>

የርስዎ ፊርማ ሜሪንና ልጁዋን ያድናል። እባክዎ በፊርማዎ የሰው ህይወት ይታደጉ

photo - Let Mary Stay pititionsሜሪ ትባላለች። ኖርዌይ ለመድረስ ከከፈለችውና ከገጠማት ኣሳዛኝ ነገር ኣንዱ በሰው ደላሎች የደረሰባት ነገር ነው። ሃገሪቱ ውስጥ ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች።  ሜሪ – መረራት። እናም ወደ ጣሊያን ለመድረስ በደላሎች ጉዞዋን ጀመረች። የሱዳንና የሊቢያን በረሃ ከኣጉዋጉዋዦች ጋር ስትቀጥል በመሃሉ ሴትነቱዋ በጨካኞቹ የሰው ደላሎች ተደፈረች። ደፋሪዎቹዋ ንጹህ ኣልነበሩም ። የ ኤድስ በሽታ ኣስያዙዋት። በመደፈሩዋም ጸነሰች። እንደኣጋጣሚ ሆኖ የተወለድው ልጁዋ ከበሽታው ነጻ ነው። ሜሪ ከሊቪያ በሁዋላ ወደ ጣሊያን የገባች ቢሆንም የኢጣሊያ መንግስት የደረሰባትን ግፍ በማመን የፖለቲካ ጥገኝነት ሰጥቶኣት ነበር። ነገር ግን በየጊዜው ክትትል የሚያስፈልጋትን የ ኤድስ መድሃኒትና ለሰው ልጅ የሚያስፈልገውን ነገር ማግኘት ባለመቻሉዋ ወደ ኖርዌይ ኣቀናች። ኖርዌይ በመግባቱዋ ጣሊያን የማታገኘውን – ማግኘት ጀምራ ነበር። የህክምና ክትትል ታገኛለች። ልጁዋም በህጻናት መዋያ ትምህርቱን መከታተል ጀምሮኣል።ይሄውም ወጪዎች የሚሸፈንላት ነጻ ከሆነ የክርስቲያን ማህበር ነው።

ከብዙ የህይወት ውጣ ውረድ በሁዋላ በዚህ ዕድል ላይ የምትገኘዋ ሜሪ ለኖርዌይ መንግስት ያቀረበችው የመኖሪያ ጥያቄ ፈቃድ ኣላስገኘላትም። የሜሪ ጉዳይ ኣሳዛኝና ኣወያይ ሆኖኣል – በሃገሪቱ ባሉት ሚዲያዎች። የሰባዊ መብት ተሙዋጋቾች ሜሪና ልጁዋ በኖርዌይ ሆና ህክምናዋን እንድትከታተልና ልጁዋም ትምህርቱን እንዲማር እየወተወቱ ነው። በተጉዋዳኝ የኖርዌይ መንግስት ”ወደ ጣሊያን ሜሪን ካላኩዋት – ሞቼ እገኛለሁ” እያለ ነው።
በኖርዌይ ያሉት የሰብኣዊ መብት ተሙዋጋቾች ለሜሪ እንደቆሙት ሁሉ፣ በዓለም ላይ የምንገኝና ይሄን የምናነብ ”ሜሪና ልጁዋ ከኖርዌይ እንዳይወጡ” በሚለው ”ፒቲሽን” ላይ ፊርማችንን እናኖር ዘንድ ስንጠይቃችሁ በታላቅ ትህትና ነው። ሜሪና ልጁዋ የመቶ ሺ ሰው ፊርማ ካገኙ ኖርዌይ የመቅረት ዕድላቸው የሰፋ ነውና። ለወገን ደራሽ ወገን ነው። በፊርማዎት የሰው ህይወት ይታደጉ ! ቀጥሎ ያለውን ይጫኑና ፍርማዎትን ያኑሩ።

https://secure.avaaz.org/en/petition/Utlendingsnemnda_UNE_Espen_Slettmyr_Let_Mary_stay/?tJDpthb

Facebook : Click to share this petition on Facebook

 

Filed in: Amharic