>

ማህበራዊ ሚዲያ እና የአማራ የህልውና ትግል፡ የሀሰት መረጃ ስርጭት ተጽዕኖ

ማህበራዊ ሚዲያ እና የአማራ የህልውና ትግል፡ የሀሰት መረጃ ስርጭት ተጽዕኖ

ግርማ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)

(ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተረጎመው፡ ደሳለኝ ቢራራ)

መግቢያ

ስለማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ገጽታዎች ብዙ ተብሏል። ተጽዕኖዎቹም ፈርጀ ብዙ መሆናቸው ታውቋል። የስነተግባቦታችን ባህርይ የሚወሰነውም በማህበራዊ ሚዲያዎቹ አጠቃቀም ላይ በምናሳየው ስነምግባር እየሆነ መጥቷል። አሉታዊ ይዘት የሚበዛበት ተግባቦት በየማህበራዊ ሚዲያው እየተንሰራፋ ነው። የማህበራዊ ሚዲያ አሉታዊ ተጽዕኖዎች በስፋት ቢጠኑም የተሳሳቱ እና የሀሰት መረጃዎችን ስርጭት መደበኛ ማድረግ ግን በተገቢው ደረጃ አልታየም። የሀሰት መረጃ እና የተሳሳተ መረጃን ሆን ብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት የዘመናችን ስነተግባቦት ካንሰር ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። እነዚህ ችግሮች ከጽንፈኛ አመለካከቶች እና ከጥላቻ ፖለቲካው ባላነሰ እንዴያውም በበለጠ፡ ከፍተኛ ቀውስ የሚፈጥሩና ዋጋቸው በደም የሚከፈል እዳዎች ናቸው።
በዚህ ጽሁፍ ትኩረት የማደርገው የማህበራዊ ሚዲያው በአማራ ፖለቲካና በህልውና ትግሉ ዙሪያ ያለውን እኩይ እና መርዛማ መስተጋብር ነው። እነዚህን መስተጋብሮች:-

 

ኢትዮ ሪፈረንስ :- መነበብ ያለበት ጽሑፍ መሆኑን እንመክራለን።  ለማንበብ ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

 ማህበራዊ ሚዲያ እና የአማራ የህልውና ትግል፡ የሀሰት መረጃ ስርጭት ተጽዕኖ

Filed in: Amharic