እስክንድር የስልጣን ጥም የማይታይበት እውነተኛ ታጋይ ነው
ዘላለም ይግዛው (ፕሮፌሰር)
ጭራቁ አብይ አህመድ በ2010ዓ፣ም. በወርሀ መጋቢት ወደ ስልጣን ማማው ሲወጣ በሚናገራቸው የማጭበርበሪያ ቃላት እና በወሬ ጋጋታ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ለማጭበርበር ችሎ ነበር፡፡ ጭራቁ አብይ አህመድ በነዚያ ስልጣን በያዘባቸው በመጀመሪያዎቹ ወራት የኢትዮጵያን ስም እያንቆለጳጰሰ በፕሮፖጋንዳ ቅጥፈት ሁሉም በሚባል ደረጃ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በመንጋ እንዲደግፉት አድርጎ ነበር፡፡
ያኔ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በአብይ የፍቅር ገመድ ታንቆ አረፋ ሲደፍቅ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በወለጋ፣ በምስራቅ እና በምዕራብ ሸዋ ትኩስ የደም ጎርፍ ይፈስ ነበር፡፡ የሚፈሰውን ደም እና ውስጥ ለውስጥ የኦህዴድ ኃይሎች የሚሰሩትን ደባ እና ሸፍጥ የተረዳው እስክንድር ነጋ እና ጥቂት ጓዶቹ ፓርቲ አቋቁመው የሰላ ተቃውሞ ሲያቀርቡ እስክንድር “እብድ ነው” ተብሎ ስሙን ለማጥፋት ተሞክሮም ነበር፡፡
በጭራቁ አብይ አህመድ በፍቅር ግለት ውስጥ የነበሩት እነ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ብርሀኑ ነጋ (ሳይነጋለት ይቅርና) እና ጭፍራዎቹ እስክንድር ላይ “እብድ ነው” ብለው አፋቸውን ለመክፈት ድድብናቸው አውንታዊ ፈቃድ ሰጥቷው ነበር፡፡ እስክንድር ግን “እብድ” አልነበረም፣ እስክንድር ግን የሚመጣውን አርቆ ማየት የሚችል የዘመናችን ነብይ ነው፣ እስክንድር ግን ለእነዚህ ጋጠ-ወጦች ምልሽ ለመስጠት ጊዜ አልነበረውም፣ እስክንድር ግን በጭራቁ አብይ አህመድ ዘመን ኢትዮጵያ እንደማታርፍ ተረድቶ ስራ ጀምሮ ነበር፡፡ እስክንድር የሰላማዊ ትግሉ ሁኔታ ተስፋ እንደሌለው ሲረዳ ደግሞ ለአማራ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው የተስፋ ምርኩዝ (ከእግዚአብሄር በታች) የሆነውን ፋኖን መቀላቀሉም የግለሰቡን ቆራጥነት የሚያስመሰክር ውሳኔ ነበር፡፡ የኢዜማ ኮልኮሌዎች በእስክንድር ነጋ ላይ ሲያሰራጩት በነበረው የስም ማጥፋት ዘመቻ ዛሬ ላይ ብዙዎቹ እንደ ባለ አዕምሮ ሰዎች ከሆኑ ሊፀፀቱበት ይገባል፡፡
ዘመነ ካሴ እና አስረስ ማረ ዳምጤ ሳንባ ርቆ ተሰቅሎባት ሽቅብ ሽቅብ እንደምታይ ድመት ሰልጣንን በርቀት ያማትራሉ እንጅ የአማራ ህዝብ ደም፣ እንባ እና ሰቆቃ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ለአብይ አህመድ መንግስት ቀናት በተጨመሩለት ቁጥር የሚያደርሰውን ጉዳት ተረድቶ ከወንድሞቻቸው ጋር ተስማምተው ስርዓቱን ከመገርሰስ ይልቅ በወንድሞቻቸው ላይ ዘመቻን ያውጃሉ፣ ለመግደል ሲዝቱ ይሰማሉ፤ ክፍለ ጦር በኮሎኔል ጌታሁን ላይ ያዛሉ፡፡ በየዕለቱ የአማራን ደም የሚጠጣ የሉሲፈር መንፈስ ያለበት አብይ አህመድን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የአማራ ወጣት ሆ ብሎ በተነሳበት ጊዜ እንዴት ሰው ለስልጣን ይሯሯጣል? እንዴትስ ሁኖ በወንድሙ ላይ ዘመቻን ያውጃል? አብሮት ሊሞት በተሰለፈው የትግል አጋሩ ላይ እንዴት ይዝታል? የእግዚአብሄር መንፈስ አዕምሮዓችሁን ይጎብኘው፡፡
የብልፅግና እና የኢዜማ ቡችሎች “እብድ ነው” እያሉ እስክንድርን ስሙን ሲያጠፉት እንደነበረው ዛሬ ደግሞ እነ መዓዛ መሀመድ(ሮሀ)፣ ህብር ሬድዬ፣ ግዬን ቲቪ እና መሰል ኮልኮሌዎች የእነ አስረስን እና የእነ ዘመነን አጀንዳ በመጋራት እስክንድር ከአብይ ጋር ተመሳጥሯል፤ ከታየ አፅቀስላሴ እና ከአምባሳደር ስልሽ ጋር ግንኙነት አለው፤ እስክንድር የአማራን ትግል ሊጠልፍ ነው፣ እስክንድር በፋኖዎች መካከል መከፋፈልን እያመጣ ነው የሚሉ በሬ ወለድ መረጃዎች በመንዛት የእስክንድርን ስም ለማጥፋት የሚሰነዘሩ ከንቱ ሙከራዎች ቢሆኑም እስክንድር ግን ከእውነት ጋር የቆመ አርበኛ ስለሆነ ልታሸንፉት አትችሉም፡፡ የብልፅግና እና የኢዜማ ተቀጣሪዎችም ጨኸታቸው የቁራ ጩኸት ሁኖባቸው እንደቀረ ልብ ይሏል፡፡
ጭራቁ አብይ አህመድን “በሞብ “ደግፈን የደረሰብንን መከራ እያየን፣ ሰው እንዴት በወሬ እና በአሉባልታ ጉዳዩን ሳያመዛዝን እንዴት የነፃነት ታጋዩን እስክንድርን “በሞብ ” ይቃወማል? የእን አስረስን፣ የዘመነን እንዲሁም የእን ዘመነን ተልዕኮ የሚጋሩ ሚዲያዎችን በመዳመጥ በእስክንድር በኩል ያለውን ሁኔታ ሳይመረምር እንዴት ሰው ፍርደ ገምድል ይሆናል? ሰው እንዴት ማሰላሰል ያቅተዋል? የሰው ልጅ እንደ ባለ አዕምሮ የሚሰማውን እና የሚያየውን ነገር መመርመር እንዴት ተሳነው? ሰው እንደ ገለባ ወይም እንደ አፈር እንዴት በወሬ ጎርፍ ይወሰዳል? ውድ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ በወሬ አትፈቱ፣ በአሉባልታ ጋጋታ እውነት አይሸፈንባችሁ፣ ነገሮችን ግራና ቀኝ አጢኑ፣ ጉዳዬችን በአንክሮ መርምሩ፡፡
ቸር እንሰንብት፡፡
በትግሉ ለተሰው ታጋዬቻችን ዘላለማዊ እረፍትን ፈጣሪ ይስጥልን፡፡