>
5:26 pm - Saturday September 15, 3246

ሸዋ የአማራ ተጋድሎ ድል ቁልፍ ነው!

ሸዋ የአማራ ተጋድሎ ድል ቁልፍ ነው!

 

ሰሞኑን የተቀናጀና የተቀነባበረ ዘመቻ በሸዋ ጠቅላይግዛት እዝ ፋኖዎቻችን ላይ መከፈቱን እያየን ስለሆነ ይህ ከኦሮሙማው ሀይል ባላነሰ አማራ ነን በሚሉት ድርጅቶችና ግለሰቦች እየተደረገ ያለውን ዘመቻ መመርመር ያስፈልጋል። እንናገር ካልን እንደውም የሚደረገው ስም ማጥፋት ከጨፍጫፊው የኦሮሙማ ሀይል ጋር የተቀናጀ(overlapping) የሚመስልበትን ሁኔታም ታዝበናል።

ተወደደም ተጠላም የአማራ ተጋድሎ ቁልፍ ያለው ሸዋ ላይ ነው። ሸዋ ሳታሸንፍ የትም አትደርስም። ሸዋ ከተሸነፈ ተጋድሎአችን ከዳር አገር አመፅነት (peripheral uprising) ያለፈ ዋጋ አይኖረውም። አገዛዙ ከሌሎቹ ክፍለ ሀገሮች በተለየ ሸዋ ላይ ላለፈው አንድ አመት በሪፐብሊካን ጋርድና በኮማንዶ ብቻ ሲዋጋ የከረመው ለምን እንደሆነ ልናስተውል ይገባል።

ዛሬ የግዙፉን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሪዎችን ለማሰይጠንና እዙን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱት ሁሉ የአማራ ህዝብ ጠላቶች ናቸው የምንለው የሀይልና የስትራቴጂክ ሬሌቫንስ ትንተና ሰርተን እንጂ እንዲሁ ስም ለመለጠፍ ፈልገን አይደለም። ሸዋን ነፃ ማውጣት አገዛዙን በኢኮኖሚም፣ በፖለቲካም ሆነ በዲፕሎማሲው መስክ ያብረከርከዋል።

የሰሞኑ ስም ማጥፋትና ማሰይጠን የሚመራው ደግሞ በዲያስፖራዎቹ የደም ነጋዴዎች ነው። በተለይም የእስክንድር ወደ አማራ ፖለቲካ መምጣት ገቢያቸውን ያቀዛቀዘባቸው የዲያስፖራ የእንባ ቸርቻሪዎች የሸዋውን ግዙፍ ሀይልና መሪውን መከታው ማሞን በሙሉ ሀይላቸው እያጠቁ ያሉት ሸዋ ከበረታ ትግሉ እንደሚያጥር ስለሚታወቅ ነው። ትግሉ መተዳደሪያቸው ስለሆነ በድል እንዲጠናቀቅ አይፈልጉትም።

@habtamumtm

እናም አማራዬ በነፋስ አትወሰድ።

ወንድሞችህን ተከላከል አግዝ አለሁ በላቸው!!

Filed in: Amharic