ከይኄይስ እውነቱ
ኢትዮጵያን ከሚያፈርስ እና ሕዝቧን ቁም ስቅል ከሚያሳይ አገዛዝ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ የሚሠራ ለዚሁ አፍራሽ ዓላማ የተቋቋመ ድርጅት‹‹ኢትዮጵያ›› የሚል ክቡር ቅፅል ሊሰጠውም አይገባም፡፡ ከመነሻውም የተለያየ ‹ሃይማኖት› በእምነት ጉዳይ የአንድነት ጉባኤ ሊኖረው አይችልም፡፡ ጨለማ ከብርሃን ጋር ኅብረት ሊኖረው አይችልምና፡፡ ክርስቶሰ ከቤልሆር ጋር መስማማት እንደሌለው ሁሉ፡፡ ስለዚህ ተቋም ከዚህ ቀደም ብዙ ተብሏል፡፡ አካፋን አካፋ ማለት ተገቢ ነው፡፡ እንኳንይሄ ‹‹ጸጕረ ልውጥ›› ተቋም ይቅርና የጥንቶቹም የእምነት ተቋማትበአገዛዙ ቊጥጥር ሥር ከዋሉና ዓላማቸውን ከሳቱ ዘመናትተቆጥረዋል፡፡ ቢያንስ በማውቀው በኢኦተቤክ አብዛኛው ‹አገልጋዮቹ› የዓላውያን አገዛዞች ሎሌዎች ሲሆኑ፣ እንደ ዴማስ ሆዴ ይሙላ ደረቴይቅላ ብለው÷ ደንደስ አበጅተው በሥጋዊ ምቾት የሚቀማጠሉ፣ የክርስቶስን መንጋ በትነው ለ‹አውሬ› አሳልፈው የሰጡ፣ ሰማይ ሩቅአደራ ጥብቅ ተብለው ከእረኞች አለቃ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ቊርጥም አድርገው የበሉ የአምልኮ መልክ እንጂ መንፈሳዊነት የሚባልየሌለባቸው በቀሚስና ካባ ውስጥ የተደበቁ ምእመኑን ለማይነጥፍገንዘቡ ብቻ የሚፈልጉ ‹ጸሐፍት ፈሪሳውያን› መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ‹‹የሃይማኖት ጉባኤ›› የተባለው ድርጅት የውሸትየፖለቲካ ማኅበር አቋቁሞ ለፈረንጆቹ ፍጆታ ለላንቲካ ለሚደረገው‹‹ምርጫ›› የርጉም ዐቢይ አጃቢ ሆኖ ቢሳተፍ ይሻለው ነበር፡፡ እንዲህማፈሪያ የሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት እንደ አሸን የፈሉበት ዘመን ላይመድረሳችን በራሱ መረገም ነው፡፡ ይሄ ድርጅት በምን የሞራል ልዕልናነው አገራዊ ምሕላ የሚጠራው? እነማንን ነው የሚጠራው? ኧረእባካችሁ ይሄ ፌዝ ይቁም! የኢኦተቤክ ምእመናን! ከዚህ ቀደም አገዛዙበተቆጣጠረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ከሥርዓት የወጣግርግር አታስታውሱም? እነርሱ ከፈለጉ አገዛዙ አገርን ማፍረሱን፣ ደሀመበደሉንና ፍርድ ማጉደሉን ቀጥልበት ብለው ይለምኑለት፡፡ እኛየተዋሕዶ ልጆች ግን የዚህ የቤልሆር ጉባኤ እድምተኞች መሆንየለብንም፡፡
በመጨረሻም ቊጥራችን ቀላል የማይበል የኢኦተቤክ ምእመናንእስከ መቼ የበዓል ክርስቲያን ሆነን እንዘልቃለን? እስከ መቼ ለዓላውያን ያደሩ ሐሰተኛ ‹አገልጋዮች› ተገዢ ሆነን ራሳችንን እናታልላለን? በዚህበከፋ ኑሮ እስከ መቼ ለፍተን ያገኘንውን ገንዘብ ለካድሬዎችና ለሌቦችእያስረከብን ‹‹እልል እያልን እና እያጨበጨብን›› እንቀጥላለን? አንዳንዱም በዘረፈው ገንዘብ የኀጢአት ስርየት የሚያገኝ እየመሰለውራሱን እስከ መቼ ያታልላል? ለቤተክርስቲያን እያላችሁ የምትሰጡትገንዘብና ማናቸውም ሥጦታ የጣዖት አምላኪዎች ለሆኑት፣ እውነተኛ አገልጋዮችን÷ መነኮሳትን÷ የአብነት መምህራንንና (ሊቃውንትን) ተማሪዎች እና ምእመናንን በጠራራ ፀሐይ በግፍ ላስገደሉ፣አድባራትንና ገዳማትን እስከነ ቅርሶቻቻ ላወደሙ ለርጉም ዐቢይናየታማኝ ተላላኪው አዳነች አበቤና ግብር አበሮቻቸው ኪስ እንደሚገባ ታውቃላችሁ? የኢትዮጵያ ምእናን ለመሆኑ እንዳታስተውሉ ማን አዚምአደረገባችሁ? የኢኦተቤክ በቅጥረኝነትና በካድሬነት ያሰማራቸውሐሳውያን ‹አገልጋዮች› ታላቁ የድኅነት ቀን ስቅለተ ክርስቶስን እንኳንመታገሥ አቅቷቸው ጥቂት የማይባሉ አድባራትና ገዳማት በዓመትአንዴ የሚፈጸመው የግብረ ሕማሙ ልዩ የጸሎት ሥርዓት ተቋርጦለ‹ገንዘብ ዝርፊያ› የሚውል የቴሌቶን ቀን ካደረጉት ከራርሟል፡፡በእጅጉ ያሳዝናል፤ ያማልም፡፡ በራሳችን ሥርዓትና እውነተኛ አባቶችመሪነት ያላደረግነውን ጸሎተ ምሕላ ርጉም ዐቢይ ባሰማራቸው ሎሌዎች አማካይነት ማድረግ የምንችል ይመስላችኋል? እንደባለአእምሮ እንመላለስ፡፡























