>

ሲኖትራኩ ሽመልስ አብዲሳ! (እንግዳ ታደሰ)

 ሲኖትራኩ ሽመልስ አብዲሳ!

እንግዳ ታደሰ


ሲኖ’ትራክ መጣ ደንፍቶ እያገሳ
ኦሮሙማን አንጋሽ ሽመልስ አብዲሳ ።
ያዝ በለው !
“እስመ ሸዋ ሀገረ መንግሥት ይእቲ”- “ሸዋ የመንግስት አገር ናት”(conti Rossini, Historia Regis Sarsa Dengel,44።
አውሮፕላን መጣ እየገሰገሰ ! በዘፈን አንደኛ ጥላሁን ገሰሰ እያልን ያደገን የአዱ ገነት ልጆች ! ከአራዳነት ወደ ወረዳነት መውረዳችንን ሲኖ’ትራክ መጣ ደንፍቶ እያገሳ ኦሮሙማን አንጋሽ ሽመልስ አብዲሳ እያልን ልንዘፍን ምንም አልቀረን ።
ተበልጠናል ! ከአራዳነት ወደ ወረዳነት ዝቅ ብለናል ። ኮለኔል መንግስቱ እንዳሉት ተንቀናል ፥ ተዋርደናልዲሲ ብንገኝም ሿሿ ተሰርተናል እስክንድር ከአገር አይበልጥም ተብለን በኢሳት ተሰብከናል። ተሰብከንም አልቀረ የቄሮ ደጋፊ ፎሌ’ ሆነን አብይን እንደግፍ በሚል ደስታ ከረሜላ ተሸውደን ኦሮሙማን አንግሰናል።
ይህ ደረተ ሰፊ ! ተክለ ሰውነቱ የድሮ ክብርዘበኞችን የመሰለው ሽመልስ አብዲሳ!ከሰውነቱ በላይ የበለጠ እንዲገዝፍ የረዱት የቤተ መንግስቱ አጫዋች ጃንደረባዎች ደግሞ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ናቸው። ለዚህም ነው ሲኖትራኩ ሽመልስ፣ እስከምንችለው እኛ ኦሮሞዎች ከበላይ ሆነን እንገዛለን ካልቻልን ደግሞ የኛን ታዛዦች እናስቀምጣለን ያለው በገሃድ ። አሉት!የአማራ ዲጄዎች ! አሉት የሽመልስን ደረት ለሜዳልያ መደርደርያ የሚያሳምሩ የአማራ ተላላኪ ተክለ ሰውነት ገንቢዎች ! አሉት ለሰፋው ደረቱ ሜድልያ ደርዳሪ ብአዴኖች !
ትንሽ ቀልድ ብጤ ያስፈልጋል! እያረሩ ከመሞት ፈገግ እያሉ ከአራዳነት ወደ ወረዳነት ዝቅ ያሉትን የዛሬ” የዲሲ ልጆች ትላንት የአዲስ አበባ አራዶች ከሾርት ሚሞሪ ለማላቀቅ ብንቀልድ ምን ይለናል?  ቀልዱ እነሆ !!
ድሮ ድሮ በአብዮት አደባባይ ስታልፉ ! ከተሰቀሉት ሶስቱ አብዮተኞች ፎቶ ውስጥ መቸም ሌኒን የተባለውን ሰው ሳታስታውሱት አትቀሩም። የድሮ አራዳዎች የዛሬ ወረዳዎች የአዲስ አበባ ልጆች። ሌኒን መዳልያ ደረቱ ላይ ለመደቅደቅ አማረውና! እንደ ሽመልስ አብዲሳ ሰፊ ደረት በማጣቱ! “Leonid IIyich is in surgery.” ድጋሚ ልቡን ኦፕራሲዮን ያደረገ የመሰለው ካድሬ His heart again? ይላል? No,chest expansion surgery, to make room for one more Gold star medal.
የደረት ስፋት ፈልጎ ነው ሌኒን ለመዳልያዎቹ ። የኛ kingmaker አንጋሾች የዲሲ አዝማቾች ደግሞ ለአንድ እስረኛ ሰው ብለን የኢትዮጵያን አንድነት አናጋልጥም ይሉናል ተደጋፊ ተቃዋሚዎች ። በሰፊው የሽመልስ አብዲሳ ደረት ላይ መዳልያ እየሰካህለት ከአያት ቅድም አያት ርስትህ ላይ እየነቀለህ እንደሆነ ያላወቅህ መፍዙዝ ሁላ የአብይን መንግስት ለመደገፍ ነው እያልህና እየተመምህ ሰልፍ ውጣ !! የቴፑን ድምጥ ሰማህ? ደሞ’ የሽመልስ ድምጥ አይደለም ብለኽ ሸምጥጥ! ሰባተኛው ንጉስ አልሰሙም ብለኽ ራስህን አሞኝ ።
በየሱስ ስም ! እሳቸው አልሰሙም።
በስቴመጨረሻ ! የጥንቱ አራዳ የአሁኑ ወረዳ ! ይህን መጽሃፍ ገዝትህ አንብብ ! የንጉስ ዳዊት ከተማ የዛሬው አዲስ አበባ የጥንት ስሟ በራራ ናት ይልሃል በ100 % መረጃ ። ፊንፊኔማ ኬኛ ‘ ነው ኬንያም ኬኛ’ ነው በራራስ ? ታሪክ አንብብ።
Filed in: Amharic