>

ኢትዮጵያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ስናይፐር የምትተኩሰው ታጋዳላይ ጋኤል ስሚዝ  ማን ነች...???  ዳንኤል ታደሰ

ኢትዮጵያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ስናይፐር የምትተኩሰው ታጋዳላይ ጋኤል ስሚዝ  ማን ነች…??? 
ዳንኤል ታደሰ

“ከፍተኛ ስልጣን ላይ ከነበሩት የትህነግ ታጋዮች አንዱ የነበረው እና በህይወት የሌለው የማነ ጀማይካ ለሸገሯ መዓዛ በጨዋታ ፕሮግራም ላይ በደርግ ጊዜ ስለነበረው የትጥቅ ትግል ወቅት አብራቸው ስለነበረች አንዲት አሜሪካዊት ያጫወታት ትዝ ይለኛል ።የማነ እንደዚህ ይላልበ1970ዎቹ በውጭ ግንኙነት ስራ ሱዳን በነበርኩበት ወቅት አንዲት ነጭ ‘ጋዜጠኛ’ በሱዳን በሚገኙ ስደተኞች ላይ ዶክዩመንታሪ ለመስራት መጣሁ የምትል  አሜሪካዊት ተዋወኩ ይላል። ጋኤል ስሚዝ ትባላለች ለመግባባት ብዙም አልፈጀብንም ጓደኛ ሆንን ብዙዎቹን የትግል ጓዶቼን(መለስ ዜናዊን ጨምሮ) በሂደት አስተዋወኳት ይላል።ይሄ በ70ዎቹ ሱዳን ላይ የተመሰረተ ጓደኝነት የማነ ጀማይካን ጋኤል ስትሞሸር ሚዜዋ እስኪሆን አድርሶታል።ጋኤልን ደግሞ ከጫካ እስከ አራት ኪሎ ያልተለየች ሁነኛ የወያኔዎች ወዳጅ……
ዴሞክራቱ ባራክ ሁሴን ኦባማ ሲመረጥ  ጋኤል ስሚዝን ዩኤስኤይድ(USAID) አስተዳዳሪ እንድትሆን ሾማት።በአሁኑ የባይደን አስተዳደር ደግሞ በውጭጉዳይ ውስጥ ሁነኛ የብሊንከን አማካሪ ነች። በአሁኑ ሰዓት በሰፊው የሚታመነው አሜሪካ በመርህ ላይ የተመሰረተ አቋም ከመያዝ ይልቅ ይችን ሴት  በመሰሉ ሰዎች በያዙት አስተሳሰብ የተቃኘ አቋም ታራምዳለች የሚነው ነው። ኬንያ ላይ ከብሊንከን ጋር ሆና ኢትዮጵያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ስናይፐር የምትተኩሰው ጋኤል ሽበትዋ እንኳን እንዳትዋሽ አላገዳትም።
Filed in: Amharic