አሥራደው ከካናዳ
ጊዜ ሰጠኝ – ብሎ የሚጀነን፤ ውስተጠ ቀፎ – አምባነን፤ ያንን_ ግረፈው ! እሱን_ እሰረው ! ይህን_ ግደለው ! እነዚያን_ አሳዷቸው ! እነዚህን_ ግፏቸው ! እነሱን_ እሰሯቸው ! ብሎ የሚያዝ – የሌለበት፤ ዘበኛ_ ! ጠባቂ ያልቆመበት፤ ናፈቀኝ የማይበት – የተዘጋ ወህኒ ቤት ::
እነዚህ የእኛ ናቸው – አትንኳቸው ! እነዚያን ግፏቸው – አሳዷቸው ! እነሱን አስርቧቸው – ግደሏቸው እነዚህን ወህኒ ቤት – ክተቷቸው፤ ብሎ የሚያዝ – የሌለበት፤ ጊዜው ናፈቀኝ – የማይበት፤ የተዘጋ ወህኒ ቤት፤ በአገሬ_! በኢትዮጵያ መሬት ::
አምባ ገነን አሳሪ – ገዳይ ገራፊ፤ የሰብዓዊ መብት – ገፋፊ ፤ አገር_ ! እየዘረፈ – የሚያዘርፍ፤ ህዝብ በርሃብ – የሚያረግፍ፤ ወገን ከወገን – ደም የሚያፋስስ፤ ህዝብ የሚያባላ – የሚያጫርስ፤ ናፈቀኝ_! ተወግዶ የማይበት፤ የአምባ ገነን ሥርዓት፤ በአገሬ ! – ተወልጄ ባደኩባት ::






















