አንድ ለእናቱ ሺህ ለጠላቱ፦ እስክንድር ነጋ!
”የአማራ ልሂቅ የትገባ ለምን ትግሉን አያግዝም የፖርቲ ፖለቲከኞች የታሉ?… ለምን የአማራን ትግል አይቀላቀሉም?” እየተባለ ሰው በሚፈለግበት ግዜ በተለይ ዓማራዊ ልሂቅ የሆነ ሰው በባትሪ በሚፈለግበት ግዜ፣ በአብይ አመጣሽ ድንዛዜና ድንጋጤ ተውጦ ሕዝብ ግራ በተጋባበት ግዜ ዓይነጥላን ገፎ አደባባይ በተቃውሞ የወጣ፣ ትግልን መደገፍ ብቻ አይደለም የሕይወት መስዋዕትነት እንኳን ቢያስከፍል ነፍሴን እሰጣለሁ ብሎ ጫካ ወርዶ ታጣቂ ኃይል አደራጅቶ፣ በገጠር በከተማው ተዘዋውሮ ሕዝብ አንቅቶ፣ ለዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ድምፅ አሰምቶ፣ ሕፃን አዋቂውን አነቃቅቶ ከጎኑ አሰልፎ ወደፊት እየገሰገሰ ያለው እስክንድር ነጋ አስደናቂ ስብዕናና ፅናት የተላበሰ ሰው ነው። ዓማራዎች አስፈላጊያችሁ ነው ተጠቀሙበት።
ይህ ምትክ አልባ ዓማራዊ ሰው ከኦሮሙማው እስከ ብአዴናዊ ጎጠኛው፣ ከአማራ ብሔርተኛ ነኝ ባዩ እስከ ሰፈርተኛው፣ ከኢጎይስቱ እስከ የስልጣን ጥመኛው፣ ከባለሚዲያው እስከ ባለቴሌግራሙ፣ ከጎርፍ አመጣሽ ፖለቲከኛው እስከ አቅሙን አያውቄ ፌስቡከኛው ቢንጫጫ ባይንጫጫ ምንም ሳይመስለው፣ ባልሰማ ባላየ እየናቃቸው ወደ ኋላው ሳይመለከት ፊቱን ፊቱን እያያ ወደ ዒላማው ወደ ዓላማው፣ ወደ ነፃነት ጉዞው፣ ወደ አዲስ አበባው ወደ ሚኒልክ ቤተመንግስት እያነጣጠረ መዋቅሩን እያሰፋ መገስገሱን ቀጥሏል።
እኛም አለንለት ! የጀርባ አጥንት፣ ሞገስ ፣ደጀን ሆነን እናበረታዋለን፣ እንደግፈዋለን፣ አብረን የክብር ውጤቱ ተቋዳሽ እንሆናለን፣ እስክንድርን ልጃችንና መሪያችንን አሳልፈን አንሰጥም፣ እንጠብቀዋለን።
እኛ የዘመኑ ኢህአፖዎች፣ የዘመኑ ደርጎች፣ የዘመኑ መኢሶኖች፣ የዘመኑ ብአዴኖች ሆነን ከጠላት አኩል አንድ ለእናቱ በሆነው ልጃችን ላይ አንዘምትም፣ እኛ እንደ ኢህአፖ ጊዜ አወቅን ባይ ጥራዝነጠቅ ደናቁርቶች ሆነን ፋና ወጊ ታጋይና አታጋይ ዓማራዊ ልሂቅ ልጃችንን ቀርጥፈን አንበላም። እኛ ለተደረገልን በጎ ስራ ምስጋና አንነፍግም፣ ውለታቢስ አንሆንም፣ ታማኝነት አናጎድልም፣ ቃልኪዳን አንሰብርም፤ ማተብ አንበጥስም፤ ምክንያቱም እኛ ፌክ አማራዎች አይደለንም።
እኛ እስክንድራውያን ሚኒልካውያን አማሮች ነን። ጎንበስ ብለን እጅ የምንነሳ፣ እምዬ ብለን መሪን በስስት የምናይ፣ የእከሌ አሽከር ብለን መሪን ከፍ የምናደርግ፣ የመሪ ስኬት ስኬታችን አድርገን የምንወስድ፣ አክብረን የምንከበር ኩሩ አማራዎች ነን። እኛ ጥሩ መሪ ስላገኘን ጥሩ ተመሪዎች የሆንን እውነተኛ የአባቶቻችን ልጆች አማራዎች ነን። ከእስክንድር ጋር አብረን እንፀናለን!
@Amhara97262
አማራ ፋኖ