አፋብን የት ነው ያለው?!

ከአዳባይ 

የአማራን የህልውና ትግል ጨፍልቆ ወደ ፓለቲካ ለማውረድና ከዋነኛ ጠላታችን ህወሃት ጋር በማበር ብዙ አማራውያን ህይወታቸውን የገበሩበትን ትግል የሃብት ማካበቻ ያደረጉት እነ ዘመነ ካሴ አስረስ ማረ ዳምጤ ምሬ ወዳጆና አበበ ፈንታው አፋብን የሚባል በተግባር መሬት ላይ እጅም እግርም የሌለው ንቅናቄ መሰረትን ካሉን ድፍን ሶስት ወር ሞላው።
የዚህ ንቅናቄ ዋና ስኬት በመርህ ላይ የተመሰረተውንና ለአማራም ለኢትዮጵያም ብሩህ ተስፋ ይዞ የመጣውን የፋኖ ተቋም አፋህድን ማፍረስ ትግሉን መጥለፍና ለህወሓት መሸጥ ሲሆን እነ አስረስ ከዘመዶቻቸው እነ ተመስገን ጥሩነህ በተሰጣቸው ስምሪት መሰረት የህልውና ትግሉን ወደ መንደር ስልጣን በማውረድ የግል ሃብት ማካበቻ በማድረግ ህዝቡን ተስፋ ለማስቆረጥ ጥረት ማድረግ ላይ መሰመራታቸው ነው ።አሁን ይችን ማስታወሻ በምፅፍበት ቅፅበት የጀኔራል ክፍያለው ደሴ ልጆች ጠላትን በክንዳቸው እየደቆሱ እነ ባንዳው ቆራጡ ለጠላት የሰጡትን ዲሽቃ ጭምር መልሰው የተረከቡበት ታላቅ ድል እያስመዘገቡ ቢሆንም ከጠላት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት አስረስ ማረ ዉጊያ ለማስቆምና ወንድሞቻችን በጠላት እንዲመቱ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ የሚሰማ አልተገኘም ።ጀግኖቹ ድል በድል ሆነዋል ።

አፋብን ከዋሽንግተንና ከኡጋንዳ ተፅፎ በሚሰጠው መግለጫ ይሁን ማላገጫ በሳምንት አንድ ጊዜ ፌስቡክ ላይ ከመለጠፍ የዘለለ የትግሉን ሁኔታ የሚተነትን የትግሉን መዳረሻ የሚያመላክት በእውቀት ላይ የተመሰረተ የፓለቲካና ዲፕሎማሲ ሥራ ለመስራት የሚያስችል አደረጃጀትና አቅም ያላቸው ሰዎችን ከኋላ ደብቆ የመጣ ፀረ አማራ ስብስብ ስለሆነ ለእውነት የተሰለፈው አማራ ሁሉ ገለል ሊያደርገው ይገባል ።አፋብን በቅንነት እየታገሉ ያሉ ፋኖዎችን በገንዘብና በቁሳቁስ እየደለለ የወያኔን የመገንጠል አጀንዳ ለማሳካት የታጋዬች ጥርነፋ ለማድረግ በአስረስ አማካይነት ከፍተኛ የገንዘብ ክፍያ እንሰጣለን የሚል ማባበያ እየነዛ ሲሆን ለዚህ ተግባር ማስፈፀሚያ በውጪ በጠረነፋቸው የሚዲያ አፈቀላጢዎቹ እና በድብቅ ባቋቋመው የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አማካይነት በአማራ ስም ከተደራጁ ማህበራት በነፍስ ወከፍ ከ5-10 ሺህ ዶላር እንዲያዋጡ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ።ዲያስፓራ ለእነ አስረስ የባህር ዳር ሰልጣንና ወንድምህን እርስ በእረስ ለማገዳደል የሚሰበስብ ገንዘብ መሆኑን አውቀህ ኪስህን ጠብቅ ።ነገ ከማዘን ከወዲሁ ለምን ብሎ መጠየቅ ከህሊና ተጠያቂነት ነፃ ያወጣልና !
በሌላ የማፍረስ ሴራ አፋብንን አናምንም ያሉትን በሃይል ለማስገባት የተደረገው ሙከራ ምንም ለውጥ ስላላመጣ በውስጥ የማስኮብለል ሥራና ምርጫ ላይ የሚሳተፈውን ሁሉ እርምጃ እንወስድበታለን የሚል የፋኖን የነፃነት ትግል የሚያጠለሽ መግለጫ እንዲወጣ በህወሓት የታዘዘው ሆን ተብሎ የተሰራ አማራን የመበታተን እቅድ አካል ነው።አፋብን በምሬ ወዳጆ በኩል ከህወሓት ሰዎች ጋር በመነጋገር የህወሃትን የወልቃይትና ራያ መሬት ለትህነግ አስረክቦ ከአብይ ጋር መደራደር የሚል አጀንዳ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን በአስረስ ማረ በኩል ደግሞ ብአዴንን ከባህር ዳር በማባረር እነ ዘመነን የባህር ዳር ሹማምንት አድርጎ ከአብይ ጋር መደራደርና ስልጣን መጋራት በሚል ስምምነት እየተተተገበረ ያለ ከህልውና ትግሉ በተቃራኒ የቆመ ፀረ አማራ ስብስብ ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው ።

መከታው ማሞና እነ ደሳለኝ ወደ አራት ኪሎ እንደሚገባ የተነገራቸው ቢሆንም የአፋብን እውነተኛ አላማ ግን የአማራን እርስቶች ለህወሓት ሰጥቶ አማራውን በተራዘመ የጦርነት አዙሪት ውስጥ ማቆየት ነው ።በዚህ ታሪክ ይቅር በማይለው ሴራ ውስጥ ገብታችሁ የአማራን የህልውና ትግል ለጠላቶቻችን ህወሃትና ኦህዴድ እየሸጠ ያለ ቡድንን በገንዘብ በሃሳብ በሚዲያና በሴራ የምትደግፉ ሁሉ ደጋግማችሁ እራሳችሁን ጠይቁ።ከህዝብና ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን አርቁ ??ይህ ወንድማዊ ምክሬ ነው።

ከዚህ በሻገር አሁንም የአማራ ህልውና ትግል የሚቋጨው አራት ኪሎ ላይ በሚደረግ ሥር ነቀል ለውጥ ብቻና ብቻ ነው የሚሉ ሚሊዮን የአማራ ታጋዬች በእውነት ላይ ቆመው ድል ለመቀዳጀት ሌት ተቀን እየሰሩ ነውና ምንም ያህል ጠላት ሊያጓትተው ቢሞክርም እወነት በቅርቡ ትገለጣለችና የሥር ነቀል ለውጥ ደጋፊ አማራውያን በያልንበት እየተሰባሰብን እንጠብቅ ??
ይሁዳም አምላኩን በ30 ዲናር ሸጦ ሳይጠቀምበት ታንቆ ሞቷልና ህዝብን በማስጨነቅ የዘረፋችሁ በውጪ ሃገር ሳይቀር ሃብት ያከማቻችሁ የቁስ ፋኖዎች ስለማትጠቀሙበት ህዝቡን መዝረፍ አቁሙ።የወንጌሉን ቃል ካላመናችሁ የባንዳውን ፀዳሉ ደሴን 20 ሚሊዮን የህዝብ ሃብት ማን እንደወረሰው እዛው ጠይቁት ??
ለዚህ ትግል መነሻ ምክንያት የሆንከውና ከክልሉ ውጪ ያለህ አማራ በሙሉ ድርጅትህን አፍርሶ እውቅናህን የነጠቀህን አፋብን የሚባል የጠላት ወኪል ምንም አይነት ድጋፍ ባለማድረግ ተቃውሞህን እንድትገልፅ ጥሪ ቀርቦልሃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.