታል፡፡ የበረራ ታሪክ ፣ ከአፄ ዳዊት ፣ ማለትም ከ1380-1413 – ቀጥሎም እስከ አፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግስት ፣ ከ1508-1540 ፤ ስለ በረራ የመጀመሪያው የታሪክ ማስረጃ ፣ በ1450 የተሳለ የአለም ካርታ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩት አፄ ዘረ-ያእቆብ ፣ ከ1434-1468 ድረስ የገዙት ናቸው፡፡ ነገር ግን የበረራ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል ማለት አይደለም፡፡ ከተማው ተመስርቶ ፣ አድጎ ፣ ለነገስታቱ መቀመጫነት እስኪበቃ ድረስ ፣ ብዙ አመታት መፍጀቱ አይቀርም፡፡ የአፍቃል መረጃ እንደሚያስረዳው ፣ “እንጦጦ ፣ ወይም በረራ” ፣ በዋናነት የአፄ ዳዊት ከተማ እንደነበር ነው፡፡ አፄ ዳዊት የዘረ ያእቆብ አባት ሲሆኑ ፣ የነገሱት ከ1380 አመት ጀምሮ ነበር፡፡ ስለዚህ ከፍራማውሮ የአለም ካርታ መዘጋጀት በፊት ፣ በረራ የአምሳ አመት እድሜ አስቆጥራ ነበር ማለት ነው፡፡ ካርታው በያዘው መረጃ ብዛትና ጥልቀት ፣ በዘመኑ ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡ የፍራማውሮ ካርታ የመጀመሪያው የሚታወቅ ሳይንሳዊ ካርታ ነው፡፡ ሳይንሳዊ የሚያደርገው ፣ በመሬት ላይ ባሉ ተጨባጭ እውነታዎች ላይ እንጂ ካርታው ከሃይማኖታዊ ግብአቶች ይልቅ ፣ በመሬት ላይ ያሉ ነበር እውነታዎች ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ በመሆኑ ነው፡፡ በካርታ ስራውም ብዙ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል፡፡ የኢትዮጵያን ካርታ የሚያሳየውን የዚህን ካርታ ክፍል እንደ ማስረጃ ተጠቅመነዋል፡፡
![](https://www.ethioreference.com/wp-content/uploads/2019/02/Addis-Abeba-Berara-Zena-adis-06022019-300x169.jpg)
በዚህ ፅሑፍ ውስጥ ያሉት ፎቶዎች እና አንድ ቪድዮ፣ የአዲስ አበባን ጥንታዊ የፈረሱ ፣ የነገስታት መኖሪያ ቤተመንግስት የሚያሳይ እና በአውሮፓዊያን የአጥኚ ቡድን ፣ እቦታው በመሆን ባደረጉት የቁፋሮ ጥናት የተረጋገጠ ነው፡፡ በተጨማሪም የሳተላይት ካርታው ፣ የምኒሊክ ቤተመንግስት ከተመሰረተበት እንጦጦ ፣ አካባቢ ይህ የቀድሞዋ ጥንታዊ ከተማ በረራ በትክክል የት ከስድስት መቶ አመት በፊት ተመስርታ ታገለግል እንደነበረች የሚያሳይ ማስረጃ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ብቻ ሳይሆን የፍራ-ማውሮ ካርታ እና የፍቱል ሃበሻ የአይን እማኝ ምስክርነቶች እና አያሌ መዛግብት፤ የአሁኗ አዲስ አበባ ፣ የቀድሞዋ ፣ የበረራ ከተማ ለመሆኗ ፣ በከፍተኛ ማስረጃ የተደገፈ ፣ ታሪካዊ ፣ የቀዳማዊ አፄ ዳዊት መናገሻ እንደነበረች ማሳያ ነው፡፡ በንባቡ ይማሩበት ፣ ሌሎቹንም ማስረጃዎች መርምሮ ለማስረዳት ፣ በዚህ ፅሑፍ ውስጥ የተጠቀሱትን ተመራማሪዎች ስራዎች በማየት ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
* የአጼ ዳዊት ከተማ አዲስ አበባ(በረራ)ና ሕልማቸው
* ከ500 ዓመት በፊት አጼ ዳዊት ስለ አዲስ አበባ ትንቢት ነበራቸው
Ze Addis
ያሁኗ አዲስ አበባ ላይ ከተማቸውን መስርተው የነበሩት አጼ ዳዊት : ስለ ከተማቸው ትንቢት ተናግረው ነበር:: ይቺ በረራ የተባለችው ከተማቸው በአህዛብ ወረራ ብርቱ ጉዳት እንደሚደርስባትና በኋለኛው ዘመን ግን እንደምትታደስ በሚገርም ሁኔታ ነው ትንቢት የተናገሩት::እንደተነበዩትም ባራራ በግራኝ ብርቱ ጉዳት ደረሰባት:: በኋላ በአጼ ምኒልክ ዘመን ታደሰች::
አጼ ምኒልክ አዲስ አበባን ድጋሚ አነሷት : አደሷት እንጂ አልቆረቆሯትም:: ብዙ ምስክር መጥቀስ ይቻላል:: የካ ያለውን የድንጋይ ፍልፍል ዋሻ ሚካኤልን ማን ሰራው? አጼ ምኒልክ የተነሱ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነው:: ዋሻ ሚካኤል ደግሞ የተሰራው በ5ኛ ው ክፍለ ዘመን ነው:(https://washamikael. wordpress.com/ )
እንጦጦ ራጉኤል ( የመጀመርያው የድንጋይ ፍልፍሉን) ቤተ ክርስትያን ማን ሰራው? አጼ ምኒልክ ከመነሳታቸው ቢያንስ ከ500 ዓመት በፊት የተሰራ የዋሻ ፍልፍል ቤተ ክርስትያን ነው::
እነዚህ አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ( Royal Churches)ናቸው:: የተሰሩት በመካከለኛው ዘመን በነበሩ ነገስታት ናቸው:: ነገስታቱም ያሰሩት መናሃርያቸው ስለነበረ ነው::
ልክ ላሊበላ : ነአኩቶ ለአብ እና ሌሎቹ ነገስታት በሮሃ ላይ የድንጋይ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት እንደሰሩ: የመካከለኛው ዘመን ነገስታትም እንዚህን አብያተ ክርስትያናት አንጸዋል:: የካ ምኒሊክ ከመነሳታቸው 500 ዓመት በፊት ሕዝብ ነበረው:: ድንቅ ቤተ መንግስታዊ ቤተ ክርስትያን ነበረው:: እንጦጦም እንደዛው:: https://uthiopia.com/barara- entoto-barara/
አስደናቂው ፎቶ
*************
አጼ ቴዎድሮስን ለመውጋት የመጡት እንግሊዞች የዘረረፏቸው መጽሓፍ ላይ ታሪኩ ከነስዕሉ አለ::የአጼ ምኒልክ አማካሪ የነበረው አልፍሬድ ኢልግ የጻፈልን መጽሓፍም ውስጥ ታሪኩን ታገኙታላችሁ::
ለዛሬ ፎቶውን እነሆ! የአጼ ምኒልክ የመጀመርያው ቤተ መንግስት ይሄ ነበር:: በጎን በኩል ተኝቶ ህልም ያየው ንጉስ አጼ ዳዊት ናቸው:: በኋለኛው ግዜ ከተማቸው እንደምትታደስ ያዩትን ህልም እንዲህ ነበር ሰዓሊው ያስቀመጠው::የፈረንሳይ ተመራማሪዎች ከጻፉት የተወሰደ ነው:: ( picture Credit እንዲል ፈረንጅ)
የድሮዋን በህረራ ያሁኗን አዲአ አበባ በተመለከተ የተጻፉ ብዙ ጥናታዊ ጽሁፎች አሉ:: በቃሌ መሰረት ለጠየቃችሁኝ ሁሉ ለመላክ እየሞከርኩ ነው:: አንዳንዶቹን የጥናት ወረቀቶች እዚህ ሊክ ላይ ታገኙታላችሁ::
ዋቢ መጻሕፍትና ሊንኮች
Vigano, M., The Names Lost, the Map Grasped. Central Shoa on the Fra Mauro map,
Academia.edu, 2015.
Fra_Mauro_map
Vigano, M., What of medieval Archaeology in Ethiopia? The quest for Barara, a plan forarchaeological urgencies, Academia.edu, 2010, pp. 14.
Barara_a_plan_for_ archaeological_urgencies
Vigano, M., Thirty-two historic/archaeo Sites in the Central Shoa-Addis Ababa area are set to prove its medieval, not recent origin, Academia.edu, 2014
baba_are_set_to_prove_its_ medieval_not_recent_origin