ዘምሳሌ
ይድረስ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመከራ ለዳረገ
ጠቅላይ
ሰው አገኘን ብለን ተስፋ አርገን ነበር
መሪ መጣ ብለን ድጋፍ ወጥተን ነበር
እንዲህ ሳንከዳ ቅስም ሳይሰበር
ኢትዮጵያ እያልከን ደጋግመህ ስትጮህ
እውነት መስሎን ነበር ካድከን አዘናግተህ
በመደመር ስሌት ስንቶችን ቀንሰህ
ያመኑህን ሰዎች በሸፍጥ አስገድለህ
አንተ የታሪክ አረም የማህፀን መርገም
አምሳያ የሌለህ ቢፈለግ በአለም
ዘረኛው ምልከታህ ሰዎች ሲገደሉ
ኦሮሞን መርዘህ የምትል ዝም በሉ
ከሴጣንም አብይ የውሸት አለቃ
ቀዳማዩ እቡይ የኦነግ ጠበቃ
የአኖሌ ጠንሳሽ
የሀገር ታሪክ ደምሳሽ
ሀገር ስትደፈር ምትሸሽ ከግንባር
መምራትም የማትችል ያለህ በግርግር
ህዝብ ሲመሳቀል ትንፍሽም የማትል
ደናቁርት ምሁራን ባንተ አፍ ሲደለል
ለሆዱ ያደረ ሀገር ክብር ረስቶ
ፈዞ አብሮህ ያለ ጉያህ ተጎልቶ
አንተን ብሎ ጠቅላይ
ህዝብን በዘር አግላይ
በኦነግ ከለላ በሸኔ ከለላ
ትንፍሽም የማትል ህዝብ አንገት ሲቀላ
ሰው እያስጨረሰ ቡትቶ ቃላትህ
ሀገር እያመሰ የምትነዛው መርዝህ
መሬት አስረክበህ ሰላም ባገር ጠፍቶ
አምሀራ ሲገደል በዘር ተለይቶ
የተለቀለከው ሜካፕህ እስኪለቅ
በሟች የምትስቅ መላው ህዝብ ሲሳቀቅ
ያልበሰለ አዕምሮህ ዘረኛ አድርጎህ
በስሌት ቆምረህ ለጊዜው ቢመችህ
አንተ ዛፍ ስተክል ሰዎች ሲታረዱ
እርዳታ ተነፍገው ተዘግቶ መንገዱ
ለህዝብ መቆም ያልቻልክ
በስልጣንህ ያበድክ
ለዘረኞች ቆመህ አምሀራን ያስፈጀህ
ጦርን ሲያደራጁ መሳሪያ እየሰጥተህ
ገንዘብን አድለህ ባንክቤት ሲዘረፍ
ሽፋን እየሰጠህ በሚዲያ ደጃፍ
ሙታንን ደብቀህ በጅምላ መቃብር
ለገዳዮች ቆመህ ወንጀሉን ስትሰውር
በተልካሻ ስብከት ያለህ ቤተመንግሥት
በውሾችህ ጩኸት ባንተ ርኩስ ዳኝነት
በፍራቻ እየኖርክ ሴራ ስትፈበርክ
ቆሻሻ አመራርህ የበታች ስሜትህ
ዘረኛ አድርጎህ ግብረቢስ ጥላቻህ
በኢትዮጵያ እያፌዝክ
ከወያኔ አብረህ ሸኔን እያሳደክ
አምሀራን ስትፈርጅ
ተኩስ አቁም ስታውጅ
በብልፅግና ስም
ሀገር ምታከስም
ኦሮሞ ጠል እያልክ የምትነዛው ሽብር
በዘረኝነትህ ህዝብ ሀገር የሚያፍር
ለሀገር አትመጥንም ችሎታ የለህም
ዘረኛ ከፋፋይ የኢትዮጵያ መርገም
ጠቅላይ አትባልም ወንጀልን ሰርተሃል
ችሎታው የለህም ሁሉ ነቅቶብሃል
ላገር አትመጥንም ህዝብ ሀገር ጠልቶሃል
የማትለቅ ከሆነ አይቀር ይሰቅሉሃል
ጋዳፊን አትሆንም እመነኝ ዘረኛዉ ያንተ ቀን
ይብሳል
ለፍርድ የምትቀርብበት ቀናት ተቆጥረዋል