>
5:29 pm - Monday October 10, 0253

ቀላማጁ ጠቅላይ ሚኒስትርና የማይጠገቡ ቅጥፈቶቹ! (አሳፍ ሀይሉ)

ቀላማጁ ጠቅላይ ሚኒስትርና የማይጠገቡ ቅጥፈቶቹ!

አሳፍ ሀይሉ

፠ የኦሮሞ ቄሮዎች መጤ ያሏቸውን ሌሎች ብሔሮች በጅምላ ከጨፈጨፉ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፦ ሬሳዎችን ስንቆጥር ያገኘነው መረጃ አብዛኞቹ ሟቾች ኦሮሞዎች መሆናቸውን ነው።
፠ ጠቅላዩ ሥልጣን ላይ ሲወጣ፦ ትግራይ የኢትዮጵያ ሞተር ናት!
፠ ከሥልጣን ማግሥት፦ ትግራይ ላይ ሕዝቡ ነው የተዋጋን፣ ቄስ ሳይቀር፣ የኢትዮጵያ አረሞች ናቸው፣ ካንሰሮች!
፠ የሰሜኑ ጦርነት ሲጀመር በፓርላማ፦ እኛ የሚሊሻ ጦርነት አንዋጋም፣ እናሸንፋቸዋለን እመኑኝ!
፠ ትናንት ባህርዳር ላይ፦ የመጣብንን ጠላት በመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት ተዋግተን ማሸነፍ አንችልም፣ ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሚሊሻ አሰባስበን መዋጋት አለብን!
፠ የሰሜኑ ጦርነት ሪፖርት ለፓርላማ፦ ዱቄት አድርገናቸዋል፣ አየር ላይ የተበተነ ዱቄት፣ ከእንግዲህ ተሰብስቦ ለምንም ሊሆን አይችልም፣ ከእኛ የውጊያ ጥበብ ዓለም አዲስ ትምህርት መውሰድ አለበት!
፠ ከሽንፈት ማግሥት፦ መልስም ጠያቂም የለም! ፍጥጥ!
፠ ከሽንፈት ማግሥት፦ ዕድሜው ለውትድርና የደረሰ ሁሉ መከላከያን መቀላቀል አለበት፣ ጦርነት ነው፣ ሰው ያልቅብናል፣ ሰው ካልተካን ያልቃል፣ ጦሩን ተቀላቀሉ፣ ክብር ነው፣ እና ሀገርን ከወራሪው ጠላት አድኑ!
፠ በባህርዳር በእርሻ መካከል ቆሞ፦ ተነስ፣ ታጠቅ፣ ዝመት ለዚች ሀገር አይጠቅማትም!
፠ አሜሪካ ሄዶ፦ መጀመሪያ ወደ ሥልጣን እንደወጣሁ ያደረኩት ነገር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ከእስር ማስፈታት ነበር!
፠ እውነታው በአቻምየለህ ሲጋለጥ፦ ጄነራል አሳምነው የተፈታው ጠቅላዩ ለሥልጣነ መንበር ከመብቃቱ በፊት ነው!
፠ በወያኔ እጅ ስለገቡት ሚሣኤሎች፦ እነሱ ያላወቁት ነገር የሪሞት ራዳር ሲስተሙ አውቶ-ሎክ እንዳለው ነው፣ እኛ ከዚህ ሆነን ሚሣኤሎቹን ቆልፈንባቸዋል፣ የታቀፉት ቀፎውን ነው፣ ቀፎውን ይዘው ነው የሚፎክሩት!
፠ ወያኔዎቹ ሚሣኤሎቹን በተመረጡ ዒላማዎች ላይ (ጎንደር፣ ባህርዳር፣ አስመራ ኤርፖርቶች ላዬ) ካስወነጨፉ በኋላ፦ የተወሰነች እጃቸው ላይ የተራረፈቻቸውን ሮኬት ተኩሰዋል፣ ሮኬቶቹ አየር ላይ ነው የፈነዱት፣ ዛፍ እንኳን አላገኙም!
፠ ከመቀሌ የውርደት ሽንፈት በፊት፦ ትግራይ በቁጥጥራችን ሥር ነች፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር እየሠራን ነው፣ የተራረፈውን ጁንታ ፖሊስ ከየቤቱ እንዲለቅመው አዘናል፣ ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም!
፠ ጦሩ መቀሌን በውርደት ጥሎ ከፈረጠጠ በኋላ ለፓርላማ፦ ከመቀሌ የወጣነው የእርሻ ወራት ስለገባ የትግራይ ገበሬ እርሻውን እንዲያርስ ብለን ነው፣ ለሕዝቡ የፅሞና ጊዜ ለመስጠት ነው፣ እንጂ ያሸነፈን ኃይል የለም! እነሱም ያውቁታል፣ ከፈለግን ተመልሰን ዛሬውኑ መቀሌን መልሰን መቆጣጠር የሚያስችል ወታደራዊ ብቃቱ አለን!
፠ ስለ ድሮኗ ሲናገር፦ እኛ ድሮን እንዳስገባን ጁንታው አያውቅም፣ የጁንታው መሪዎች ልጆቻቸውን እየጎተቱ ሲፈረጥጡ፣ እኛ ከሲቹዌሽን ሩም ሆነን እንደ ቴሌቪዥን እያየናቸው ነበር፣ ያልተኮስነው ለህፃናቱ ነፍስ ብለን ነው!፠ ድጋሚ ድሮኗ ለምን ጥቅም እየሰጠች እንዳልሆነ ሲጠየቅ፦ ድሮን እኮ የሰው ልጅ ጭንቅላት የፈጠረው ነገር ነው እንጂ፣ የሰውን ልጅ የሚተካ ነገር አይደለም፣ የእኛ ድል በድሮን ላይ የተመሠረተ አይደለም፣ ከፈለግን ግን ድሮኑንም፣ አውሮፕላኑንም፣ ሚሳኤሉንም፣ በእጃችን ላይ ያለውን ሁሉ እንጠቀማለን፣ አሁን መናገር አያስፈልግም፣ ውጤቱን በቅርቡ እናየዋለን!
፠ ጠቅላዩ ለጊነስ የዓለም ሪከርድ መዝጋቢ አካል፦ በአንድ ቀን 3 ቢሊየን ችግኞችን አስተክዬአለሁና አዲስ የዓለም ሪከርድ ተብሎ ይመዝገብልኝ!
፠ የጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ አስተዳዳሪ መግለጫ፦ የኢትዮጵያው መሪ የተናገሩት ክብረወሰን በትክክል ስለመፈፀሙ ማረጋገጥ ስላልቻልን በድንቃድንቅ መዝገባችን አልመዘገብነውም!
፠ በሥልጣን ሞቅታ ላይ ሲናገር፦ ኢትዮጵያን በቅርቡ ከዓለም ሁለት ኃያላን ሀገሮች አንዷ እናደርጋታለን! ዝም ብላችሁ ብቻ የሚሆነውን ጠብቁ!
፠ ብዙም ሳይቆይ፦ አሁን ባለን የገንዘብ አቅም መንግሥት ደመወዝ እንኳ መክፈል የሚቸገርበት ሁኔታ ውስጥ ነን፣ ለዚህ ነው የዓለማቀፍ አበዳሪዎችን ደጅ ጠንተንም፣ ያሉንን መሠረተ ልማቶች ለውጭ ባለሀብቶች ሸጠንም ህልውናችንን ለማስጠበቅ ለማዋል የምንገደደው!
፠ በፓርላማ ላይ፦ አይኤምኤፍ እና ዎርልድ ባንክ እናት ማለት ናቸው፣ የእናት መቀነት፣ የጠየቅናቸውን የሚሰጡን፣ የችግራችን ደራሾች!
፠ ጥቂት ቆይቶ፦ የሚሰጡን ሽርፍራፊ ሣንቲም ይቀራል እንጂ፣ እኔ በህይወት እያለሁ በእነ አይኤምኤፍ እጃችን እንዲጠመዘዝ አልፈቅድም፣ ሁሉ ነገር ይቀራል እንጂ ብር ወርውረው በኛ ጉዳይ ይሄን አድርግ፣ ያንን አታድርግ ሊሉን አይችሉም!
፠ ስለወያኔ ወታደራዊ አዛዦች እያናናቁ በፓርላማ፦ እኔ የማረጋግጥላችሁ ነገር 100 ፐርሰንት የጁንታው አዛዦች ወታደራዊ ዕውቀት የላቸውም፣ ወታደራዊ ትምህርት አልተማሩም፣ ስለወታደራዊ ሳይንስ ይቺን ታክል የሚያውቁት ነገር የለም፣ እመኑኝ መቶ በመቶ መሀይሞች ናቸው!
፠ ከሽንፈት ማግሥት፦ እኛኮ 80 ፐርሰንቱ የጁንታው አዛዦች ጥለውት ሄደው ባዶውን የቀረውን መከላከያ እኮ ነው፣ ወር ባልሞላ ጊዜ እንደ አዲስ አደራጅተን ያዘመትነው፣ የሀገሪቱን ጦርሀይል ሎጂስቲክስ 2/3ኛውን የያዘውን የሰሜን ዕዝ በቁጥጥራቸው ካዋሉ ሰዎች ጋር እኮ ነው ያለበቂ ዝግጅት ወደህልውና ጦርነት የገባነው፣ ይሄ መታወቅ አለበት፣ ማድረግ የሚቻለው ሁሉ ባለውና በተቻለው አቅም እየተደረገ ነው!
፠ ስለ አሜሪካ በኖቤሉ ማግሥት፦ አሜሪካ ቀኝ እጃችን ነች!
፠ ከድል ቁርሱ፣ አነፍናፊው፣ ወዘተ ውርደት በኋላ አሜሪካ ከወያኔ ጋር ላደራድርህ ስትለው፦ በአሜሪካ የሚጠመዘዝ መንግስት ድሮ ቀርቷል፣ በአሜሪካ ትዕዛዝ የሚሾር አካል የለም አሁን፣ በሉዓላዊነታችን ከመጣ ማንም ወዳጃችን ሊሆን አይችልም፣ በባዕዳን የሚደገፈውን ጁንታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንቀብረዋለን!
፠ የቀላምዴ ትክክለኛ ስም፦ አብዮት ካሣሁን በላይነህ
፠ የቀላምዴ የመታወቂያ ስም፦ አብይ አህመድ አሊ!
እኔ የምለው አብዮት (አብይ)  .. ድንገት የነፍስ ኦዲተር ቢመጣበትስ????
ስንት ወታደር አስጨረስክ? = ______
ስንት ሚሊሻ? = ______
ስንት ልዩ ኃይል? = _______
ስንት ወዶ ዘማች? = ______
ስንት ሠላማዊ ሰው? = ______
ስንት ኤርትራውያንን? = ______
ስንት የትግራይ ልጆችንስ ገደልክ? = _______
አጠቃላይ የስንት ሰው ነፍስ አለብህ? = ______
(ወይም ኢዜማ ጠየቀ እንደተባለው) ጦርነቱን ለመጨረስ የስንት ሰው ነፍስ ይቀርሃል? = _______
እንቅልፍ ይወስደዋል ግን? አባባሌ የነፍስ ኦዲተር ባይመጣበት ራሱ… ይሄን ሁሉ ወታደር፣ ይሄን ሁሉ ሕዝብ፣ ይሄን ሁሉ ዜጋ፣ ይሄን ሁሉ የጎረቤት ሀገር ዜጋ ሁሉ አስጨፍጭፎ…. እውነት በሠላም ይተኛል ግን?
ይደንቀኛል በጣም። እጅግ በጣም።
Filed in: Amharic