ከጌታቸው እና ከደብረፅዮን ድብድብ ምን እውነት አገኝን?
አሸናፊ
ሰሞኑን መቼም የፓርቲዋች መከፈል የሚባል ቫይረስ ገብቶ እያንዳዳቸውን የቤታቸውን ገበና እያዘከዘካቸው ይገኛል። ፋኖ አገር አዳኝ እየተባለ ሲሞካሽ ዘመነ ካሴ አፈንድቶት ቁጭ ከለ። ¨እኔ መንገዴ የትህነግ ኢህአዴግ አይነት ነው¨ ብሎ ቁጭ አለ። ¨እኔ አራት ኪሎ ካልገባሁ ምን አገባኝ ለኢትዮጵያ¨ ብሎ ቁጭ። ዘሜ ያልገባት ሌላው ብሔር ብሔረሰብ የሱን ንግር እንዴት እንደሚያያት ነው። ለስክንድር ሀሳብ ቦታ አጥቶ ¨ላግኝው ተኩሼ ልክ አገባዋለሁ¨ ንግግር ለሌሎች ብሔሮች ከአደጋም አደጋ በላይ እንደሆነ ግልጽ ማሳያ መሆኑ መች ገብቶት?!… እናም ፓለቲካ ስትገማ እንዲህ ናት።
ከነሱ መለስ ስንል ደግሞ የትህነግ ክፍፍል ነው ። ማነው ከሽንፈት መልስ ዋና ችግር በፓርቲ መካከል የሚኖር ክፍፍል ነው ያለው። ዋጥ አርገዋት ከርመው ነበር አሁን ግን አልቻሉም ጌቾ ምላሱ አፈነዳችው። የዚህ ዘመን ትውልድ ትግልን በውስኪና በቁርጥ የምታውቀው ። 17 አመት ትግልን በትረካ እና ፕሮቫዋን ለ8 ወር ብቻ የምታውቀው ጌቾ ከትህነግ ቀንበር ሸርተት ብላ ጉድ አፈላች። ይህው ተበጣበጡት። ጌቾ በአንድ በኩል ደጺ በሌላ በኩል ተናረቱ። ከሁለቱ ጌቾ ትንሽ በጥራቃ ብትሆንም ከንግግሯ መሀል ጥሩ ጥሩ መረጃ አግኝተናል። መረጃ አንድ ጦርነቱ አሸንፈናል አሜሪካ ተመለሱ ብላን ነው የአብይን ወታደር ዘርረነው ነው ፓለቲካ ስላልመራ ነው ወደ ኋላ የተመነስነው እያሉ ሲበጠረቁ የነበሩ የትግራይ የትህነግ ፓለቲካ ኤሊቶች ጌቾ በማያሻማ መንገድ ጦርነቱን ተሸንፈው መቀሌ ዙሪያ ተከቦ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ እንደነበር አረጋገጠልን። ይችን አድም ትግሪ ብሏት የማያውቀውን ወይም በሹክሹክታ ለሚስቱ የሚነግራትን ሚስጥር ጌቾ ዘረገፈላቸው። እኛም ብለን ነበር እናመሰግናለን ጌቾ።
ሌላው እውነት የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲሆን ከእስታሊን ቴድሮስ አንባሳደር ፍሳሀዪ ስዪ እረ ስንቱ ህወሀት አሸናፊ እንዳደረጋት ሲበጠረጉ ነበር። የትግሪ ፓለቲካ ኤሊቶች የአሸናፊነት ሰነድ እንደሆነ ሲበጠረቁ እንዳልከረሙ ሁላ ጌቾ ምላሱ ነፍሳቸውን ያዳኑበት ሰነድ እንደሆነ ። ከፍጽም መጥፋት የአብይ የማሪያም መንገድ እንደሆነ በማያሻማ ሁኔታ አረጋግጦልናል። ከሱ ይልቅ የናይሮቢው የውስጥ ስምምነት የተሻለ እንደነበረ በገደምዳሜው ነግሮናል።
ሌላው በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት መሳሪያ መፍታት ሲገባቸው እንዳልፈቱ ስምምነትቱ ናይሮቢ ላይ እንደተስተካከለ በመንገር የአብይን የድብቅ ስምምነት መሳሪያ አስረከብ የኢቲቪ እና የፋና ፕሮፓጋንዳ ውሸት መሆኑን አረጋግጦልናል። ሌላው ደግም ቲዲኤፍ ጉዳይ ወሪ መሆኑን በተግባር ትንሽዪ ጥንቸል መሆኗን እና እነሱ ግን በመቶሺ ናቸው እያሉ ሊያገዝፏት እንደሚፈልጉ በገደምዳሜ ነግሮናል። እናመሰግናለን ጌቾ ካንተ ካልሆነ ከማን እንሰማ ነበር። መቼም ከደብረጺዮን አትለኝም። ጌች እራያ ልጅ። እንኳንም አላማጣ ተወለድክ።
ሌላው ጌቾ የቀጠፋት ነገር ጦርነቱ መንስኤ ምርጫው እንደሆነ ሊነግረን ፈልጓል እናም ያሁኑ ምርጫ ለጦርነት ነው ሲል ተናግራል። እዝች ጋር ግን ትልቅ ውሸት ናት ጦርነቱ መንስኤ ምርጫ ላመሆኑ ማሳያ ላምጣ ። ምርጫው በተደረገ በሳምን አካባቢ አብይ ኢንተርቪው ተደርጎለት ነበር። ቃል በቃል ያለው ህግን የጣሰ ቢሆንም አብረውን ቢያደርጉት የተሻለ ይሆን ነበር ያኔም አሁንም የሚያሸንፈው ትህነግ ስለሆነ ለመቀበል ችግር የሌለበት መሆኑን አስምሮ ተናግሯል። እናም ጦርነቱ የጀመረው ሰሜን እዝን በመግደላቹ ወደ አራት ኪሎ ጉዞ በመጀመራቹ ብቻ ነው ። ይችን*እውነት ደግሞ መቼ ትነግረን ይሆን?
ደጺ ደግም ምን ነገረን መሰላቹ አንደኛው ከኤርትራው ኢሳያስ ጋር ሰላም ለመፍጠር ከአማራ ፋኖ ጋር ሰላም ለመፍጠር እንደሚፈልጉ ይህንንም በጋራ ተነጋግረው ወስነው በጌቾ አማካኝነት እንደተጀመረ አብይ እንደሚያውቀው አስረድቶ ጌቾን እና አብይ አይን ላይ በርበሪ ነው የጨመረው። ጌቾም ከኤርትራ ጋር አብራ ጦርነት ልትጀምር ነውን ፓለቲካ ወሪ መሆኑን ነው ያረጋገጠው ። እንግዲህ ጀኖሳይደር እያለች በየቀኑ የምትሰድበው ኢሳያስ እግር ላይ ትህነግ ድፍት ብላለች። በበኩሌ ከዚያ ከኛ በላይ ተዋጊ ከኛ በላይ ጀግና ትርክቷ ወጥታ ጭንቅላቷ ትንሽ ወደ ፓለቲካ ጨዋታ መመለሷ አስደስቶኛል። እውነቷን ከሆነ።
ሌላው በኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር የሚጠብቅ አንድም ኢትዮጵያ ወታደር አለመኖሩን አረጋግጦልናለ። እናም ተፋጠዋል ወሪ እንደሆነ ድንበሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጧል። በመሆኑም የስዪም ተሾመ ፉከራ እንደ ቲዲኤፍ 275 ሺ ጧር ጉዳይ መሆኑን አረጋግጦልናል።
ሌላው የደጺ ንግግር የገለጸው እውነት አብይ ለድሮን መተኮሻ የሚያወጣውን ገንዘብ ወደ ጥሪ ገንዘብ በመቀየር ትህነግ ላይ በማርከፍከፍ የተወሰኑትን ገቢ ማድረግ መቻሊን አሳብቆልናል። እናም በቅርብ ጊዜ ትህነግ ብልጽግናን እንደምናይ አትጠራጠሩ። ጌቾም አይናን እንኳን መግለጽ አቅቷት የማማ ዝናሽ ያደፈ ነጠላ መስላ እንዳልነበር አሁን ሴሚላክ የዋጠ ህጻን መስላ መኖር ሳይመቻት አልቀረም። ማነው ጌቾ ቁርጥና ውስኪ ካገኝ ያለው… እውነት ሆነ ማለት ነው? ይብላኝ ልጆቿን ለተነጠቀች ይብላኝ አካላቸው ለጎደለ የትግራይ ወጣቶች።