>

"ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ አጣዬ የደረሰው በብአዴን መንገድ መሪነት፣ መረጃ አቀባይነትና አስተኳሽነት ነው...!!!" (አቻምየለህ ታምሩ)

“ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ አጣዬ የደረሰው በብአዴን መንገድ መሪነት፣ መረጃ አቀባይነትና አስተኳሽነት ነው…!!!”
አቻምየለህ ታምሩ

ከዚህ በፊት ባተምናቸው ጽሑፎች የኅልውና ዘመቻው ብአዴን የሚባለው ጉድ በማይደርስበት አኳኋን እስካልተመራ ድረስ ከፋሽስት ወያኔ ጋር የሚደረገው የኅልውና ተጋድሎ ከባድ መስዕዋትነት እንደሚያስከፍለን በተደጋጋሚ አሳስበን ነበር። ይህንን ያልንበት ዋና ምክንያት የብአዴን መዋቅር ፋሽስት ወያኔ የዘረጋው መዋቅር በመሆኑ ብቻ ሳይሆን የፋሽስት ወያኔ ታማኝ  የውስጥ የመረጃ ምንጮች እና አስተኳሾቹ የአማራ ርግማኖች የሆኑት ነውረኞቹ ብአዴኖች በመሆናቸው ነው። ፋሽስት ወያኔን ከኮረም እስከ አጣዬ የደረሰው እዚህ ግባ የሚባል ጦርነት አድርጎ በድል አድራጊነት አይደለም። ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ አጣዬ የደረሰው በብአዴን መንገድ መሪነት፣ መረጃ አቀባይነትና አስተኳሽነት ነው።
ከታች የሰፈረው ሰዒድ ያጋራን የከለላ ወረዳ አመራሮች የባንዳነት ተግባር የብአዴንን ማምነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ብአዴን ሁሉ እንደ ከለላ ወረዳ የብአዴን አመራሮች ነው። ፋሽስት ወያኔን ደብረ ታቦር ድረስ እየመራ የወሰዳቸው የብአዴኑ ሹም፤ እንደ ከለላ ወረዳ አመራሮች ሁሉ የብአዴን ሹም የነበረው የምዕራብ ደንብያው የደኅንነት ኃላፊ ነው።
ባጭሩ ፋሽስት ወያኔ ከኮረም እስከ አጣዬ  ድረስ ያደረገው የግፍ ወረራም በእንደ ከለላ ወረዳ አመራሮች አይነት የብአዴን ሰዎች የተመራና ከነሱ በሚገኝ ጥብቅ ወታደራዊ መረጃ የታገዘ ነበር። ብአዴን ባለበት ሁሉ የፋሽስት ወያኔ መዋቅር፣ የፋሽስት ወያኔ ዓላማ፣ የፋሽስት ወያኔ ስር አለ። ብአዴን እንደ ድርጅት የተፈጠረው አማራን ለመታገል ነው። እስካሁን ድረስ በተካሄደው ተጋድሎ አማራን የከዳ፣ ለፋሽስት ወያኔ የሚያስተኩስና መረጃ የሚሰጠ ብአዴን እንጂ አማራን የከዳ ፋኖ፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና መከላከያ ሠራዊት አልታየም።
በመሆኑም የፋሽስት ወያኔ አስተኳሽ የሆኑት ብአዴኖች ከጥቅም ውጭ ሆነው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎው በሕዝብ ልጆች ፊታውራሪነት እስካልተካሄደ ድረስ በሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት በብአዴን አዝማችነት የሚካሄደው ጸረ ፋሽስት ወያኔ ተጋድሎ ከጠላት ጋር ተሰልፎ ጠላትን አሸንፋለሁ ብሎ እንደማሰብ አይነት ቂልነት መሆኑ መታወቅ አለበት። ባጭሩ የኅልውና ዘመቻው ውጤት ከእስከንደዛሬው የተለየ እንዲሆን ከተፈለገ የብአዴን የሆነው ነገር ሁሉ ታግዶ ጸረ ፋሽስት ወያኔ የኅልውና ተጋድሎው ብአዴን በማይረርስበት ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በመከላከያው፣ በልዩ ኃይሉ፣ በሚሊሻውና በፋኖው የተቀናጀና የተናበበ ስምሪት መካሄድ ይኖርበታል።
እነዚህ እጅ ከፈንጅ የተያዙት የከለላ ወረዳ የብአዴን አመራሮች በሙሉ ያለ ምሕረት እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። እነዚህን ባንዳዎች ለመከላከል የሚሞክር ብአዴን ቢኖር እንደነሱ ያለ ባንዳ ስለሆነ ዋጋውን ማግኘት አለበት። ለባንዳ፣ ለከሀዲ፣ ለፋሽስት ወያኔ አስተኳሽና መረጃ አቀባይ ምህረት ሊኖር አይገባም።
የከለላ ወረዳ አመራሮች የክህደት ስራ !
አሸባሪውን ወራሪ ሃይል ለመመከት ከደገር እስከ ልጓማ ያሉ የከለላ ሚሊሻዎች ተሰባስበው ለሳምንት የዘለቀ ተጋድሎ ባደረጉበት ወቅት የከለላ ወረዳ አመራሮችና ባለሃብቶች የሰሩት ስራ እጅግ አስነዋሪ እጅግ አስፀያፊ ነበር ።
እነዚህ የህዝብ ጠላት የሆኑ ባንዳዎች የፀጥታ ሃይሉ ወደ ግንባር ማቅናቱን እንዳወቁ ቀጥታ የገቡት ወደ ዘረፋ ነበር ። ጥይትና ሌሎች በትግሉ አስፈላጊ የነበሩ ቁሳቁሶችን ሳይቀር የዘረፉት ሌባዎቹ አመራሮች ህዝባቸውን አደራጅተው ከፊት መምራት ሲጠበቅባቸው እነርሱ ግን የመረጡት ከሗላ ህዝባቸውን መምታት ነበረ ።
የወረዳ አመራሮቹ ከአንዳንድ ባለሀብቶች ጋር በመሰማራት ከተራ ሱቅ ዘረፋ እስከ መንግስት ተቋማት ድረስ ሙልጭ አድርገው በመዝረፍ ከከተማ ሲያሸሹ ነበር የከረሙት ። ወራሪው የትግራይ ሃይል ወደ ከለላ እንደሚገባ እርግጠኛም ስለነበሩ ለህወሃት አቀባበል ለማድረግ ዝግጅታቸውን ጨርሰው ነበር ። አዎ እነርሱ ይህን ክህደት በሀገራቸውና በህዝባቸው ላይ ፈፀሙ !! የሚመሩትን ህዝብ እንደ ተራ ዱርየ ዘረፉት ። የሚያስተዳድሩትን ተቋም ሙልጭ አድርገው ሰረቁት ። ከዚያም አልፎ ለመከላከያ ሃይሉ የተዘጋጁ በሶና ኮሾሮዎችን ሳይቀር ነበር ሙልጭ አድርገው የዘረፉት ። ጥይት አለቀብን አቀብሉን እያለ የሚማፀናቸውን ሚሊሻ ክደው የወረዳውን የጥይት ክምችት ለመሸጥ በጆንያዎች ቆጥረው እያዘጋጁ ነበር ።
ግና እነርሱ ያሳቡት ሳይሆን ቀርቶ አሸባሪው ሃይል ከለላን ሳይረግጥ ከልጓማ ተመለሰ ። የአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ ከለላ ሲገባ ግን ለነርሱ ጨለማው ነው የተደፋባቸው ። ፋኖና ልዩ ሃይሉ እነዚህን ሌባ ቀማኛና ህዝብን የካዱ አመራሮችን ከነዘረፉት ንብረት በቁጥጥር ስር አውሎ ” እኔን ያየ ይቀጣ ” እያስባለ አሸክሞ ከተማውን አዙሯቸዋል ። እስካሁን ከመቶ በላይ አመራርና ባለሀብት ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ቅጣታቸውን የሚጠብቁ ይሆናል ።
አሁንም ቢሆን መንግስት አመራሮች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ያድርግ ። ከሰሜን ወሎ ጀምሮ ያሉ የወረዳ አመራሮች የወረዳውን ትጥቅ ለተዋጊው ማህበረሰብ አናስረክብም በማለት እምቢ ካሉ በሗላ በሴራ ለወራሪው ሀይል ሲያስረክቡ እዚህ አድርሰዋል ።
የቀድሞ የህወሃት ካድሪዎችን በአመራርነት ያስቀጠለው መንግስት ህዝብንም ሀገርንም ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነውና ይታሰብበት !
Filed in: Amharic