ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቡና እና የጊዮርጊስን የደርቢ ጨዋታ ለመታደም አዲስ አበባ ስታድየም ቢገኝም ፌደራል ፖሊስ እንዳይገባ ከልክሎታል።

“ ስታዲየም የሄድነው ለምርጫ ቅስቀሳ አይደለም!!!” 

  እስክንድር ነጋ

•ተረኝነቱ እዚህ ተደርሷል!

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቡና እና የጊዮርጊስን የደርቢ ጨዋታ ለመታደም አዲስ አበባ ስታድየም ቢገኝም ፌደራል ፖሊስ እንዳይገባ ከልክሎታል።
ዘጋቢ ዮናስ አበራ
—-
ዛሬ በተከናወነው የጊዮርጊስና የቡና ጨዋታ ላይ ለመገኘት ወደ ስታዲየም ያቀኑት የባልደረስ ስዎች እንዳይገቡ ተከልክለዋል በተባለው ጉዳይ ላይ እስክንድር ነጋን ከደቂቃዎች በፊት አነጋግሬው ነበር ።እስክንድር በወከባና በማስገደድ እስታዲየም እንዳይገቡ መደረጉን ገለፆልኛል::
 ወደ ስፖርት እና ከፖለቲካ የፀዳ ወደሚባለው ቦታ ማቅናቱን ለምን ፈለጋችሁት?  ለሚለው ጥያቄዬ እስክንድር ሲመልስ ” እኛ እዚያ የተገኘነው የጊዮርጊስና የቡና ደጋፊዎች ከግጭትና ከመራራቅ ወጥተው ወደ እንድነት መንፈስ እንዲገቡ መልእክት ለማስተላለፍ ነበር:: የቡናና የጊዮርጊስ ደጋፊዎች አንድነት ለአዲሰአበቤዊያን አንድነት አስተዋፆ አለው” ብሏል::  ከዚህ የዘለለ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ በእርግጥ አልነበራችሁም ወይ?” ስልም ጠይቄው ነበር:: ሲመልስም ” አልነበረንም:: እኛ ወደዚያ የሄድነው ለምርጫ ቅስቀሳ አይደለም” በማለት መልሶልኛል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.