>

የአምሀራ የህልውና ትግል ድምፅ ይሰማ! (ዘምሳሌ)

የአምሀራ የህልውና ትግል ድምፅ ይሰማ!

 

ዘምሳሌ


አዎ አምሀራ ነኝ
በሰላም የምዳኝ
ፍቅር የሚጥለኝ
ደግነት ሚገደኝ
ጠላት የበዛብኝ
ሰላሜን ያጣሁኝ
ባጎረስኩ ፈንታ
እጄን የነከሱኝ

በኢትዮጵያ መሬት
ሀገር ባቀናሁት
ብትዘሉ ከሰማይ
ብትወርዱ ከመሬት
ያለኝ ሙሉ እምነት
መችም ማይለውጡት
ታሪኬን አይፍቁት
በሀሰት ቢፅፉት

አዎን አምሀራ ነኝ
ተስፋ ከቶ የማልቆርጥ
ፍፁም ማልናወጥ
ድንበሬን የማልሰጥ
ህዝቤን የማከብር
ነፃነት የምመርጥ
ጠላት ምደፈጥጥ

አምሀራ ነኝ እኔ
የለም ቢሉ አምሀራ
በከፋፋይ ሴራ
ህዝቤ ደም ሲዘራ
ስቃዩ ያልቆመ
ዘንቦ ማያባራ
በየሁሉ ጎራ
ህዝቤ የሚያነባ
በስቃይ መከራ

አዎ አምሀራ ነኝ
በዝምታዬ ልክ
በታገስኩት መጠን
ህዝቤን ያረዱብኝ
ያጣሁኝ መሬቴን
አለም ተገልብጦ
የተጋገዘብኝ
ህፃናት አዛውንት
የተደፈረብኝ

አምሀራ ነኝ እኔ
ለሀገሬ በቆምኩ
የተወጋ ጎኔ
እረሀብ የጣለኝ
ያለቀ ወገኔ
ዘሬ የመከነ
በክትባት ጭኔ
ቢገሉኝ የማልሞት
የምኖር በቅኔ
ተፈጥሮተዬ ሚስጥር
የታደልኩ ድንቅ ወኔ

አዎ አምሀራ ነኝ
መሬት የተዘረፍኩ
በግፍ የተገደልኩ
በሀገሬ የተጋዝኩ
ተራራ የተባልኩ
በፊልም ትወናም
እንደሞኝ የተሾፍኩ
ስሜን ሲያጎድፉብኝ
ታግሼ የተቀመጥኩ

አዎ አምሀራ ነን
በቁም የተከዳን
ነፍጥን ይዘን የኖርን
መልካም ባህል ያለን
ያከበርን እንግዳን
ታሪክ ያከበረን
ለዘመናት የኖርን
ሀገር ህዝብ ባቀናን
መሰረትን በጣልን
የጥላቻ ሀውልት
የተገነባልን
ገደል የተጨመርን
ኧረ ስንቱነ ገልፀን
ግፍ ያደረሱብን

አዎ አምሀራ ነኝ
ባገሬ የተገፋሁ
ስም የለጠፉልኝ
ሀገርን ባዳንኩኝ
አላስነካም ባልኩኝ
ወራሪ እያሉ
ስሜን ያጠፉብኝ
ላገሬ በታመንኩ
ተባብረው የከዱኝ

አዎን አምሀራ ነኝ
ውብ ደምግባት ያለኝ
በአክራሪ ዘረኞች
ሀብት የወደመብኝ
እርሻ ከብት ሊጤ
የተዘረፈብኝ
በሰው የማልቀና
በረከት የታደልኩ
ፈጣሪ ማመሰግን
ሁሌ እየተንበረከኩ
ለሀገር የምማፀን
ስታገል የምጥል
ጠላትን የምምር
ገዳዮች የምገል
ጥዬ የምፎክር
አዎ አምሀራ ነኝ
አዎ አምሀራ ነኝ!

Filed in: Amharic