የአፋሕድን የዲያስፖራን ታላቅ የድጋፍ መሰረት የናዱት ሰርጎ ገቦቹ ብአዴናዊያን
– ዛሬም አይናቸውን በጨው አጥበው በ “አንድነት ” ስም ሕዝባችንን ለመጋጥ እያቆበቆቡ ነው!!!
እርሳቸውን በ Bad and Negative Reputation ያስተዋወቁት አፍቃሬ ብአዴናዊያን በአፋሕድ ስም እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ የ 2017 ውድቀት በ2018 እንዲደገም መፍቀድ ማለት ይሆናል!!!
አፋሕድ አዳዲስ ፊቶችን ወደ ፊት ይምጣ!!!
ጋዜጠኛ ወንድወሰን ተክሉ
የዲያስፖራው አማራ ለአፍቃሬ ብአዴንና የብአዴን ተልእኮን ይዞ በእውነተኛ ታጋዮች ላይ ለዘመቱት የፖለቲካ ጊንጦች ቅንጣት የሚሰጠው እድል የለም፣ አይኖርምም!!!
አማራዊ አንድነት የእውነተኛ አማራዊያን ህያው መሰባሰቢያ እና የማሸነፊያ ኃይል ነው እንጂ – አማራዊ አንድነትን የመፈረካከሻ መዶሻ ሆና ፈጽሞ አያገለግልም።
ይህ ቡድን – ሀፍርት፣ ይሉኝታና ሞራል የለሹ ቡድን ላለፉት ስድስት ወራት አፋሕድን ድጋፍ አልባ አድርጎ እርቃኑን በማስቀረት ደረጃ ስኬታማ የሆነ የጠላትን ስራ የሰራ አይን ያወጣ ሰርጎ ገብ ብአዴን ነው። ይህ ቡድን ብአዴናዊ ተልእኮን ይዞ በአፋሕድ ውስጥ ሰርጎ በመግባት የአፋሕድን የዲያስፖራን የድጋፍ መሰረት ፍጹም በመናድ – ባለፈው ሀምሌ በሲያትል በተደረገው የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጲያዊያን አመታዊ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ አዳራሽ ተከራይቶ ብቻውን አዳራሹን ታቅፎ አፋሕድን እርቃን ያስቀረ የጠላት የትሮዣን ፈረስ የሆነ ቡድን ነው።
ይህ የጠላታችን ብአዴን የትሮዣን ፈረስ የሆነው እና የከሀዲ ባንዳዎቹ የእነ ጸዳሉ ደሴን ክህደት፣ የሰርጎ ገቡን መስፍን ከፈለኝን ከአብዱ ሁሴን ጋራ ምስጢራዊ ግንኙነትን አሳላጭና አጀጋኝ ቡድን ከወራት ደብዛው መጥፋት በሃላ እረሳስቶ በቅዱሳዊው አንድነታችን ስም – ያለ አንዳች ሀፍረት ብቅ ብሎ መርዛማ ተልእኮ ውን ለፈጸም አንገቱን ቀና ያደረገ የፖለቲካ ጊንጥ ቡድን ነው።
በእውነተኛ የአፋሕድ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ስለአፋሕድና ብሎም ስለነገደ አማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ብሎ አብሮ መስራት ያልቻለው ጎጠኛው ቡድን ቅዱሳዊውን እና የማሸነፊያችን ሀይል ምንጭ በሆነው አንድነት ስም ብቅ ብሎ ማየት እጅግ ጸያፍና አሳፋሪ ቢሆንም ቡድኑ ግን ሞራል የለሽ፣ ህሊና ቢስ ጥቅመኛ እና እራሱን ለአለቃው ያስገዛ ጎጠኛ ከመሆኑ አንጻር ተረሳስቶልኛል በሚል ቁንጽል ስሜትና እምነት አንገቱን ብቅ ሲያደርግ ልናይ ችለናል።
አፋሕድ – እንደ ድርጅት – ይህንን ማረቅና ማስተካከል ያለመቻሉ ጉዳይ ድርጅታዊ ክሽፈትን የሚያረጋግጥልን ሲሆን በተጨማሪም ድርጅቱ ምናልባትም በዚህ ሰርጎ ገቡ ብአዴናዊ ወካዮቹ የበላይነት ሆስቴጅ ስር የወደቀ መስላል።
እናም ዛሬም እውነተኛ ደጋፊዎችን በትነውና በታትነው አፋሕድን በዲያስፖራ ደጋፊና ተወካይ አልባ ያደረጉትን እነዚህን ምንደኞችን ዳግም በአንድነት ስም እንዲንቀሳቀሱ መፍቀዱ ድርጅቱ ከውድቀቱ ሊማር ያለመቻሉ እና ለመማርም ፈቃደኛ ያለመሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው።
ለምንድነው አፋሕፍ እንደ ድርጅት በዲያስፖራው አማራ ማንነታቸው ተጋልጦ ተተፍተው የተባረሩትን ሰርጎ ገብ ብአዴናዊያንን በስሙ ሲንቀሳቀሱ በዝምታ የሚያየው??።
የእነዚህ ሰርጎ ገቦች የስድስት ወር እንቅስቃሴ የአፋሕድን የዲያስፖራን የድጋፍ መሰረት በመናድ ደጋፊ አልባ ማድረጋቸውን እያየ፣ በሲያትሉ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ባዶ አዳራሽ ታቅፈው እርቃናቸውን መቅረታቸውን እያየ ስለምንድነው በስሙ ሲንቀሳቀሱ በዝምታ ለማየት የወደደው?? ይህ ህመም ካልሆነ በስተቀር ጤናማነት አይደለም።
ሌባም ሆነ ሰርጎ ገብ ብአዴን እኔ እስከፈለግኩት ድረስ ዲያስፖራው ቢቃወመውም ስለድርጅቴ ይንቀሳቀሱልኝ ብሎ ማሰብ ድርጅታዊ ኪሳራን ፣ቅንጣት መቀራረብን እና የሚፈለገውን የ Mass mobilization የድጋፍ ማሰባሰቡን ስራ በአግባቡ እንዲያሳልጥ የሚያስችል አይደለም።
ይህ ሰርጎ ገቡ ብአዴናዊ ቡድን ባለፈው ሀምሌ የሲያትሉ ፌስቲቫል ላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ ከታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ጨምሮ ሁሉንም የአፋሕድ እመራሮችን በቲክቶክና በሚዲያ እያቀረበ ጥሪ እንዲያደርጉ ቢወተውትም በዲያስፖራው ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በሆነ ታላላቅ መሪዎች ጥሪ አድርገው አንዳችም ሰው ባለመገኘት ባዶውን የቀረበትን ክስተት ካስተዋልን Just ሁለት ወር ቢሞላን ነው። ታዲያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተከስቶ ነው በእነዚሁ ተመሳሳይ ሰዎች ፣ ተመሳሳይ አንደበት አንዳችም የሆነ የአካሄድ፣ የአነጋገር እና የአቃም ለውጥ ሳያደርጉና አንዳችም የሆነ አዳዲስ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሳይታከልበት በአንድነት ስም ብቅ ለማለት የቻሉት????
በተመሳሳይ መንገድ እየተጋዙ የተለየ ውጤት መጠበቅ የድንቁርና መገለጫ ነው። ይህ ቡድን ከአፋሕድ እውነተኛ ደጋፊ እና አባላት ጋር ይዞት በመጣው ብአዴናዊ ተልእኮ ምክንያት አብሮ መስራት አቅቶት የተነጠለና በዲያስፖራው አማራ ተወግዞ አይንህን ላፈር የተባለ ቡድን ዛሬ በምን ሞራል ነው ስለ አንድነት የሚያወራው ሳይሆን ዛሬ ከየትኛው አማራ ጋር ነው ስለ አንድነት የሚያወራው ተብሎ ቢጠየቅ የሚኖረው መልስ የሰሞኑ የፖለቲካ መንፈስ የአንድነት ጥሪ ስለሆነ እኔ ያው የምታውቁኝ ብሆንም በአዲሱ አንድነት ስም እኔን የማያውቁትን ማሰባሰብ ከቻልኩ ብዬ ነው አንድነትን ቃል የተጠቀምኩት ብሎ እንደሚመልስልን ግልጽ ነው።
ይህ ውንብድና መቆም አለበት። የዲያስፖራው አማራ አንዴ ብአዴናዊ ማንነቱን ላወቀ ሰርጎ ገብ ልቡን መልሶ የሚሰጥ አማራ አይደለም። በዚሁ አጋጣሚ ይህ ጸሀፊ መግለጽ የሚወደው ሰሞኑን በአርበኛ ዘመነ ካሴ በኩል የተላለፈን የአንድነት ጥሪን ሀሳብ ተከትሎ በተለያዪ መድረኮች ላይ ይህንን የአንድነቱን ሀሳብ ጉዳይ ላይ ውይይት ሲያደርግ ከ90% በላይ የሆነው የአማራ ዲያስፖራ የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች አንድነ ለጥያቄ የማይቀርብ ብቸኛ የማሸነፊያችን ሀይል ነው፣ ሆኖም አርበኛ ዘመነ ካሴን ለአንድነቱ እንቅፋትና ተግዳሮት ሆኖ ያየነው ስለሆነ ዛሬ ላይ ለማመን ይቸግረናል፣ አናምነውም የሚሉ አስተያየቶች መሆናቸውን ማስተዋሉን ለመግለጽ ይወዳል።
ይህ ማለት Your Reputation matters a lot ማለት ነው።
በአፋሕድ ውስጥ ሰርገው የገቡት እነዚህ አፍቃሬ ብአዴናዊያን Reputation ምንድነው ብለን ብንመለከት የምናገኘው ቡድኑ በአፋሕድ እውነተኛ ደጋፊዎች ላይ ዘመቻ መክፈት፣ የጎጥ መንፈስ የበላይነትን ለማስፈን መጋጋጥ፣ ለከሀዲ ባንዳዎች እነ ጸዳሉ ደሴ ጥብቅና መቆም፣ ክህደትን ማጀገን እና በዲያስፖራ ሆኖ ለአፋሕድ የ Reforum ሰነድ አዘጋጅቶ የ Leadership Reshuffle አላማን ለማሳካት በታላቁ አርበኛ እስክንድር ነጋ ላይ ከሀላፊነት ተነስታል እና መሰል የሆኑ ጠላታዊ ስራዎችን በመስራት ነው Reputation የገነባው።
እናም ዛሬ በዚህ ጸረ አንድነት ፣ ጸረ አማራዊ ብሄርተኝነት በሆነው Reputation የሚታወቀውን ቡድን ዳግመኛ በአንድነት ስም ስለ አንድነት እንዲቃትት መፍቀድ ማለት ድርጅቱ ምን ያህል ቅርቃር ውስጥ እንደገባ ከማሳየት የዘለለ ዲያስፖራው የሰርጎ ገቦቹን ስራና ተግባር ዘንግቶ ፊቱን ያዞርልናል ብሎ ማሰብ እጅግ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።
አፋሕድ በ 2017 ያጋጠመውን ውስጣዊ ስብራትና ጉዳት በአዲሱ 2018 አመት እንዳይቀጥል ከፈለገ ይህንን ማስተካከል የቅድሚያዎች ሁሉ ቅድሚያ ሰጥቶ ማስተካከል ይጠበቅበታል። አፋሕድ የብዙ ደጋፊዎችና አባላት ባለቤት እንደመሆኑ መጠን ምንም አይነት Bad and Negative Reputation Built ያላደረጉ አዳዲስ ፊቶችን ወደፊት ለማምጣት የሰው ሀይል እጥረት የሌለው ድርጅት እንደመሆኑ መጠን እራሱን ከእነዚህ ጋር አጣብቆ የዲያስፖራ መሰረቱን ድጋፍ አልባ ከማድረግ በአዳዲስ ሰዎች በመተካት ድጋፍ የማሰባሰቡን እና ደጋፊን Mobilization ስራን በአግባቡ ማሳለጥ ይጠበቅበታል። ለዲያስፖራው ብሎ ሳይሆን ለራሱ ብሎ ይህን መፈጸም ይገበዋል። አበቃሁ።