እጅግ አስገራሚ ድል !
የፋኖ ትግል ከተጀመረ ወዲህ በዚህ ደረጃ አስደማሚ ድል ሲመዘገብ የመጀመሪያ ነው ማለት ይቻላል። በዕለተ አርብ በጎንደር አይምባ ላይ የተመዘገበው ድል የብርሃኑ ጁላን ጦር በአስደናቂ ሁኔታ ያንኮታኮተ ነው።
በቁጥር 30 የሚሆኑ ስንቅና ትጥቅ የጫኑ ለማገዶ የተላኩትን የኦህዴድ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ለምልክት ሳይተርፉ በደፈጣ ጥቃት ብትንትናቸው ወጥቶ ጭሳቸ ሲጉለፈለፍ አምሽቱኣል። ብርሃኑ ጁላ ስምሪት የሰጣቸው የመከላከያ ዩኒፎርም የለበሱ 800 ወታደሮች ከነ አዛዣቸው እጅ ወደላይ ብለው የተማረኩ ሲሆን እንቢኝ ብለው ያንገራገሩ በገፍ በየ ጢሻው ስር ወድቀዋል።
በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ በፋኖ እጅ ገብቷል። የተማረከው መሳሪያ በብዛትና በአይነት በዚህ ደረጃ ተገኝቶ አያውቅም።
የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን ከመሰረቱት መካከል የጎንደር እዝ እና የአማራ ፋኖ በጎንደር ሁለቱም አደረጃጀቶች አንድነታቸውን በማጠናከረ አስደናቂ ድል ማስመዝገባቸውን የቀጠሉ ሲሆን፥ በወሎ እና በሸዋም እጅግ ከፍተኛ ኦፕሬሽን እየተሰራ ይገኛል።