>
5:13 pm - Tuesday April 18, 0739

አብርሀ ደስታ ነገ ፍ/ቤት ይቀርባል። ኣጋርነትዎን ኣራዳ ፍርድ ቤት በመሄድ ያሳዩ!

Abrha Desta (Poster by Netsanet Yohans -FB)

 

የማሰብ፣ የመጻፍና የመናገር መብቱን በመጠቀም የብዙ መቶ ሺዎችን ፍቅርና ክብር ያገኘው ወጣቱ ፖለቲከኛና መምህር ኣብርሃ ደስታ በነገው ዕለት 8 ሰዓት ላይ በኣራዳ ፍርድ ቤት ይቀርባል። የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኅላፊ የሆነው አብርሀ ደስታ  ከጁላይ 8 ቀን 2014 ጀምሮ ከኣንድ ወር በላይ በእስር መሆኑ ከመገለጹ ውጭ ማንም የቤተሰብ ኣባልም ሆነ ወዳጆቹ እንዲጎበኙት ኣልተደረገም።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች (ፌስ ቡክና – ትዊተር) ይህን ወጣት ፖለቲከኛ የናፈቁ ሁሉ በነገው ዕለት ኣዲስ ኣበባ ኣራዳ ፍርድ ቤት በመሄድ ኣጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ እየተላለፈ መሆኑን በዚሁ ኣጋጣሚ እንገልጻለን።

ወጣቱ ፖለቲከኛና የዩንቨርስቲ መምህር ኣብርሃ ደስታ ጁላይ 8 ቀን መቀሌ ውስጥ በፖሊሶች እየተደበደበ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ በማዕካላዊ ዕስር ቤት ተጨማሪ ድብደባ ሳይፈጸምበት እንዳልቀር የትግል አጋሮቹ ጥርጣሬያቸውን አሰምተው እንደነበር ኣይዘነጋም።

Filed in: Amharic