>

ወያኔ ሳይለወጥ ከወያኔ ጋር ተባብራችሁ ለመሮጥ ለተነሳችሁ ለሌሎች የፖለቲካ ሀይሎች ጥብቅ ማሳሰቢያ

ወያኔ ሳይለወጥ ከወያኔ ጋር ተባብራችሁ ለመሮጥ ለተነሳችሁ ለሌሎች የፖለቲካ ሀይሎች ጥብቅ ማሳሰቢያ:-

  • ይድረስ ለወያኔ አመራሮች

    ወያኔዎች ኢትዮጵያን በማዳን ላይ የመሳተፍ እድል እግዚአብሄር ሊሰጣችሁ ፈቃዱ ነዉ::ግን ቀድማችሁ የሚከተሉትን ሶስት ቅድመ ሁኔታዎችን ማድረግ ይጠበቅባችኋል?

    ሸንቁጥ አየለ

    1. የካዳችሁትን ኢትዮጵያዊነት : በሀሰት የረገማችሁትን : የከሰሳችሁትን ኢትዮጵያዊነት እንዲሁም በጠላትነት የተነሳችሁበትን ኢትዮጵያዊነት ይቅርታ መጠዬቅና ተሳስተን ነበር ብላችሁ በአዋጅ ስህተታችሁን ማመን ግዴታችሁ ነዉ:: እንዴት ?

     

    ሀ. ኢትዮጵያዊነት የተፈጠረዉ በቅኝ ግዛት ነዉ::

    ኢትዮጵያዉያን ምንም የታሪካዊ ትሥስር እና የጋራ መሰረት የሌላቸዉ ህዝቦች ናቸዉ:: በአማሮች በጉልበት እና በሀይል የተሰበሰቡ ህዝቦች ናቸዉ ብላችሁ በማኒፌስቷችሁ ጽፋችኋል:: በፕሮፖጋንዳ ኢትዮጵያዉያንን አሳስታችኋል:: በዚህም የራሳችሁን ጥንታዊ የኢትዮጵያዊነት ታሪክ ክዳችሁ ይሄንኑ ክህደት ከኦነግ/ኦህዴድ/ብአዴን/ኢህአዴግ/ደህዴን እና ልዩ ልዩ ምናምንቴ የጎሳ ፖለቲካ ሀይሎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ጥንታዊ ህዝብነት ነጥቃችሁት ኖራችኋል::

ይሄም ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በርሱ በጎሳ ተከፋፍሎ እንዲጫረስ የተረት ተረት ክልሎችን ፈጥራችሁ ኢትዮጵያዉያንን ነገዶች እርስ በርስ እንዲጫረስ ብዙ ሰርታችኋል::በተለይም አማራን ለመጉዳት በማስላት እና በማቀድ የሀሰት እና ፈጽሞ በተንኮል ላይ የተቀመረ ስትራቴጅ በመንደፍ ኦሮሚያ የሚባል የተረት ተረት ክልል ፈጥራችኋል::

ይሄም ሳይበቃችሁ በፈጠራችሁት ኦሮሚያ የሚባል የተረት ተረት ክልል የሚኖሩ ሌሎች ነገዶችን ሁሉ መጤ እና ወራሪ ናቸዉ በማለት እንዲታረዱ አድርጋችኋላ::እስካሁንም የቀጠለዉ ይሄዉ ነዉ::አንዳንድ ሰዉ የሚመስለዉ በኦሮሚያ ቄሮ የሚባለዉ አራጅ በኦህዴድ/ኦነግ የተደራጀ ጥላቻ የተጋተ ይመስለዋል::ሆኖም ዋናዉን መሰረት የጣላችሁት እና በሀሰት ጥላቻን የመገባችሁት እናንተ ናችሁ::ሁኔታዎችንም የተረት ተረት ክልል ፈጥራችሁ ያመቻቻችሁለት እናንተ ናችሁ::

ለ. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለዉ ወንጀል ሰርታችኋል::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያን ከአማራ ጋር ተባብራ በቅኝ ግዛት የፈጠረች ናት:: ወራሪና ጨቋኝ ናት ብላችሁ ተዋህዶ ከኢትዮጵያ ህዝብ ልብ እንድትፋቅ ሰርታችኋል::ተዋህዶ እንድትዋረድ እና እንድትኮሰምን በተቃራኒዉ ደግሞ ተዋህዶን ይቃወሙልናል የምትሏቸዉን ሌሎች እምነቶች እንዲፋፉ ሰርታችኋል::ተዋህዶን የሚከተል እዉነተኛ አማኝን ከመሃከላችሁ አጥፍታችኋል::ልክ እንደ ደርግ ኮሚኒስት ሌላዉ ቀርቶ ከመሃላችሁ ከወያኔ ውስጥ አንድም የተዋህዶ አማኝ ባለስልጣን ወደ ቤተክርስቲያን ዝር እንዳይል አድርጋችሕውል::

ይሄ አሰራራችሁም ከስልጣን እስከተባረራችሁበት ዘመን ድረስ ጸረ ተዋህዶ ፖሊሲ ስታራምዱ በፖሊሲ ትንታኔአችሁም ተዋህዶን ስትከሱ ኖራችሁ ነበር:: ተዋህዶ ላይ የተለያዩ የሀሰት ጥናቶችን እያቀረባችሁ ተዋህዶ የልማት እንቅፋት ናት የሀገር ሸክም ናት የቅኝ ግዛት ምንጭ ናት በሚል ስትከሷት ነበር::

ሆኖም ከስልጣን ስትባረሩ ግን አሁን አሁን በትግራይ ገዳማት ካባ ለብሳችሁ እንደ ክርስቲያን በዬመድረኩ የምትታዩ በመሆን ታጭበረብራላችሁ::አሁንም ቢሆን ግን እናንተ በፈጠራችሁት የዘር ፖለቲካ የኮሰመነችዉን የኢ/ኦ/ተ ኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተክርስቲያንነንድትከፋፈል ትግራይ የብቻዋ ሲኖዶስ እንዲኖራት ሰርታችኋል::ያዉ ሰይጣኑ እንደሰፈረባችሁ ነዉ::ያደቆነ ሰይታን ሆኖባችሁ ኦርቶዶክሳዉያን እንዲከፋፈሉ አሁንም የኦሮሚያ ቤተክርስቲያን የትግራይ ቤተክርስቲያን የሚል የሰይጣን ሀሳብ ደጋፊ ሆናችሁ ተነስታችኋል::እናንተ ያጠፋችኋትን የኢ/ኦ//ተ ቤተክርስቲያን ያለ ርህራሄ መልሳችሁ ትከሷታላችሁ::

ሐ. ነገደ አማራን ለማጥፋት የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኋል::

የአማራን ነገድ ለማስጠላት:ለማስጨፍጨፍ :ለማፈናቀል ማኒፌስቶ ቀርጻችሁ; ህገመንግስት ጽፋችሁ እና የፖለቲካ ስትራቴጅ ነድፋችሁ ሰርታችኋል::በኢትዮጵያ በህዝብ ቁጥር በዉህደት እና በባህላዊ ተሳልጦ ብሎም ለኢትዮጵያ አንድነት እሴታዊ መሰረቱ ታላቅ የሆነዉን የአማራ ነገድ በማስጨፍጨፍ: በማፈናቀል:የስነልቦና ሰበራ በማድረግ : በ86ቱም ነገዶች እንዲጠላ በሀሰት የመርዛማ ጸረ አማራ ፕሮፖጋንዳ በማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጋችኋል::

እንቅፍ ሳይወስዳችሁ ሰርታችኋል::አማራ ሀገር እንዳይኖረዉ ከአባቶቹ ምድር ሁሉ መጤ ተብሎ እንዲፈናቀል በብዙ መልክ ሰርታችኋል::አማራን አናሳ ነገድ ለማድረግ ከመላዉ አለም ያገኛችሁትን የልማት ገንዘብ እርዳታ ሁሉ ተጠቅማችሁበታል::ሌላዉ ቀርቶ በርዳታ የምታገኙትን ገንዘብ ምነዉ ቆመንለታ ለምትሉት ነገድ ልማት ብታዉሉት ኖሮ ብዙ ይጠቅም ነበር::እናንተ ግን ገንዘቡን ጸረ አማራ ፕሮፖጋንዳ እና ጥቃት ለማድረግ የሀሰት ክልል ከመፍተር እስከ ሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ብሎም እስከ አካላዊ የዘር ማጥፋት ስራ ሰርታችኋል::

2. የፖለቲካ ርዕዮተ አለም ለዉጥ የግድ ማድረግ ይጠበቅባችኋል:: የወያኔ የፖለቲካ ርዕዮተ አለም አሁን ድረስ ተሸልመዉት በሚዞሩት ማኒፌስቷቸዉ ላይ የቆመ ነዉ::ይሄም ማኒፌስቶ ከላይ እንደተጠቀሰዉ ኢትዮጵያን ረግሞ:አማራን መጥፋት አለበት ብሎ : ኦርቶዶክስን የጠላት ሀይማኖት አድርጎ የተነሳ ነዉ::

የአሁን ያለዉ የኢትዮጵያ ህገመንግስት የሚባለዉን ህገመንግስትም ወያኔ የቀረጸዉ በዚሁ ሀሰተኛ ማኒፌስቶ ላይ በመቆም ሲሆን : የጎሳ ክልሎችንም ሲሸነሽን የጎሳ ክልሎሎቹ መሰረት ይሄዉ የወያኔ ማኒፌስቶ ነዉ::

ይሄን የወያኔን ርዕዮተ አለም በሚገርም መልኩ ከትግራይ የወጣ አንድም ጳጳስ ወይም የሀይማኖት ሰባኪ ሲያወግዝና ልክ አይደለም ይስተካከል ሲል አይደመጥም:: ይሄም በጣም አሳዛኙ ነገር ነዉ:: እዚህ ጋ የትግራይ ምሁር የሚለዉን መጥቀስ አያስፈልግም::

ምክንያቱም የትግራይ ምሁራን የመንፈሳዊ ልብሳቸዉ አዉልቀዉ በወያኔ ፕሮፖጋንዳ የህሊና እጥበት የተደረገባቸዉ ስለሆነ ይሄን ቁም ነገር ለማስተዋል እና ለመተቸት የተቸገሩ ብቻ ሳይሆን የወያኔን ማኒፌስቶ እንደ እዉነት መሰረት የተቀበሉ ስለሆነ ነዉ::እርርስ በርስ ሊታሉ ይችላሉ እንጂ ወደ ግራም ሆነ ወደ ቀን ዞረዉ የሚያርፉት እዚያዉ የወያኔ ማኒፌስቶ ህሳቤ ላይ ነዉ::

በደንብ ለሚያስተዉል ግን ይሄ የወያኔ የፖለቲካ ርዕዮተ አለምም ለጠቅላላ ኢትዮጵያ መጥፊ ብሎም ለትግራይ ህዝብ ፍጅት መነሻ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል:: ወደፊት ደግሞ የከፋ የኢትዮጵያ ህዝብ የእርስ በርስ መተላለቂያ የሚሆን ነዉ:: በተለይም ትግራይ ላይ ለሚመጣዉ መከራ ሁሉ ምንጭ ይሄዉ የወያኔ ማኒፌስቶ ይሆናል::

ስለሆነም ወያኔ የፖለቲካ ርዕዮተ አለሙ መሰረቱን እንደሚከተለዉ ማስተካከል ይኖርበታል:: እናት ሀገር ኢትዮጵያ :ሀይማኖታችን ተዋህዶ በሚል ህሳቤ መተካት ይኖርበታል::በተያያዥም የትግራይ ህዝብና የአማራ ህዝብ አንድና ወንድማማች ነዉ በሚል ርዕዮተ አለም ማንበር ይጠበቅበታል::ይሄንንም በተጻፈ እና በአደባባይ በሚሰበክ በሰነድ በተደገፈ እንቅስቃሴ መተግበር ይጠበቅበታል።
• • •

3. የጎሳ ፖለቲካ ከሀገሪቱ በህግ እንዲታገድ በዚህ ሀሳብ ከሚስማሙ ልዩ ልዩ ኢትዮጵያዊ ሀይሎች ጋር መወገን ብሎም ኢትዮጵያ ነጻ ሀገር እና የህግ የበላይነት የሰፈነባት ህዝቧም አንድ እና የተከበረ ህዝብ እንዲሆን መስራት

የትግራይ ህዝብ እፎይታ አግኝቶ ሊኖር የሚችለዉ ኢትዮጵያ እፎይታ ያገኘች እንደሆነ ብቻ መሆኑን ወያኔዎች እየመረራቸዉም ቢሆን መዋጥ አለባቸዉ::ትግሬ አልፎለት ፈጽሞ ሌላዉ ግን ተብድሎ ምድሪቱ አትረጋም::ወይም ደግሞ ሌላዉ ነገድ ሁሉ እኩል እፎይታ ሳያገኝ ትግሬ ብቻዉን ሊያርፍ አይችልም::

በሌላ አገላለጽ የሀገር ካንሰር የሆነዉ የጎሳ ፖለቲካ ህሳቤ እንደሚለዉ ዲሞክራሲን እና ብልጽግናን ለኦሮሞ ብቻ:ነጻነትን ለትግሬ ብቻ የሚለዉ ሸፋፋ ህሳቤ የትም አያደርስም::

ማንም ኢትዮጵያ ሳትድን የሚድን የለም:: አማራም ኢትዮጵያ ሳትድን አይድንም::ትግሬም ኢትዮጵያ ሳትድን አይደንም::ኦሮሞም ኢትዮጵይ ሳትድን አይደንም::ኦርቶዶክሱም:እስላሙም:ፕሮቴስታንቱም ወይም በጠቅላላ አነጋገር ኢትዮጵያ ሳትድን የሚድን ነገር አይኖርም::

ኢትዮጵያ ስታርፍ እና ስትድን ሁሉም ይድናል::ስለሆንም ሁሉ የፖለቲካ ሀይሎች የሚሰሩት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆን ይኖርበታል::ይሄም ማለት የጎሳ ፖለቲካ በህግ መታገድ ይኖርበታል::ወያኔም የአስተሳሰብ ለዉጥ በማድረግ የጎሳ ፖለቲካ በህግ እንዲታገድ የራሱን አበርክቶ ለማድረግ መነሳት ይኖርበታል::

መደምደሚያ:-

የበደሉትን:የካዱትን የናቁትን ያጠፉትን ሁሉ ይቅር ብለዉ ወደ ቀልባቸዉ በመመለስ የዘሩትን የጎሳ ፖለቲካ በእግራቸዉ ረግጠዉ በአንደበታቸዉ ረግመዉ ኢትዮጵያዊነትን ተቀብለዉ ብሎም ለኢትዮጵያዊነት ለመታገል የተነሱ እንደሆነ ወያኔዎች ኢትዮጵያን በማዳን ላይ የመሳተፍ እድል እግዚአብሄር ሊሰጣቸዉ ፈቃደኘ ይሆናል::

ይሄ በምን ይታወቃል ቢሉ እግዚአብሄር እዉነትን የሚወድ የሰዉ ልጆችን እና አንድነት የሚናፍቅ እና በሰዎች መሀከል ወንድማማችነትን ለማዬት አብዝቶ የሚዋትት ብቻ ሳይሆን ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ እራሱን በቀራኒዮ መስቀል ላይ እስከ ማዋል የተራመደ ነዉና::

የጎሳ ፖለቲካ በነገዶች መሃል እልቂት ለመፈጸም የሚጠቀምበት አንዱ የዲያቢሎስ መሳሪያ ሲሆን የአንድነት ፖለቲካ ግን በሰዉ ልጆች መሃል ፍቅር እና እኩልነት እንዲፈጠር እግዚአብሄር የሚሰራበት/የሚፈቅደዉ መንገድ ነዉና::

ወያኔ ሳይለወጥ ከወያኔ ጋር ተባብራችሁ ለመሮጥ ለተነሳችሁ ለሌሎች የፖለቲካ ሀይሎች ጥብቅ ማሳሰቢያ:-

ወያኔዎች ስህተታቸዉን ሳያርሙ: አሁንም በቀደመ ማኒፌስቷቸዉ እየተመሩ: ከወንጀላቸዉ ሳይጸዱ : ማኒፌስቷቸዉን በአደባባይ እንደ አዲስ ሳያዉጁ :የበደሉትን ይቅርታ ሳይጠይቁ እና የቀበሩትን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማዳን ሳይወስኑ የጠላቴ ጠላት በሚል መርህ አብራችሁ እሮጣችሁ የምትገኙ ሁሉ በወያኔዎች የሀጢያትና የወንጀል ወጥመድ ትያዛላችሁ::

እግዚአብሄር በሀጢያት በተያዘ ሀይል ሀገር አያድንም::ህዝብን አያድንም::ጠላትንም አያጠፋም::እናም ንሰሃ ገብቶ እራሱን ካላስተካከለዉ ወያኔ ጋር የምትተባበሩ እና የምትሮጡ ሰዎች ቆማችሁ እንድታስቡ ይሁን::

እንቢ ካላችሁ ግን ምርጫችሁ ያወ ከወያኔ ጋር አብሮ መጥፋት መሆኑን እወቁት::ምናልባትም እናንተን ወያኔ ቀድሞ ሊያጠፋችሁም ይችል ይሆናል:: በሌላዉ ሀጢያት ዉስጥ ገብታችኋል እና::ወገን እና ህዝብ ለማዳን ከሀጢያተኞች እራቁ::

ከእዉነተኞች ተባበሩ::ስልጣንን መመኘትን እና ጎተኝነትን ተዉ:: የግል ዝናችሁን ወደጎን ብላችሁ ህዝቡ የሚድንበት ጉዳይ ላይ ብቻ አተኩሩ::ከሁሉም. በላይ ግን ምንም ቢሆን በሃጢያት ከተያዘዉ ወያኔ ጋር አትተባበሩ::

 

Filed in: Amharic