>

ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው! (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው!

ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ

•በተደጋጋሚ ስጋታችንን እንደገለጥነው የትግራይ ነፃ አውጪ ፓርቲ (ትህነግ) ባስቀመጠችው እቅድ መሰረት እየሔደች ነው። 

 

 1. የተፈፀሙ እቅዶች

፪: – በትህነግ ፓሊት ቢሮ ምርጫ እንደሚካሄድ መወሰን…ወሰነ!
፩:- በትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ እንዲካሄድ መወሰን…ወሰነ!
፫:- መቶ ፐርሰንት በትህነግ ካድሬዎች በተሞላው “የትግራይ ክልል ምክር ቤት(ፓርላማ)” ምርጫው እንዲካሄድ መወሰን…ወሰነ!
፬:- ከኦሮሞ ዘውጌ አክራሪ ብሔርተኞችና ተገንጣይ ድርጅቶች ድጋፍ ያሰባስባል…እያሰባሰበ ነው።

2. ቀጣይ ተግባራት፣

፭:- ለምርጫ ቦርድ ምርጫውን እንዲያስፈጽም ደብዳቤ መላክና በተጓዳኝ የትግራይ ክልል ምርጫ አስፈፃሚ ማደራጀት
፮:- የፌዴራል መንግስት ምርጫ ማካሄድ አትችሉም በማለት እርምጃዎች መውሰድ ሲጀምር ህውሓት የትግራይ ክልል ምክር ቤትን በአስቸኳይ ጠርቶ በህገ-መንግስቱ መሰረት የራስን እድል በራስ መወሰን( መገንጠል) በሙሉ ድምፅ ይወስናል።  ትህነግ የሚንቀሳቀሰው በሕገ-መንግስቱ መሰረት በመሆኑ የትኛውም የአገሪቱ ምድራዊ ህግ አይገታውም።
፯:- ፌዴራል መንግስቱ ትህነግ ምንም አያመጣም ብሎ ችላ ካለው ፤ ትህነግ የክልልና የፌዴራል 38 ወንበር ፓርላማ አባላት ምርጫ ያካሂዳል። ምን አልባትም ውጥረቱን ለማባባስ ከፊሉን የፌዴራል ፓርላማ አባላት አዳዲስ ሰዎችን ይመርጣል።

 3:- መፍትሔ

አንድ:– የመጣው አደጋ ወቅታዊ እና ተጨባጭ መሆኑን መገንዘብ
ሁለት:- የመጣው ወቅታዊና ተጨባጭ አደጋ በህገ-መንግስቱ መሰረት ይሂድ ከተባለ አገር የመበተን አቅም እንዳለው መገንዘብ። ስለዚህ ኢ-ሕገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ሄዶ መፍትሔ መፈለግ።
ሶስተኛ :- የመጀመሪያውና የቅድሚያ ቅድሚያ መፍትሔው ሕገ-መንግስቱን ማገድ ነው። ይህ ለጊዜው የማይቻልና ጊዜ የሚወስድ ከሆነ ህውሓት እና ኦነግን በፓርላማ በሽብርተኛ ድርጅትነት መፈረጅ።
Filed in: Amharic