መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ፣ ያማራን ጠላቶች ማንነት ያላገናዘበ ብአዴናዊ መፈክር
ይገሰማል እንጅ ውሃ አይላመጥም፣ ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም።
መስፍን አረጋ
እነ ዘመነ ካሴ እንደሚሉት፣ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻውም አማራ ነው ማለት፣ የትግሉ አላማ አማራ ክልል የሚባለውን ወያኔ ሠራሽ ክልል በመቆጣጠር በቂ ኃይል ገንብቶ በቀረው የጦቢያ ክፍል ላይ ከኦነግና ከወያኔ ጋር መደራደር ማለት ነው። ስለዚህም ትልቁ ጥያቄ ካማራ ጠላቶች ከወያኔና ከኦነግ ጋር መደራደር ይቻላል ወይ የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ ለመመልስ ደግሞ ወያኔና ኦነግ ላማራ ሕዝብ ምን ዓይነት ጠላቶች ናቸው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል።
ጠላቶች የድርጊት ጠላት እና የማንነት ጠላት ተብለው በሁለት ምድቦች ሊመደቡ ይችላሉ። የድርጊት ጠላት ማለት በድርጊት ሳቢያ የሚጠላ ጠላት ማለት ሲሆን፣ የማንነት ጠላት ማለት ደግሞ በማንነት (ማን በመሆን) ሳቢያ የሚጠላት ጠላት ማለት ነው። ድርጊትን መለወጥ ይቻላል። ማንነትን ግን መለወጥ አይቻልም፣ “በውኑ ጦቢያዊ መልኩን፣ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይችላልን?” እንዲል ክቡር መጽሐፍ (ኤርምያስ 13፡23)።
በድርጊትህ የሚጠላትህን ጠላት በድርጊትህ ላይ በመደራደር ጠላትነቱን ልታለዘበው ወይም ጨርሶ ልታጠፋው አልፎ ተርፎም ወዳጅህ ልታደርገው ትችላለህ። ለምሳሌ ያህል ወያኔና ኦነግ የድርጊት ጠላቶች ናቸው፣ ጠላትነታቸው የስልጣንና የጥቅም ብቻ ነውና። የስልጣንና የጥቅም ቅሬታወቻቸውን ካስወገዱ ደግሞ ጠላትነታቸውም አብሮ ይወገዳልና፣ እየተወገደም ነውና። የጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ መንግስት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ትግሬወች በጦርነትና በረሐብ መሞት ቀጥተኛ ተጠያቂ መሆኑ፣ ወያኔን ከጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ መንግስት ጋር ከመወዳጀት ያላገደውም በዚሁ ምክኒያት ነው። ባደባባይ እየተንከባለሉ ጭራቅ አሕመድን ሲያወግዙ የነበሩት ወያኔወች አሁን ላይ ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ቀንደኛ ደጋፊወች የሆኑትም አነግን ጠልተውት የነበረው በድርጊቱ እንጅ በኦነግነቱ (በማንነቱ) ባለመሆኑ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ በማንነትህ የሚጠላህ ጠላት የሚጠላው ድርጊትህን ሳይሆን አንተነትህን ስለሆነ፣ ያደረከውን ብታደርግለት (ወርቅ ብታነጥፍለት) ጠላትነቱን ማጥፋት ቀርቶ ልትቀንሰው አትችልም። እንደውም በተቃራኒው ጠላትነቱን እቀንሳለሁ ብለህ ስትለማመጠው (appease) በጥላቻው ላይ ንቀት ይጨምርበትና የበለጠ ይጠላሃል። እንደጠላህ ጠልተኸው ባገኘኸው ጅራፍ ስትገርፈው ግን፣ ቢጠላህም እንዲያከብርህ በማስገደድ ጥላቻውን ታለዝበዋለህ።
ማክበር የግዴታ መውደድ የቸሬታ ስለሆነ፣ በማንነትህ የሚጠላህን ጠላት እንዲያከብርህ እንጅ እንዲወድህ ማስገደደ አትችልም። ማስገደድ ቀርቶ ማስተማርም አትችልም። አብናቶቻችን (ማለትም አባቶቻችን እና እናቶቻችን) ይገሰማል እንጅ ውሃ አይላመጥም፣ ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም የሚሉትም መቸም ወዳጅ የማይሆንን የማንነት ጠላት ነው።
በማንነትህ የሚጠላህ ጠላት ምንም ብታደርግለት ጠላትነቱ መቸም የማይወገድ ስለሆነ፣ ዘላለማዊ ጠላትህ ነው። ስለዚህም በማንነትህ የሚጠላህን ዘላለማዊ ጠላትህን በተመለከተ ያሉህ ምርጫወች፣ እርሱን ማጥፋት ወይም በርሱ መጠፋት ወይም ደግሞ ርስበርስ መጠፋፋት ብቻ ነው። ከነዚህ ሦስቱ ምርጫወች ውጭ ሌላ ምርጫ የለህም። በማንነትህ ከሚጠላህ ዘላለማዊ ጠላትህ ጋር ማድረግ የምትችለው ገድሎ የመዳን የሞት ሽረት ትግል ብቻ ነው። በተለይም ደግሞ በማንነትህ ከሚጠላህ ጠላት ጋር መከራከርም ሆነ መደራደር አትችልም፣ ዓላማው አንተን በማጥፋት ማንነትህን ማጥፋት ነውና። በማንነትህ የሚጠላህ ጠላት እንደራደር ካለህ ደግሞ፣ ለመደራደር አስቦ ሳይሆን በድርድር አዘናግቶ ሊያጠፋህ ሲፈልግ ብቻ ነው።
ወያኔና ኦነግ አማራን በድርጊቱ ሳይሆን አማራ በመሆኑ (ባማራዊ ማንነቱ) ብቻ የሚጠሉ፣ መነሻቸውም መድረሻቸውም አማራን ማጠፋት የሆነ፣ አማራን ከምድረገጽ ካላጠፉ የማይተኙ፣ ያማራ ሕዝብ የማንነት ጠላቶች፣ ስለሆነም ዘላለማዊ ጠላቶች ናቸው። መሆናቸውን ደግሞ ደግመው ደጋግመው አስመስክረዋል።
ወያኔ አማራን በማታለል ያማራን ድጋፍ ካላገኘ ስልጣን እንደማይዝ ያውቅ ስለነበር፣ ኢሕአዴግ የሚባል የኢትዮጵያን ስም ያዘለ አማራን ማታልያ የቁጩ ድርጅት መስርቶ አማራ ነጠቀኝ ያለውን ስልጣን ባማራ ድጋፍ ያዘ። አማራ ነጠቀኝ ያለውን ስልጣን ባማራ ድጋፍ ከያዘ በኋላ ግን፣ አማራን አሸነፍኩ አለና ባማራ ጥላቻው ላይ ንቀት ጨምሮበት፣ ላማራ ያለው ጥላቻ ደግሞ ከመለዘብ ይለቅ ይበልጥ ብሶበት ሥራው ሁሉ አማራን መጨፍጨፈ፣ መዘለፈ፣ ማወረድና ማሳደድ ሆነ። አማራን የበለጠ ሲመስለው፣ ያማራ ጥላቸው የበለጠ ሆነ። አማራን የሚጠላው በስልጣን ጉዳይ ሳይሆን አማራ በመሆኑ (ባማራዊ ማንነቱ) እንደሆነ በግልጽ አሳየ።
በተመሳሳይ መንገድ ኦነግ አማራን በማታለል ያማራን ድጋፍ ካላገኘ ስልጣን እንደማያገኝ ያውቅ ስለነበር፣ ኢትዮጵያ ሱሴ፣ ኢትዮጵያ ቅብጥርሴ፣ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እያለ የኢትዮጵያን ስም እያንቆለጳጰሰ አማራ ከለከለኝ ያለውን ስልጣን ባማራ ድጋፍ አገኘ። አማራ ከለከለኝ ያለውን ስልጣን ባማራ ድጋፍ ካገኘ በኋላ ግን አማራን አሸነፍኩ አለና፣ ባማራ ጥላቻው ላይ ንቀት ጨምሮበት፣ ላማራ ያለው ጥላቻ ደግሞ ከመለዘብ ይለቅ ይበልጥ ብሶበት ሥራው ሁሉ አማራን ማረድ፣ ማወራረድ፣ መስቀል፣ ማፈናቀል ሆነ። ካማራ በላይ ከፍ ያለ ሲመስለው፣ ያማራ ጥላቸው ከፍ አለ። አማራን የሚጠላው በስልጣን ጉዳይ ሳይሆን አማራ በመሆኑ (ባማራዊ ማንነቱ) እንደሆነ በግልጽ አሳየ።
የማንነት ጠላት በራሱ ማንነት ስለማይተማመን አለቀጥ ፈሪ ነው። አልቅጥ ፈሪ ስለሆነ ደግሞ በዚያው ልክ አለቅጥ ጨካኝ ነው። አለቅጥ ጨካኝ ስለሆነ ደግሞ ብትሩ አለቅጥ አሰቃቂ ነው፣ የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር እንዲሉ። ወያኔና ኦነግ አማራን አሸንፈን ስልጣን ላይ ወጣን ካሉ በኋላ ባማራ ሕዝብ ላይ በዚህ ደረጃ የጨከኑትም፣ ያማራ ስም ሲጠራባቸው ሲቃዡ የሚያድሩ ቱርቂወች ስለሆኑ ነው። ባማራ ድጋፍ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ ተራሮችን አንቀጠቀጥን፣ ነፍጠኛን ሰበርን እያሉ ቱሪናፋ በመንፋት አማራን ለማስፈራራት የሚሞከሩትም፣ እንቅልፍ የሚነሳቸውን ያማራ ፍራቻ ለመወጣትና ራሳቸውን በራሳቸው ለማደፋፈር ሲሉ ብቻ ነው።
በተጨማሪ ደግሞ የማንነት ጠላት፣ የራሱን ማንነት የሌላውን ማንነት በማጥፋት ላይ የመሠረተ፣ በሥርሰደድ (chronic) የማንነት ቀውስ የሚሰቃይ፣ የዝቅተኝነት መንፈስ ክፉኛ የሚጫወትበት የስነልቦና በሽተኛ ነው። ወያኔ ማንነቱን መሠረት ያደረገው የሐበሻ የሚባሉት ትውፊቶች (ታሪክ፣ ሐይማኖት፣ ባሕል፣ ስነጽሑፍ ወዘተ. ) አንዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉም የትግሬና የትግሬ ብቻ ናቸው በሚለው ድቡሽት ላይ ነው። ለዚህ ደግሞ የአማራን ሕዝብ ቀን ከሌት ስለሚዘልፍ ብቻ ወያኔወች በታላቅ አክብሮት “መምህር” ይሉት የነበረው፣ ነውር ጌጡ የሆነው ወያኔው አቶ ገብረኪዳን ደስታ “ትግሬ የራሱ ታሪክ አለው፣ አሮሞም የራሱ ታሪክ አለው፣ አማራ ደግሞ የራሱን ታሪክ ይፈልግ” ሲል የተናገረውን መጥቀስ ብቻ ይበቃል። ስለዚህም ወያኔ አማራን ለማጥፋት የተነሳው ይህን በድቡሽት ላይ የተመሠረተ የትግሬነት ማንነቱን እውን ማድረግ የሚችለው አማራን በማጥፋት ስለሆነ ብቻ ነው።
የወያኔ ጎጠኛ የትግሬን ማንነት ከሚወደው በላይ ያማራን ማንነት ይጠላል፣ ከትግሬ መጠቀም በላይ ባማራ መጎዳት ይደሰታል፣ ያማራን አንድ ዓይን የሚያጠፋለት እስከሆነ ድረስ የትግሬን ሁለት ዓይን ከሚደረግም ጋር ይተባበራል። ጭራቅ አሕመድ፣ ጃዋር ሙሐመድ፣ ሕዝቅኤል ጋቢሳና ሌሎች የኦነግ ብልጣብልጦች በትግሬ ሞት አማራን ለማጥፋት የተነሱትም፣ የወያኔ ጎጠኛ ትግሬን ከሚወደው በላይ አማራን እንደሚጠላ በደንብ ስለሚያውቁ ነው። ወያኔ ደግሞ አማራን ለማጥፋት ከኦነግ ጋር የሚተባበረው፣ ኦነግ ተሳክቶለት አማራን ቢያጠፋ፣ ቀጥለው የሚያጠፋው ትግሬን እንደሆነ በደንብ እያወቀ ነው። ወያኔ ግን፣ አማራ ይጥፋለት እንጅ ትግሬ ቢጠፋ ግድ የለውም።
ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል፣ ባዲሳባ ውስጥ ከሚገኙት አዳዲስ ሕንፃወች ውስጥ አብዛኞቹ የወያኔወች ሲሆኑ፣ የተሠሩትም በወያኔ ዘመን በተዘረፈ መሬትና ሐብት ነው። የወያኔ ጎጠኞች ግን፣ ኦነግ አንድ ያማራ ጎጆ እስካፈረሰ ድረስ መቶ የትግሬ ሕንፃ ቢወርስ ዴንታ ስለሌላቸው፣ ከኦነግ በላይ ኦነግ ሁነው አዲሳባ የኦሮሞ ናት እያሉ ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። ወያኔ አማራን የሚጠላው እስከዚህ ድረስ ነው።
ኦነግ ደግሞ አማራን ለማጥፋት የተነሳው በጭፍጨፋ የተስፋፋ መጤ የመሆን ታሪኩን ማጥፋት የሚችለው አማራን በማጥፋት ስለሆነ ነው። የኦነግ ትርክት አሌፍና ፓሌፍ (አልፋና ኦሜጋ) አማራ መጤ ነው የሚለው የሆነበትም ምክኒያት ይሄው ነው፣ ኋላ የመጣ ዓይን አወጣ እንዲሉ። ጥንካሬው አረመኔነቱ ብቻ የነበረው፣ አባ ባሕሬ ዜናሁ ለጋላ ላይ እንደዘገቡት ደግሞ ታፋው ላይ በሚፍለከለከው የኮሶ ትል ብዛት ይታበይ የነበረው የሉባ ዘላን ሠራዊት፣ በሐበሻ ምድር ላይ ተስፋፍቶ የተንሰራፋው፣ ሱማሌ በጅራፍ ሲገርፈው ከነከብቱ እየከነፈ፣ በግራኝ ጦርነት የተዳከመውን የአማራን ሕዝብ ያለርህራሄ እየጨፈጨፈ ነበር። ይህ እውነታ ደግሞ አነግን ስለሚያሸማቅቀው፣ አማራን ድራሹን በማጥፋት እውነታውን ለማጥፋት የማይፈነቅለው ዲንጋ፣ የማይቆፍረው ጉድጓድ፣ የማይፈበርከው ሐሰት፣ የማይፈጽመው ሐጢያት የለም።
ወያኔና ኦነግ አማራን አማራ በመሆኑ ብቻ የሚጠሉ፣ የአማራን ሕልውና ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ፣ የአማራ ሕዝብ የማንነት ጠላቶች ስለዚህም ዘላለማዊ ጠላቶች ስለሆኑ፣ ወያኔንና ኦነግን በተመለከተ የአማራ ሕዝብ ያለው ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም ወይ እነሱን ማጥፋት ወይም በነሱ መጥፋት ነው። በመሆኑም፣ የአማራ ሕዝብ መቸም ወዳጅ ከማይሆኑት፣ ከዘላለማዊ የሕልውና ጠላቶቹ ከወያኔና ከኦነግ ጋር መደራደረ ቀርቶ ለመደራድረ ማሰብም የለበትም።
መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ የሚለው የነ ዘመነ ካሴ መፈከር ላማራ ሕልውና የማይበጅ ብአዴናዊ መፈክር ነው የሚባለውም፣ ዓላማው ባማራ ሕዝብ ስም ከወያኔና ከኦነግ ጋር መደራደር በመሆኑ ነው። የወያኔና የኦነግ ዓላማ ግን ሰጠቶ በመቀበል መርሕ መሠረት ካማራ ሕዝብ ጋር ተደራድረው፣ ተከባብረው ለመኖር አይደለም። ወያኔና ኦነግ አማራን አማራ በመሆኑ ብቻ የሚጠሉ ያማራ ሕዝብ የማንነት ጠላቶች ስለሆኑ፣ መቸም የማይለወጥ ቋሚ ዓላማቸውና ዘላለማዊ ምኞታቸው አማራን ሙሉ በሙሉ አጥፍተው ጦቢያን አማራአልባ ማድረግ ነው። ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ከወያኔና ከኦነግ ጋር እደረደራለሁ ቢል፣ ትርፉ ወያኔና ኦነግ ይበልጥ ተጠናክረው የሕልውናውን ክስመት ይበልጥ እንዲያፋጥኑት ጊዜ መስጠት ብቻ ነው። ስለዚህም፣ መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ የሚለው የነ ዘመነ ካሴ መፈክር አማራን ከጠፋት የሚቤዝ (የሚያድን)፣ ቤዛማራ መፈክር ሳይሆን፣ ወያኔና ኦነግ አማራን እንዲያጠፉ የሚያመቻች ፀራማራ መፈክር ነው።
እስክንድር ነጋ እንደሚለው፣ ያማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል መነሻው አማራ መድረሻው ጦቢያ ነው ማለት፣ የጭራቅ አሕመድን (በወያኔ የሚደገፍ) ኦነጋዊ መንግስት ካፈራረሱ በኋላ በፍርስራሹ ላይ ጦቢያን ጦቢያ ለማድረግ ያንበሳውን ሚና የተጫወተው፣ በጦቢያዊነቱ የማይደራደረው፣ በቁጥር ደግሞ ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ድምር በሚሊዮኖች የሚበልጠው ትልቁ ያማራ ሕዝብ በቁጥሩ መጠን ተመጣጣኝ ሚና የሚጫወትባትን፣ በተገቢው ደረጃ አማራ አማራ የምትሸትን፣ ሕብረብሔራዊት ጦቢያን እንዳዲስ መገንባት ማለት ነው። በተለይም ደግሞ የመነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ ዓላማ ወያኔንና ኦነግን ድምጥማጣቸውን ካጠፋ በኋላ፣ የወያኔና የኦነግን ፀራማራ አጀንዳ የሚፈጽሙ ቀርቶ የሚያልሙ ሰወች ትርው (ዝር) የማይሉባትን፣ ከፀራማሮች ሙሉ በሙሉ የፀዳችን፣ ፀራማሮች ብቅ ባሉ ቁጥር ወዲያውኑ እንዲጠልቁ አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ ባፋጣኝና በቁርጠኝነት የሚወሰድባትን፣ ጎጥኝነት በሕግ የተከለከለባትን፣ አዲሲቷን ጦቢያ መመሥረት ነው። መነሻችን አማራ መድረሻችን ጦቢያ የሚለው መፈክር ያማራን ሕልውና የሚታደግ፣ ያማራ ቤዛ የሆነ አማራዊ መፈክር ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው።
እነ ታምራት ላይኔ በመለስ ዜናዊ ቀጭን ትዕዛዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን) ይሰኝ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ድርጅታቸውን አፍርሰው፣ መለሰ ዜናዊ ባወጣላቸው የትግረኛ ስም ብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብእዴን) መባልን መርጠው፣ ራሳቸውን ከኢትዮጵያዊነት አውርደውና አዋርደው አማራን እንወክላለን እያሉ፣ የፀራማሮቹ የወያኔና የኦነግ ሎሌወች ሁነው አማራን ቁጥሩ በሚሊዮናች እስኪቀንስ ድረስ የሚችሉትን ያህል ጨፈጨፉት፣ አስጨፈጨፉት። የብአዴን ውላጆች የሆኑት እነ ዘመነ ካሴ ደግሞ ራሳቸውን በራሳቸው ከጦቢያዊነት ማማ አውርደው፣ መነሻቸውንም መድረሻቸውንም ወያኔና ኦነግ ከብአዴን ጋር በመተባበር በፈጠሩት አማራ ክልል ላይ አድርገው፣ መነሻችን አማራ መድረሻችንም አማራ ብለው የተነሱት፣ ባማራ ሕዝብ ስም እየነገዱ፣ ብአዴን መንገድ እየነጎዱ (እየሄዱ)፣ አማራን እያዋረዱ ከጦቢያዊነት ሊያወርዱ ነው።
ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተነሳው በእስክንድር ነጋ ላይ ግልጽ ጦርነት እከፍታለሁ ብሎ በመዛት ነበር። ያማራ ሕዝብ ደግሞ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ በማድረግ ቅኔያዊ ፍትሕ (poetic justice) ሊሰጠውና ሕልውናውን ለማጠፋት የሚማከሩ ቀርቶ ዝንቡን እሽ ለማለት የሚሞክሩ ፀራማሮች ትርው (ዝር) የማይሉባትን ጦቢያን መመሥረት የሚችለው እስክንድር ነጋ በፈጠረው መነሻች አማራ መድረሻችን ጦቢያ በሚለው መሪ መፈክር ሥር በመታገል ብቻ ነው።
መስፍን አረጋ ⇓
mesfin.arega@gmail.com