>
5:13 pm - Sunday April 20, 2988

የካሩቱሪ ቁጣና የህንድ ሃያልነት በኢትዮጵያ፣ [ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም - ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ]

የጸሐፊው ማስታወሻ፡ ይህንን ትችት የጻፍኩት በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት መካከል በጋምቤላ የመሬት ስምምነት ውዝግብ ላይ እየተካሄደ ያለው የሕግ ጉዳይ የሚያሳስበኝ በመሆኑ ምክንያት አይደለም፡፡ ወሮበላ ዘራፊዎች እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ጋር የሚነግዱ አካሎች የገቡበትን ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ ቢፈቱት ወይም ደግሞ ባይፈቱት ጉዳዬ አይደለም፡፡

ሆኖም ግን በካራቱሪ-ዘ-ህወሀት የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አጋጣሚ እንደምታ የደረሰው የውድቀት ቀውስ ጥልቅ በሆነ መንገድ ያሳስበኛል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች የካሩቱሪ ፕሮጀክት በጋምቤላ ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን በሚል ስሌት ከመሬታቸው በኃይል ተፈናቅለዋል፣ እንዲሰፍሩ እና በ”መንደር”  እንዲሰባሰቡ ተደርገዋል፡፡ እራሳቸውን የቻሉት አነስተኛ አምራች ገበሬዎች እና የአርብቶ አደሩ ማህበረሰቦች ከይዞታቸው እንዲነቀሉ እና ወደ አስከፊ ድህነት ውስጥ እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ የምግብ እርዳታ ተመጽዋች  በመሆን ኑሯቸውን እንዲገፉ ተገደዋል (ለማኝ እንዲሆኑ ማለት) ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የካሩቱሪ ፕሮጀክት በመውደቁ እና የማይቀጥል መሆኑ በመታመኑ ከጋምቤላ ዘለቄታዊ በሆነ መልኩ እንዲባረሩ ተደርገው የነበሩት ዜጎች በአሁኑ ጊዜ ያላቸው ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው? በካሩቱሪ ፕሮጀክት ምክንያት ከይዞታ መሬታቸው በኃይል ተፈናቅለው ለነበሩት ዜጎች ምን ዓይነት የመፍትሄ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፣ ወይም ደግሞ እነዚህ ሰዎች እና የስነ ምህዳር ውድመት የደረሰበት አካባቢ እንደገና እንዲያገግም ለማድረግ ምን የተወሰዱ እርምጃዎች እና የታቀዱ ነገሮች አሉ? ለወደፊት በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈስሱ የውጭ ባለሀብቶች የከሰረው እና በቀውስ ባህር ውስጥ ዋኝቶ የወጣው የካሩቱሪ ፕሮጀክት ምን ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ሊያስከትል ይችላል?

በዚህ ትችት በጋምቤላ የቁማር ጨዋታ ላይ ካሩቱሪ እና ዘ-ህወሀት ባጣመሙት እና በገመዱት የሕግ መረብ ላይ ከበርካታ ጉዳዮች መካከል ጥቂቶችን ብቻ አመላክታለሁ፡፡

“እስኪ ትንሽ ንካኝ፣ ከዚያ በኋላ የሕንድን ኃያልነት ታያለህ”

The Wrath of Karuturi and the “Power of India” in Ethiopiaበቅርቡ ለሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ በተደረገለት ቃለ መጠይቅ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን(ህወሀት) በቀጥታ በሚገዳደር መልኩ በንዴት በገነፈለ ስሜት “እስኪ ትንሽ ንካኝ ከዚያ በኋላ የሕንድን ኃያልነት ታያለህ” በማት አውጇል፡፡ ይኸ የወሮበላ ንግግር ትንሽ ብትነካኝ ግንባርህን ነድዬ እጥልሀለሁ ማለቱ ነውን? የማፊያ ዓይነት ስሜትን የሚያንጸባርቅ ንግግር ነው፡፡

ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ የካሩቱሪ ግሎባል ኃላፊነቱ የተወሰነ (Karuturi Global Ltd.) እና እራሱን የዓለም የጽጌረዳ አበባ ንጉስ አድርጎ የሰየመው እንዲሁም “የጋምቤላ አንበሳ” ነኝ የሚለው ድርጅት መስራች እና ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር እንዲህ በማለት አምባርቋል፣ “በኢትዮጵያ የንግድ እርሻ/commercial farming ፈጥሪያለሁ እንዲታወቅም አድርጊያለሁ…በውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች የሚከናወን የንግድ እርሻ የወደፊት ታላቅ የኢንቨስትመንት አማራጭ ተደርጎ አይታሰብም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ካሩቱሪ ይህንን ተግባራዊ ሲያደርግ የመጀመሪያው ነው፡፡“

ወይ ጉድ! ካሩቱሪ እንደ አቡጀዲ እየተቀደደ ነው ወይም ደግሞ ጥንቃቄ የተመላበት ንግግር እያደረገ አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ በንጉሱ ዘመን ጊዜ የንግድ እርሻዎቸ/commercial farms ይካሄዱ ነበር፡፡

ፕሮፌሰር ኤድመንድ ኬለር፣ “አብዮታዊት ኢትዮጵያ፡ ከአገዛዝ ወደ ሕዝባዊ ሬፐብሊክ“ በሚል ርዕስ በጻፉት መጽሐፋቸው ውስጥ ገጽ 127 ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አስፍረዋል፡

“አጼ ኃይለ ሥላሴ የልማት ሂደትን ከላይ ለመጀመር በማሰብ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በመንደፍ በስራ ላይ አውለው ነበር፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች/manufacturing industries እና ለንግድ እርሻዎች/commercial agriculture የተለዬ ትኩረት በመስጠት በተለይ ከውጭ ሀገር የሚመጡትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት/import substitution ዓላማ በማድረግ ምርትን ለማሳደግ ጥረት አድርገዋል…የአጼ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ የንግድ እርሻውን ከፊውዳሉ የምርት ግንኙነት እና መዋቅር ውጭ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት አልነበረም ጥረት ሲያደርጉ የነበሩት፣ ሆኖም ግን በአርሶ አደሩ ላይ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ጉዳት እና አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ እውነት ነው፡፡ የፊውዳሉ ስርዓት ለለውጥ እንቅፋት ስለነበረ ንጉሱ የመጣው ይምጣ በማለት ለንግድ እርሻው ስኬታማነት እስከ መጨረሻው ገፍተውበታል፡፡ ንጉሱ ከዚያ ማግኘት የነበረባቸውን አግኝተዋል፡፡ ምናልባትም ያንን ለማስፈጸም ቀናት አጥረውባቸዋል፣ ችግሩን በአንድ ምት ለመምታት ዝግጁነቱ አልነበራቸውም፡፡“

ስለሆነም የንግድ እርሻን በተመለከተ ዘ-ህወሀትም ሆነ ካሩቱሪ ከአጼ ኃይለ ሥላሴ ጋር ምንም መፎካከር አይችሉም፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች በእነዚህ ታሪኮች ላይ እውነተኛ እና የማያወዛግብ እውነታን እንዲይዙ እፈልጋለሁ፡፡

እጅግ በጣም በተጋነነ እና ሳቢነት ባለው ዝቅተኛ “የመሬት ኪራይ ስምምነት” በግብርና እና በገጠር ልማት ሚኒስቴር እና በካሩቱሪ የግብርና ምርቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት/Karuturi Agro Products Plc መካከል በተደረገ የመሬት ኪራይ ስምምነት መሰረት ካሩቱሪ በረዥም ዕቅድ የመሬት ሊዝ (ኪራይ) ሌላ መጠባበቂያ 200,000 ሄክታርን ታሳቢ በማድረግ 100,000 ሄክታር ተረከበ፡፡ ተግባራዊ ሆኗልን?

በዘ-ህወሀት እና በካሩቱሪ መካከል በጋምቤላ ባደረጉት የመሬት ኪራይ ስምምነት መሰረት በአሁኑ ጊዜ አወዛጋቢ የሆነ የሕግ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ካሩቱሪ እየተከራከረ ያለው በውስጠ ተዋቂነት ስምምነቱ ዋጋ ያለው ከመሆኑ ጋር ባለው ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በተጨማሪ ስምምነታቸውን መተርጎም ስለሚችሉት የህግ መሳሪያዎች ባህሪ በማንሳት ዘ-ህወሀትን በመሞገት ላይ ይገኛል፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ጋር የሊዝ ስምምነት እንዳለው ይናገራል፡፡ የዘ-ህወሀት ሰነድ በበኩሉ ካሩቱሪ “የመሬት ኪራይ” ስምምነት አለው ይላል፡፡

ሸፍጡ የበለጠ እየተወሳሰበ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ እንደ ካሩቱሪ ከሆነ ሁለት የተለያዩ ዓይነት የሊዝ ስምምነቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ካሩቱሪ ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ጋር 300 ሺ ሄክታር መሬት እንደሚረከብ የሚገልጸው እናት ሰነድ ስምምነት ሲሆን፣

2ኛ) ሁለተኛው እና ሌላው ስምምነት ደግሞ “100 ሺ ሄክታር መሬት ለማረስ እረከባለሁ፡፡ ከዚያም 100 ሺ ሄክታሩን መሬት አርሸ የምጨርስ ከሆነ እና ከፈለግሁ ሌላ 200 ሺ ሄክታር ተጨማሪ ማግኘት እችላለሁ“

ካሩቱሪ እናት ሰነዱ የጋምቤላ ስምምነት እንጅ የግብርና ሚኒስቴር (ከላይ የተጠቀሰው የመሬት ኪራይ ስምምነት) ቅጅ አይደለም ይላል፡፡

መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም መሬት ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡ (ግን የመንግስትነቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የሚገኘው ማን ነው? ማለቴ ለመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘውን መሬት በሙሉ ጠቅልሎ በመያዝ የመሬት ከበርቴ ሆኖ የሚገኘው ማን ነው? በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስትነቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የሚገኘው ማንም ቢሆን ኢትዮጵያንም በባለቤትነት መያዝ ይችላል ማለት ነውን?

በአሁኑ ጊዜ ባለው ውዝግብ በዘ-ህወሀት የበላይ ተቆጣጣሪነት የሚመራው መንግስት እና የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት በአንድ ጊዜ የመሬት ባለቤትነቱ የእኔ ነው የእኔ ነው በማለት ሁሉቱም የመሬት ባለቤትነት የይገባኛል ጥያቄ በማቅረብ አንዱን ዓይነት መሬት ለካሩቱሪ ሰጥቻለሁ በማለት ላይ ናቸው፡፡ ከህገ መንግስቱ እና ከኮንትራት ስምምነት አንጻር የትኛው የመሬት ስምምነት ነው በሕግ ተቀባይነት የሚኖረው?

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ያገኘው የመሬት ኪራይ ከሆነ ዘ-ህወሀት የመሬት ከበርቴ ነው ማለት ነው? ካሩቱሪ እንዳለው ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት የሊዝ ስምምነት ካለው የሕግ ጥያቄ በማስነሳት የሊዝ ስምምነት ሰጭ እና የሊዝ ስምምነት ተቀባይ የሆኑት ተዋንያን ፍጹም የሆነ ልዩ ልዩ ዓይነት ግዴታዎች፣ ጥቅሞች እና ክልከላዎች ይኖሯቸዋል ማለት ነው፡፡

የካሩቱሪን መብት እና ግዴታዎች ለመቆጣጠር የሚያስችሉት የመቆጣጠሪያ ህጎች የዘ-ህወሀት ወይም ደግሞ የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ስምምነት ሁለቱም ናቸውን? ወይስ የትኛው?

ዘ-ህወሀት የመሬት ኪራይ ስምምነት በመጀመሪያው አንቀጽ በመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር ላይ የሰፈረው እንዲህ በማለት ይገልጻል፣ “ይህ የመሬት ሊዝ ስምምነት ተደረገ…ሆኖም ግን “የመሬት ኪራይ ስምምነቱ” እንዲህ ተከፋፍሏል “የመሬት ኪራይ ኮንትራክቸሯል ስምምነት…“

ዘ-ህወሀት ያረቀቀው “በግብርና እና በገጠር ልማት ሚኒስቴር እና በካሩቱሪ አግሮ ኢንዱስትሪ ፕሮዳክትስ ፒኤልሲ መካከል የተደረገ የመሬት ኪራይ ኮንትራክቸሯል ስምምነት ወይስ ደግሞ የመሬት ኪራይ ኮንትራት ነው?“

ያም ሆነ ይህ በመጨረሻ ላይ ጉዳዩ ነጻ ወደሆነ የፍትህ አካል ሲቀርብ  ስምምነቱ ሊዝ ወይም ደግሞ የመሬት ኪራይ የሚሉት ነገሮች በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት መካከል ላለው ውዝግብ ዋና ወሳኝ ነገሮች ሆነው የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

የጎሳ ፌዴራሊዝም መዋቅር (ማጭበርበር አላልኩም) እየተባለ እንደሚጠራው የፌዴራል መንግስት ወይም ደግሞ ክልላዊ መንግስታት በክልላዊ መንግስት ስር ያለን መሬትን የመያዝ ቅድሚያ የመብት ተጠቃሚነት ዕድል ይኖራቸዋልን?

ካሩቱሪ በቀጣይነት እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቧል፣ “ስምምነቱ እየተረቀቀ በነበረበት ጊዜ 300 ሺ ሄክታር እንዳይሆን ስለምናቸው ነበር፣ ሆኖም ግን በማስገደድ የተጠቀሰውን ብዛት እንዲሰፍር አደረጉ፡፡“

ካሩቱሪ ከዚህም በተጨማሪ 300 ሺ ሄክታር ሳይሆን 10 ሺ ሄክታር ብቻ ይፈልግ  እንደነበር ግልጽ አድርጎ ነበር፡፡

ካሩቱሪ የመሬት ኪራይ ስምምነቱን ፈርሞታል ወይስ ደግሞ ኃይልን በመጠቀም ሊዝ እንዲፈርም ተደርጓል?

የዘ-ህወሀት-ካሩቱሪን የመሬት ኪራይ ወይም የሊዝ ስምምነቱ ሰነድ በአንክሮ ሲታይ ወጥነት የሌለው፣ የተወሳሰበ እና የተጣመመ የሕግ ግንኙነት እንዳለው ያሳያል፡፡

ዘ-ህወሀት ከካሩቱሪ ጋር የፈረመውን ስምምነት ሰረዘው ምክንያቱም ካሩቱሪ ከሚጠበቀው በታች 1200 ሄክታር ብቻ ነው ያለማው፡፡ የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር የሆነው ጌታቸው ረዳ ዘ-ህወሀት ለካሩቱሪ ለረዥም ጊዜ ሲያራዝምለት ቆይቷል ብሏል፡፡

ረዳ የስምምነቱን መሰረዝ በሚከላከል መልኩ በካሩቱሪ ላይ በመሳለቅ እንዲህ ብሏል፣ “የሕግ አማራጭ አለው ብሎ የሚያስብ ከሆነ ይሞክረው፡፡“ (ረዳ በካሩቱሪ ላይ በመሳለቅ የሕግ አማራጭ አለው ብሎ የሚያስብ ከሆነ ይሞክረው ሲል ካሩቱሪ ወደ ይስሙላው የዘህወሀት የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ይዞ የሚሄድ መስሎት ከሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ የዘ-ህወሀት ስምምነቱን የመሰረዝ ትረካ ትንሹንም መስፈርት የሚያሟላ አይደለም፡፡ ዘ-ህወሀትን ከማመኔ በፊት ፒኖክዮን አምናለሁ፡፡ እኔ እስከማስበው ድረስ ”TPLF   “ በሚለው አህጽሮተ ቃል  “LF“ የሚሉት ሁለት ፊደሎች Lie Factory/የውሸት ፋብሪካ የሚለውን ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ ተወደደም ተጠላም እኔ እንዳለ እውነታውን እናገራለሁ!

ስድስት ዓመታት ወይም ደግሞ ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ የዌልስን ሀገር ያህል መጠን ያለውን ሰፊ ቦታ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እና አካባቢያዊ ሁኔታ መመንጠር እና የንግድ እርሻ ለማድረግ ማልማት ይቻላልን?

መሬቱን ለማልማት ምን ያህል ጊዜ ሊወስድበት ይችላል ተብሎ ሲጠየቅ ካሩቱሪ ወዲያውኑ እንዲህ የሚል ጥያቄ በዘ-ህወሀት ላይ ያቀርባል፣ “በግልገል ጊቤ 3 ግድብ ቁፋሮ ላይ የፈላ ምንጭ በተገኘ ጊዜ የኤሌክትሪክ ምርት ለማምረት ምን ያህል ጊዜ ይፈጃል በማለት ልትነግረኝ ትችል ነበር ወይ? ንገረኝ፡፡ ጀነሬተር በመያዝ ከቤቴ ተቀምጨ እሰራ ነበር፣ ምክንያቱም ለሁለት ዓመታት ያህል ምንም ዓይነት በቂ ኃይል አልነበረም፡፡ ዘ-ህወሀት የጊቤ 3ን የግድብ ግንባታ ስራ የጀመረው እ.ኤ.አ በ2008 ነበር፡፡ እናም  እስከ አሁንም ድረስ ትርጉም ያለው እና ሊለካ የሚችል የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት አልቻለም፡፡ በሀሳብ ደረጃ እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 በድረ ገጽ ላይ ተለቋል፡፡“

በዘ-ህወሀት የመሬት ኪራይ ስምምነት የአፈጻጸም መርሀ ግብር ወይም ደግሞ መገኘት ያለባቸው የስራ ውጤቶች በእርግጠኝነት የሉም፡፡ ስራውን ለመገምገም የሚያስችል የመነሻ መረጃ ቁጥር ወይም ደግሞ ሜትሪክስ በ9 ገጽ የመሬት ኪራይ ስምምነት ላይ የሌለ ከመሆኑም በላይ በካሩቱሪ በኩል የአፈጻጸም አለመኖርን ያመላክታል፡፡ በመሬት ኪራይ ስምምነቱ ውስጥ ካሩቱሪ ስኬታማ መሆኑ ወይም ደግሞ መውደቁን ለመወሰን የሚያስችል ምንም ዓይነት የተጻፈ ነገር የለም፡፡

የረዳ ለረዥም ጊዜ የማራዘም ጥያቄ በመሬት ኪራይ ስምምነቱ ላይ ምንም ነገር የማያመጣ የሕግ ትርጉም የለሽነትን የሚያመላክት ነው፡፡

ዘ-ህወሀት ፕሮጀክቱ የተሰረዘ መሆኑን ለካሩቱሪ ባሳወቀበት ጊዜ ተከላካዩ ካሩቱሪ እንዲህ አለ፣ “ለዚህ ስረዛ ዕውቅና አልሰጥም፡፡ የማቋረጡ ሁኔታ በህገ ወጥ መንገድ ንብረትን እንደመዝረፍ ያህል ነው፡፡ እናም በሁለትዮሽ የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ስምምነት በሚደረግበት ጊዜ በጊዜው የገበያ ዋጋ ታስቦ ካሳ መከፈል አለበት ይላል፡፡“

ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ወይም ደግሞ ከህዝቡ ጋር ምንም ዓይነት ችግር የለበትም፡፡ ለኢትዮጵያ ያለውን ፍቅር በይፋ ግልጽ አድርጓል፡፡ “ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት አጥባቂ ሀገር ናት፡፡ በጣም ጠንካራ የሆኑ እሴቶች፣ የእራሳቸው ደካማ እና ጠንካራ ጎኖች ያሏቸው በጣም ጠንካራ የሆኑ ባህል  አሏት፡፡ እኔ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ፡፡ እዚህ መጣሁ ምክንያቱም ይህችን ሀገር እወዳታለሁ፡፡ ቦታውን እወደዋለሁ እናም በርካታ የሆነ የእራሴን ገንዘብ በማውጣት በዚህ ሀገር ውስጥ አፈሰስኩ፡፡” በእርሱ ተማዕኒነት ላይ ጥርጥር የለኝም ሆኖም ግን ከመኖሪያ ቦታቸው በጅምላ ተፈናቅለው እና በመንደር ማሰባሰብ በሚል ፈሊጥ በአስር ሺዎች የሚሆኑ ዜጎች ለአስከፊ ድህነት ሲዳረጉ እያየ ዝም የሚል እንዴት ለህዝቡ ፍቅር አለኝ ሊል ይችላል?

ኢትዮጵያን ስለመውደድ ሁኔታ ከተነሳ ዘንድ አንድም የዘህወሀት አመራር በይፋ ኢትዮጵያን እወዳለሁ ወይም ደግሞበአንደበቱ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ የሚል ሰምቸ አላውቅም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንም ቢሆን ለማስተባበል የሚሞክር ካለ የእርኩም ስጋ ለመብላት ዝግጁ ነኝ፡፡ ይኸ በአትክልት ተመጋቢዎች ከባድ አነጋገር ነው!

የካሩቱሪ ችግር ዘ-ህወሀት እራሱ ነው፡፡ በበርካታ በዘ-ህወሀት ቃላት የተሞኙ የተጭበረበሩ መሆኑን ይናገራል፡፡ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ መስመር በመስመር በማንበብ ካሩቱሪ የተሞኘ መሆኑን በመጮህ ይናገራል፡፡ ካሩቱሪ ተታሏል ተጭበርብሯል፣ ተሞኝቷል፣ እናም ተጃጅሏል! በዘ-ህወሀት፡፡

ዘ-ህወሀት ካሩቱሪን ሙልጭ አርጎ በልቶ በወንዝ ላይ ላከው ፡፡

ካሩቱሪ በእርግጠኝነት በአታላይ ዘ-ህወሀት ጌቶቹ ትብብር ተነፍጓል፣ ተታሏል፣ ተጭበርብሯል?

እ.ኤ.አ በ2016 ካሩቱሪ በዝቅተኛ ማዕበል ብቻ አይደለም ክልከላ የተደረገለት ሆኖም ግን በጋምቤላ ቁማር ደሙ እስከደርቅ ድረስ መከራውን አይቷል፡፡

ለካሩቱሪ ቀደም ሲል እንዲህ በማለት ነግሬዋለሁነጻ መሬትን የሰጠ እጅ በነጻ የሚወስድ እጅ ነው…“

ካሩቱሪ የፈረመው ሊዝ  (ከዘ-ህወት ወይም ከጋምቤላ መንግስት ጋር ማለቴ ነው) ቀለሙ ከመድረቁ በፊት ሊቀማ እንደሚችል አውቃለሁ፡፡

በመጨረሻ ላይ ካሩቱሪ እየገለጸ ያለው ነገር በእርግጠኝነት በጣም መጥፎ ነገር ነው፡፡ ቃለ መጠይቅ በተደረገለት ጊዜ ካሩቱሪ እንዲህ ብሏል፣ “ በአፍረካ ውስጥ ውድቀት ከደረሰብህ አለቀልህ፡፡ ከወደቅህ ጆቢራዎቹ ይመጡና መሞትህን ይጠባበቃሉ፣ ከዚያም እየዘነጠሉ በሚገባ ይበሉሀል፡፡“

ደህና፣ ካሩቱሪ የዘ-ህወሀት ጆቢራዎች 100 ሺ ሄክታር ከእይታ ውጭ የሆነ መሬት ሲሰጡት በፍጥነት ከበው በመያዝ ሊዘነጥሉት እንደሚችሉ ሊያውቅ በተገባ ነበር፡፡ ይኸ ነገር በዩናይትድ ስቴትስ በፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ሲደረግ እንደነበረው ዓይነት ነው፡፡

ካሩቱሪ ልዩ በሆነ መልኩ በእይታ ካልተጠበቀ በስተቀር ስምምነት እያደረገ ያለው ከዳክየዎች ጋር ሳይሆን ከጆቢራዎች ጋር ነበር፡፡ ካሩቱሪ አጥንቱ እስኪቀር ግጠው ሊበሉት ስለሚችሉት ጆቢራዎች በአሁኑ ጊዜ ስሞታ እያሰማ የመሆኑ ጉዳይ በጣም የዘገዬ አይደለምን?

በእርግጥ እኔ ቀደም ሲል አውቄዋለሁ፡፡ በእርግጥ ካሩቱሪ ወደ ወንጀለኞቹ ሲሄድ ገና በመጀመሪያው ዕለት ምን ሊሆን እንደሚችል አውቅ ነበር፡፡ የካሩቱሪ ፕሮጀክት እንዴት ወደ መቀመቅ ሊወርድ እንደሚችል በእርግጠኝነት አውቂያለሁ፡፡

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 “ኢትዮጵያ፡ ለሽያጭ የቀረበች ሀገር“ በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችቴ ነጻ ስጦታ የያዙትን ማለትም ነጻ መሬት የሚያቀርቡትን ተጠንቀቅ በማለት ለካሩቱሪ ነግሬው ነበር፡፡

እነዚህ ነጻ መሬት ሰጭ ፍጡሮች እንዴት እንደሚያታልሉ፣ እንዴት በሸፍጥ የተሞሉ እንደሆኑ፣ አጭበርባሪዎች እና አታላዮች እንደሆኑ ለካሩቱሪ ተናግሬ ነበር፡፡ ይህን ነገር አታድርገው ወይም ብታደርገው እንኳ ኋላ ትጸጸታለህ በማለት ነገሬው ነበር! ነጻ መሬት የሰጡህ ሰዎች በገብጋባ ሰዎች ልብ እና አዕምሮ ውስጥ ያለውን የገብጋባዎችን ኃያልነት ይገነዘባሉ በማለት ነግሬው ነበር፡፡

ተስፋ የለሽ በመሆን እራስን በማግለል ካሩቱሪ በዘ-ህወሀት ሸፍጥ ተጠልፎ እንዳይወድቅ አስቀድሜ በማወቅ እንዲህ በማለት አስጠንቅቄው ነበር፡

“ካሩቱሪ ስለ ነጻ ምሳ፣ ነጻ ገንዘብ እና ነጻ መሬት በህልመኝነት ተነሳስቶ ከመቅጽበት እራሱን ለመዶል ነጻ ነበር፡፡ ነጻ ምሳ እንደሌለ ሁሉ ነጻ መሬትም እንዲሁ በነጻ አይገኝም፡፡ ካሩቱሪ ደኑን ለመመንጠር በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ካጠፋ በኋላ በጣም ውድ የሆኑ የግብርና መሳሪያዎችን አመጣ፣ እንደዚሁም ሁሉ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እና እርሻውን በአስቸኳይ መጀመር ነበር፡፡ ሆኖም ግን ነገሮች ሁሉ እንዲህ ቀላል ሆነው አልተገኙም፡፡  ካሩቱሪ በጋምቤላ አንድ ቀን ከእንቅልፉ ሲነቃ የእርሱ ኩባንያ በነጻ ያገኘው መሬት ከሁሉም በላይ ነጻ አይደለም፡፡ ካሩቱሪ ይህን ወይም ያን ለማግኘት ወይም ደግሞ የ50 ዓመት ሊዙን ህግ በመጣስ ወድቋል፡፡ ይህንን ትምህርት ቤት ወይም ደግሞ ያንን ክሊኒክ አልገነባም፡፡ የገነባቸውም ቢሆኑ በቂዎች አይደሉም ወይም ደግሞ ጥሩዎች አይደሉም፡፡ በትክክለኛው መንገድ ይህንን መንገድ ወይም ያንን ከተማ አልገነባም፡፡ እናም የገነባቸው በቂዎች አይደሉም፣ እንዲሁም ገና ብዙ መገንባት ይኖርባቸዋል፡፡ ካሩቱሪ በሚሊዮኖች ሄክታር ነጻ መሬት ያሰጣቸው የውጭ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ሕጉ ነጻ መሬት የሰጡት አካሎች ምን እንደሚፈልጉ መተርጎም አለበት… በመጨረሻም ነጻ መሬት የሰጠ እጅ በደንብ የለማውን ነጻ የእርሻ መሬት በነጻ የሚወስድ እጅ እንደሆነ ካሩቱሪ ይደርስበታል!…በመጨረሻ ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ሁሉንም ነገር ያጣሉ፡፡ በመጨረሻ ነጻ መሬት አዳዮች መልሰው ይወስዱታል፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ከአንጎላ እስከ ዙምባብዌ ለባዶ ዓይነት ሸፍጦች ነጻ መሬቶችን አይተናል፡፡“

ካሩቱሪ ከቅርብ ጊዜ በፊት በተደረገለት ቃለ መጠይቅ ይህንን ነገር ማድረግ እንደሌለበት ወዳጆች ነግረውት እንደነበር አመነ፡፡ እንዲህ ነበር ያለው፣ “ጥቂት ኢትዮጵዊ የሆኑ ወዳጆቼ ጋምቤላ የመሄዴን ጉዳይ እብደት እንደሆነ ነግረውኝ ነበር፡፡“ ሆኖም ግን እወጣዋለሁ የሚል መልስ በመስጠት ለስጋታቸው አመስግኛቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በዚህች ሀገር ውስጥ የምግብ ምርትን ለመጨመር በሚል ዓላማ ወደ ጋምቤላ ሄጃለሁ፡፡ ግን ያ ከመቼ ጀምሮ ወንጀል እንደሆነ የማውቀው ነገር የለም፡፡ ገንዘቤን አፍስሻለሁ እናም እርሻዬን አልምቻለሁ፡፡

ጋምቤላ መሄድ እብድነት አይደለም፡፡ ይልቁንም እብድነቱ የዘ-ሀወሀትን ቃልኪዳን ከማመኑ ላይ ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ቃልኪዳን ከማታለል ቃልኪዳን የዘለለ ጠቀሜታ የለውም፡፡ ካሩቱሪ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን ትምህርት የወሰደበት አጋጣሚ ነው፡፡

ስለሆነም እ.ኤ.አ ጥር 2016 ሁሉም ትንበያዎቼ እውነት ሆኑ፡፡

ይህንን ማለት ያስጠላኛል፣ እናም ይህንን ከማለት የማገኘው ደስታ የለም፡፡ ሆኖም ግን እለዋለሁ፡፡ ስለካሩቱሪ ሲደረግ ስለነበረው የስምምነት ጉዳይ ትክክል ነበርኩ፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ ትክክል ነበርኩ፡፡ የዘ-ህወሀት ስምምነት ምን እንደነበረ አስቀድሜ ደምድሚያለሁ፡፡ ሌላ ምንም ሳይሆን ሸፍጥ!

ካሩቱሪ ለውድቀት ነበር የተዘጋጀው?

ካሩቱሪ የገዥ ጥፋተኝነትን በመያዝ በአሁኑ ጊዜ ጆቢራዎቹ በፍጥነት እየተሰባሰቡ እየሞተ ያለውን ፕሮጀክት ለመጋጥ አሰፍስፈው እንደሚጠባበቁ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህሀወት ጋር ስምምነቱን ሲፈራረም ምን እያሰበ ነበር? (ይኸ ግልፅ ጥያቄ ነው፡፡ መልሱ አያስብም ነበር ነው ፡፡)

ምናልባትም “የዓለም የጽጌረዳዎቸ ንጉስ” ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነቱን ሲፈራረም ጽጌረዳ ዓይነት መነጽር አድርጎ ነበር፡፡ ጽጌረዳን በሌላ በማንኛውም ስም ብንሰይማትም ያው ጫፋጭ ሽታዋ አይቀየርም፡፡ ሆኖም ግን “የመሬት ኪራይ ስምምነት” በሌላ በማንኛውም ስም “ሊዝ” ነውን?

ካሩቱሪ 10 ሺ ሄክታር መሬት ብቻ ነበር የጠየቀው ምክንያቱም ለጊዜው ሊያለማው የሚችለው መጠን ይህን ያህል ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከፍላጎቱ እና ከአቅሙ ወጭ በግዳጅ 100 ሺ ሄክታር እንዲቀበል ተደረገ፡፡ እንዲወድቅ የተደረገ ድርጊት ነበርን? ይህንንም ድርጊት በተመሳስሎ ለመግለጽ አንድ ሰው አንድ እንጀራ (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳቦ) ለመብላት ብቻ ቢችል እና አምስት እንጀራዎች ተሰጥተውት እንዲበላ ቢገደድ ቀሪዎቹን አራቱን እንጀራዎች ሳይበላ በመቅረቱ ሊወቀስ ይችላልን? ካሩቱሪ አሁን ነጥቡን አግኝቶታል፡፡

ዘ-ህወሀት የክርክራቸውን መጨረሻ በመያዝ እንደሚቀጥሉ በእርግጠኝነት ካሩቱሪ እምነት አለውን? አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ እና የእርሱ ዘ-ህወሀት በጋምቤላ እንዲያሸንፍ ቢፈቅዱለት የለየለት ሞኝ ነው፡፡

ካሩቱሪ ገዥ ተጠንቀቅ የሚለውን መርህ በእራሱ የአደጋ ተጋላጭነት እንዳለ ትቶታል፡፡

አምባገነኑ መለስ እና የእርሱ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሆነው ዘ-ህወሀት አንድ ጨዋታ ብቻ እንዴት እንደሚጫወት ያውቃል፡፡ የዜሮ ድምር፡፡ ይህም ማለት ሁልጊዜ መቶ በመቶ ያሸንፋሉ፡፡ ሌላው እያንዳንዱ ሰው ሁልጊዜ መቶ በመቶ ይሸነፋል፡፡

እኔን ልታምነኝ አትችልምን? ከዚያም እንዲህ የሚለውን ይህንን ጥያቄ መልስ፡  “ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ ግንቦት 2005 የተካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በስንት መቶኛ ነው ያሸነፈው? ደህና! አንተን ልሰማህ አልችልም፡፡ እኮ በስንት መቶኛ?!“

እንዲህ የሚል ቀላል ጥያቄ እነሆ፡ ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2010 የተካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በስንት መቶኛ ነው ያሸነፈው? (ፍንጭ፡ 99.6%::)

ጉዳዬን ላጠቃለው!

ካሩቱሪ እና አምባገነኑ መለስ በመጨረሻ አንዱ አንዳቸውን ለማታለል በመተንበይ ነበር እንዴ ይህንን ስምምነት የተፈራረሙት?

በተኩላዎች መካከል መከባበር ይኖራልን? የሚለው ሌላኛው የጥያቄ መንገድ ነው፡፡

በእርግጠኝነት አላውቀውም፣ ሆኖም ግን  የትኛው የማድረግ ብቃት እንዳለው መናገር አልችልም፡፡

ሆኖም ግን ካሩቱሪ በእራሱ በኩል ያለውን ታሪክ ያቀረበበት መንገድ አሁን በህይወት በሌለው በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ እየተባለ በሚጠራው በታናሽ ታላቅ ሰው እና ታላቅ ቦታ በያዘው የአጭበርባሪዎች ጌታ ጋር ባደረገው ስምምነት ሙሉ በሙሉ መታለሉን የማያውቀው መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን እንዲፈርም ሲጨቀጨቅ የነበረበትን ዕድለቢስ ቀን እንዲህ በማለት በሀዘን ያስታውሳል፡፡

“አንድ ቀን ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው እና በመንግስቱ ላይ ታላቅ የስልጣን ቦታ ከያዘ ሰው ጋር ተገናኘሁ፡፡ ከእርሱ ጋር ቀጠሮ ነበረኝ፡፡ በቀጠሮው መሰረት ወደዚያው በመሄድ በእንግዳ መቀበያ ማረፊያ ቦታው ላይ ተቀምጨ በነበረበት ጊዜ ‘ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ 70 ሺ ቶን ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ታስገባለች‘ የሚል ጽሑፍ በጋዜጣ ላይ አየሁ፡፡ ከዚያ በኋላ የንግድ ስምምነቴን ከፈጸምኩ በኋላ ከ80 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ያላት፣ በቂ ዝናብ እና ዓመቱን ሙሉ የማያቋርጥ የጸሐይ ብርሀን ሀገር እና የ80 ሚሊዮን ህዝብ ባለቤት የሆነችው የተገላቢጦሽ በሆነ መንገድ ምግብ ከደቡብ አፍሪካ ስታስገባ በማየቴ ስሜቴን ጎዳው አልኩ፡፡ እኔ ማንም አይደለሁም፡፡ የዓለም ባንክ አይደለሁም፡፡ ሆኖም ግን ጎዳኝ፡፡”

ስም የለሹ ታላቅ መሪ ተብዬ (ካሩቱሪ ኪም ጆንጊል የ ሰሜን ኮርያ ነበር አላለም) ካሩቱሪን እንዲህ በማለት ጠየቀው፡

“በግብርና ላይ መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ መሰረተ ሀሳቡ የለኝም፡፡ እኔ የማውቀው የአበባ ንግድን ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ260 ኪ/ሜ ርቀት አካባቢ ላይ በምትገኘው ከባኮ ከተማ መሬት ተሰጠሁ፡፡ እዚያ ላይ እርሻውን ማረስ ጀመርኩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት እኔን ለማየት ፈለገ፡፡ ኤምባሲው የት እንዳለ ጠየቅሁ፡፡ በቃላቴ ላይ ምልክት በማድረግ ጋምቤላ ሌላ ሀገር እንደሆነች አድርጌ አሰብኩ፡፡ ድንቁርናዬን ደገምኩት፡፡ እርሱ ከቢሮዬ ድረስ በመምጣት እንደሚጎበኘኝ ተነገረኝ፡፡ ከዚህ ይልቅ በግዮን ሆቴል ተገናኘን እና ጋምቤላ ውስጥ መሬት እንደሚሰጡኝ ተናገረ፡፡ ስለሆነም በፕሬዚዳንቱ እና በጋምቤላ መንግስት ግብዣ መሰረት ጋምቤላ ሄድን፡፡ 10 ሺ ሄክታር መሬት እንዲሰጡን ጠየቅን…መላው የጋምቤላ መንግስት ካቢኔት በስብሰባ ላይ ነበር፣ እናም 300 ሺ ሄክታር መሬት መውሰድ አለብህ አሉ፡፡ ሆኖም ግን እኔ መውሰድ የምችለው 10 ሺ ሄክታር መሬት ብቻ ነው ምክንያቱም አቅሜ ያንን ያህል ነው አልኩ፡፡ ምንም ዓይነት ምርጫ አልሰጡኝም፡፡ ከስብሰባው በኋላ ሰዎቹ ጠሩኝ እና 300 ሺ ሄክታር መሬት እንሰጥሀለን አሉኝ፡፡ አመሰግናለሁ ሆኖም ግን 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ማልማት የምችለው አልኩ፡፡ እነርሱ ግን 300 ሺ ሄክታር መሬት እንድወስድ ማግባባት ጀመሩ፡፡ እናም ስምምነቱን አደርጋለሁ ግን እነርሱ ግን በዚህ መሬት እንደማይስማሙ ገለጹልኝ፡፡ መንግስት ይህን የሚያህል ግዙፍ መሬት በጣም ርካሽ በሆነ ዋጋ በመስጠቱ ምክንያት ከሁሉም ማዕዘን ትችት ይጎርፍበት ጀመር፡፡ እኔ ግን አልወሰድኩትም፡፡ በአንድ ጊዜ አንድ እንጀራ ነው መብላት የምትችለው፡፡ ሆኖም ግን አምስት እንጀራ አቀረቡልኝና ብላው አሉኝ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ተመለስኩ እና ለምን መጨረስ እንዳልቻልኩ ወቀሳ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ከዚህ በስተጀርባ ምን ዓይነት አመክንዮ ነው ያለው?“

እ.ኤ.አ መስከረም 2010 አምባገነኑ መለስ በካሩቱሪ ስምምነት ላይ በመመካት እራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ እንዲህ በማለት አወጀ፣ “ትርፍ ምርት ማምረት የሚያስችለንን እ.ኤ.አ በ2015 ምንም ዓይነት የውጭ እርዳታ ሳይስፈልገን እራሳችንን መመገብ የሚያስችል ዕቅድ ነድፈናል፡፡“ (እ.ኤ.አ በ2016 ግን እራስን መመገብ መቻል ሳይሆን 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ለረሀብ መጋለጣቸውን ልብ ይሏል፡፡)

ካሩቱሪ እንዲህ ይላል፣ “ መንግስት የእህል ምርት ወደ ውጭ እንዳይወጣ ክልከላ የሚጥል አዋጅ በማወጅ እና 180 ሚሊዮን ዶላር ለዚሁ ተግባር የተመደበውን በማገድ የስምምነቱን የመጨረሻ ካርታ አልሰጠንም፡፡ እንደዚሁም ከብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እ.ኤ.አ በ2014 በጦርነት ከተበጣጠሰችው ከደቡብ ሱዳን የቅርብ ጎረቤት ወደሆነችው ወደ ጋምቤላ የዲዝል ነዳጅ እንዳይገባ ከለከለ፡፡“ እንዲህ ይላል፣ “100 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ የማስፈጸም ጥረቶች እና ዓመታዊ የጎርፍ አደጋን በመቀልበስ መንግስት እያካሄደው ያለው  ዕድገት በቂ ማስረጃ ነው፡፡“

የካሩቱሪ ታሪክ ቀላል እና በዋናነት አሳማኝ ነው፡፡ እኔ ዳኝነት እየሰጠሁ እና ዘ-ህወሀትን እየወቀስኩ አይደለም (ይህንን መገመት የማትችሉ ከሆነ)፡፡ ሆኖም ግን በቀረበው መረጃ መሰረት የካሩቱሪ ታሪክ በእውነታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የካሩቱሪን ፕሮጀክት በቅርብ ስከታተል ቆይቻለሁ፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ ያሉ የሕግ ሰነዶችን በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት ባለስልጣኖች ሲሰጡ የነበሩትን መግለጫዎች ሳነብ እና ስመረምር ቆይቻለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የካሩቱሪ ፕሮጀክት በጋምቤላ ላይ ስለሚያስከትለው ተጽዕኖ በአበዳሪ እና በለጋሽ ድርጅቶች የወጡ ሰነዶችን እና ህትመቶችን እንደዚሁም ነጻ ጥናቶችን እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን እና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ሲሰጡ የነበሩትን ትችቶች እና መግለጫዎች ሁሉ ስመረምር ቆይቻለሁ፡፡

በእኔ መደምደሚያ ካሩቱሪ እንዲወድቅ አልነበረም የጀመረው፡፡ ሆኖም ግን የውድቀት ዕድል እንዲገጥመው ተደርጓል፡፡

ዘ-ህወሀት ከካሩቱሪ ስምምነት ጋር በተያያዘ መልኩ በእኔ አመለካከት ለመጨረሻው የፍልሚያ ጨዋታ ሁለት ስትራቴጂዎችን ነድፏል፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ካሩቱሪ ግዙፍ የሆነ የንግድ እርሻ ድርጅትን በማቋቋም መሬቱን ከማልማት አንጻር ስኬታማ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ሁሉንም ነገር እነርሱ በመበዝበዝ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለግብረ አበሮቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው ለማከፋፈል የሚያስችል መንገድ ይፈልጋሉ፡፡

2ኛ) ካሩቱሪ እየወደቀ ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉንም የእርሱን የእርሻ መሳሪያዎችን እና የፈሰሰውን መዋለ ንዋይ በመያዝ ካሩቱሪንን ድራሹን አጥፍቶ ከሀገር ማባረር ነው፡፡ በሁለቱም መንገዶች ዘ-ህወሀት ያሸንፋል! በአሁኑ ጊዜ ለዘ-ህወሀት ጆቢራዎች የእራት ጊዜ መሆኑን ካሩቱሪ አሳምሮ ያውቃል!

በእርግጥ ዘ-ህወሀት በካሩቱሪ ላይ ያደረገው ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ እርሱ የተለየ ሰለባ እንደሆነ አድርጎ የማሰብ ስሜት ሊኖረው አይገባም፡፡ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ መዋለ ንዋይ ማፍሰስ እና የማጭበርበር የሸፍጥ ስራ በመስራት በርካታ ዕኩይ ተግባራትን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ ብዙ ነገር ይማር ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ነገር አላደረገም፡፡

እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 ወደኋላ መለስ ብለን ስናየው በኢትዮጵያ የካሩቱሪ ፕሮጀክት ማናጀር የነበረው ካርምጅት ሴክሆን በጋምቤላ ውስጥ ያለውን መሬት እንዴት እንዳገኙት እጅግ በደስታ ስሜት ፍንድቅድቅ ባለ ሁኔታ እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው፡ “መሬቱን ፍጹም አይተነው አናውቅም፡፡ እነርሱ ሰጡን እኛ ደግሞ ተቀበልናቸው፡፡ በእውነት ይህንን ነው ያደረግነው፡፡ መሬቱን እንኳ አላየነውም፡፡ (በድል አድራጊነት ሳቁን ለቀቀው፡፡) እነርሱ ሰጡን፡፡ ይኸው ነው፡፡ በጣም ጥሩ መሬት ነው፡፡“

“የዓለም የጽጌረዳው ንጉስ” የንግድ ስምምነቶችን ሲያካሂድ ጽጌረዳ ዓይነት መነጽር አድርጎ ነው እዴ ሄዶ የነበረው? እሪ ብሎ በመጮህ አንድ በዓለም ላይ ያለ የንግድ ድርጅት እንዴት ባላየው መሬት ላይ የ10 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ያፈስሳል?

የካሩቱሪ-ዘ-ህወሀት ስምምነት በዓለም የቅጥፈት ዓለም ውስጥ የፑፍን ታምራዊ ድራጎን እና የሳንዲን የቀይ እና ሰማያዊ ላሞች እና ቀይ ዝሆኖችን ሁልጊዜ ያዩ እንደነበር የሚተርተውን ተረት እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡

በእርግጥ ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ በዘ-ህወሀት የቢዝነስ ፕላናቸውን ይዘው እንዲመጡ ሲጠየቁ እና እንዲጸድቅላቸው ለበርካታ ወራት ጠብቁ እየተባሉ ሲጠብቁ ቆይተው ባልታሰበ እና በድንገት የዘ-ህወሀት ግብረ አበሮች በቢዝነስ ፕላናቸው ላይ ዲያስፖራዎቹ ያቀረቡትን ፕላን እንዳለ በመውሰድ እነርሱ ሲሰሩበት የነበረበትን እና በርካታ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ለክስረት የዳረገበትን ሁኔታ መረዳት አይችሉም ነበርን?

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ የዲያስፖራ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ከፍተኛ በሆነ ግብር እንዲደቆሱ ተደርገው ውጤታማ ከነበረው ቢዝነሳቸው ከተባረሩ በኋላ ያቋቋሟቸው የንግድ ስራዎች ለዘ-ህወሀት ግበረ አበሮች እና ደጋፊዎች በጨረታ እየተቸበቸቡ መሰጠታቸውን በማየት ትምህርት ይሆናቸው ነበር፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ህጋዊ የቢዝነስ ሰዎች የቢዝነስ ስራዎቻቸው በዘ-ህወሀት መሪዎች ወይም ደግሞ በቤተሰብ አባሎቻቸው፣ በግብረ አበሮቻቸው እና በጓደኞቻቸው እየተነጠቁ ሲወሰዱባቸው ከነበረው ሁኔታ በመማር ከኪሳራው ይድን ነበር፡፡

ካሩቱሪ ስምምነቱን ከመፈረሙ በፊት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ቢያደርግ ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ ህጋዊ የቢዝነስ ሰዎች ቢዝነሶቻቸውን ከዘ-ህወሀት እና ከእነርሱ ግብረ አበሮች ጋር በድብቅ የእነርሱን እውነተኛ ማንነት በመደበቅ ለዘ-ህወሀት ባለቤቶች ያስረክቡ እንደነበር ትምህርት በመውሰድ ከእንደዚህ ያለው ኪሳራ እራሳቸውን ያድኑ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2011 ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ/Global Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2000 እና በ2009 በህገወጥ መልኩ የተገኘ 11.7 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ወደ ውጭ በማስወጣት እንድታጣ ተደርጓል፡፡“ የበለጠ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ የዚያ ዓይነት ገንዘብ ያለው ማን ነው፣ እናም እንዴት አድርጎ ነው በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ውስጥ እንዲወጣ የተደረገው? የሚለው ነው፡፡

ዘ-ህወሀት በካሩቱሪ ላይ ያደረገው ነገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲጫወቱት የቆዩት ጨዋታ ነው፡፡ የቆየው የማታል ድርጊት ነው፡፡

አንድ እንግዳ የሆነ ነገር ግን አግኝቻለሁ፡፡ ዘ-ህወሀት ጥቂት ቁራጭ መሬት ከመስጠቱ በፊት ጥቂት መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ሰዎችንም ቢሆን ሁልጊዜ የቢዝነስ ፕላንን ለማየት ይጠይቃል፡፡ ታዲያ እውነታው ይኸ ከሆነ ዘ-ህወሀት በእግሩ ላልረገጠው እና መሬቱን ላላየው ለውጭ ሀገር ሰው 100 ሺ ሄክታር መሬት እንዴት ሊሰጥ ቻለ?

እውነት ለመናገር ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ውስጥ በፊውዳሉ ስርዓት ሲያደርጉት ከነበረው እጅግ በከፋ መልኩ መሬትን በዓይነ ገመድ የመስጠት ሁኔታ ነው፡፡

በእርግጥ ይህ ነገር በጣም አውሬነት፣ አዕምሮን የሚበጠብጥ እና በቀላሉ ሊታመን የማይችል ነገር ነው!

እኔን ታማኝነት የሌለው፣ ከካሩቱሪ ጋር የወገነ፣ ዘ-ህወሀትን የሚጠላ ወዘተ፣ ወዘተ በማለት የሚከሱኝ ጥቂት ሰዎች እንደሚኖሩ እርግጠኛ ነኝ… ማለት የምችለው ነገር እንደዚህ ነው!

ማለት የምችለው እ.ኤ.አ መጋቢት 2011 የሰጠሁት ትንታኔ እና ትንበያ ትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር መሆኑን ነው፡፡ መካድ አይቻልም !

በማይበገረውየጋምቤላ አንበሳእናበዘህወሀት ጅቦችመካከል ያለ ጦርነት፣

እራሱን “የጋምቤላ አንበሳ” አድርጎ የሚጠራው ካሩቱሪ ጥፋተኛ ያለመሆኑን በጽናት እንደሚያስመሰክር አውጇል፡፡

ዘ-ህወሀት የግል ለማድረግ እያደረገው ያለው ስረዛ የሁለትዮሽ የጋራ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ስምምነት እንደሚለው የገበያ ዋጋን መሰረት ባደረገ መልኩ በካሳ መደገፍ አለበት፡፡

ካሩቱሪ በመከላከል ተግባሩ ከዚህም በበለጠ ዘልቆ የሚሄድበት ይሆናል፡፡ መሬቴን የሚነካ ማንኛውንም ባለስልጣን እሟገታለሁ ብሏል፡፡ ከዚያ በኋላ ውጤቱን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የሚያዩት ይሆናል፡፡ እኔ ግማሽ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነኝ፡፡ የህይወቴን አስር ዓመታት ያህል እዚህ አሳልፊያለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ ክርክር እንድናደርግ እጠይቃለሁ፡፡ ከዚህ በላይ የመናገር መብት የለኝም ምክንያቱም የኢትዮጵያዊነት ዜግነት የለኝምና፡፡ እኔ ለዚህች ሀገር እንግዳ ነኝ፡፡

እንደ ግማሽ ኢትዮጵያዊነቱ ካሩቱሪ ለጠብ አይጋበዝም፡፡

ካሩቱሪ እንዲህ ይላል፣ “እኔ ወደ ጋምቤላ የሄድኩ አንበሳ ነኝ፡፡ ምናልባትም የቆሰልኩ፣ ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ያው አንበሳ ነኝ፡፡ እያምባረቅሁ ወይም ደግሞ እራሴን ከፍ ከፍ እያደረግሁ አይደለም፡፡“

ምንጊዜም ካሩቱሪንን እንደ ቢዝነስ ሰው ሳስበው ካሩቱሪ በጽናት የተሞላ ጀግና ሰው ነው፡፡

ካሩቱሪ በዘ-ህወሀት ወሮበሎች ፊት በመቅረብ የእርሱን መሬት ሊዘርፉት እንደማይችሉ እና ይህንን ሙከራ የሚያደርጉ ከሆነም ትልቅ አቧራ ሊያስነሳ እንደሚችል ይነግራቸዋል፡፡

ሚስተር ካሩቱሪንን አክብሩት! በዘራፊ ወሮበሎች ገንዘብህን ልታጣ እንደማትችል መጠራጠር የለብህም፣ ሆኖም ግን ለመብትህ የቆምክበትን መንገድ እወደዋለሁ፡፡ ጉዳቶችን አስወግድ! በሙሉ ፍጥነት ወደፊት ቀጥል፡፡

ካሩቱሪ ለንብረቱ እና ለመብቱ መታጋሉን እቀጥላለሁ ሲል ጉዳት ለማድረስ መሆን አለመሆኑን የማውቀው ነገር የለም፡፡ ረዳ የህግ ምርጫውን መሞከር ይችላል ብሏል፡፡

ይኸ የሚሆነው በዘ-ህወሀት የይሰሙላው የዝንጀሮ ፍርድ ቤት ነውን?

ስለዚህ ጉዳይ እርሱት!

በቆሰለ አንበሳ እና በሚስከመከሙ ጅቦች እና በሚንጋጉ ዞቢራዎቸ መካከል የሚደረገውን ጦርነት ለማየት መቆየት አልችልም፡፡

በጋምቤላ ክልል ውስጥ በአንበሶች እና በጅቦች መካከል በመደበኛነት የአጭር ጊዜ ጦርነት እንደሚካሄድ እውነት ነው፡፡

ብቸኛ ጥያቄ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው ጉዳይ በቆሰለ አንበሳ እና በሚስከመከሙ ጅቦች እና በተራቡ ጆቢራዎች መካከል የሚደረገው ጦርነት ውጤት ነው፡፡ ህይወትን ከዱር አራዊት ጋር ማመሳሰል ምን ዓይነት አስገራሚ ነገር ነው?

ካሩቱሪ በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ የመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ሁኔታ እራሱን ከጥቂት ቀልደኞች ለመከላከል በማሰብ አንዳንድ ሀሳቦችን ለመፈንጠቅ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ “ይኸ ማስፈራራት ነው ምክንያቱም በቃ በቃ ነው” በማለት ሲናገር ቃላትን ለማሳመር አይደለም፡፡ እራሴን መከላከል አለብኝ፡፡ መሬቴን የሚነካ ማንኛውንም ባለስልጣን እሟገታለሁ፡፡ (እንደ አበደ ውሻ ነው! ካሩቱሪ በመንፈሰ ጠንካራነት እና በጽናት ቆሟል፡፡)

በሁሉም በህንድ የሁለትዮሽ ኢንቨስትመንት አጠባበቅ ስምምነት አወዛጋቢ የሆኑ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የሚከተሉትን እንደ ቅደም ተከተላቸው ይቀርባሉ፡፡ እነርሱም፡

1ኛ) ስምምነት፣

2ኛ) ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ካልተፈቱ ግጭቱ ወደ ፍትህ አካል ይቀርባል፣

3ኛ) ግጭቱ የተከሰተባቸው ፓርቲዎች በአስታራቂዎቸ አማካይነት መታረቅ ካልቻሉ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አስፈላጊዎቹን ቀጠሮዎች ያዘጋጃል፡፡ የአስታራቂ ፍርድ ቤቱ የእራሱን የአሰራር ስርዓት እንዲወስን ስልጣኑ ተሰጥቶታል፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ጋር ያለውን ግጭት በእርቅ መፍታት እንደሚያስፈልግ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ (የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች የሁለትዮሽ ኢንቨስትመንት አጠባበቅ ስምምነትን እርቅ ወይም ደግሞ የህግ እና የፖለቲካ ጠቀሜታ ያውቁታልን?)

የመሬት ማከራየት ስምምነት አንቀጽ 12 የሚከተለውን መብት እንደሚያጎናጽፍ ማስተዋል ጠቃሚ ነው፣ “ በዚህ ስምምነት መሰረት ስለአፈጻጸም ህጉ በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል“ ይላል፡፡

በእኔ ትንታኔ መሰረት ግጭትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ለዘ-ህወሀት ጥሩ ነገር አይመስልም፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2002 ለመጨረሻ ጊዜ የግጭት መፍቻ ስምምነት በቀረበላቸው ጊዜ በኢትዮ-ኤርትራ የወሰን ድንበር ላይ የምትገኘውን ባድሜን እንዲለቁ ታዝዘው ነበር፡፡ (እኔ እንደዚህ ያለውን ነገር ለመግለጽ ይከብደኛል፡ አንድ ሀገር አንጸባራቂ በሆነ መልኩ ድልን ተቀዳጅታ ጠላቷን ካሸነፈች በኋላ እና በጦር ሜዳ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ህይወት በመገበር ድንበሩን ካስከበረ በኋላ ተመልሶ ይህንኑ ግዛቱን ለወራሪው ኃይል በግጭት ማስወገድ ስምምነት መሰረት ለመስጠት እንዴት ስምምነት ያደርጋል?

ይኸ ነገር አጠቃላይ ግራ የተጋባ ነገር እኮ ነው!)

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን የዘ-ህወሀት “የመሬት ኪራይ ስምምነት” ደካማ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ የሕግ መሳሪያ ከወንፊት በላይ ቀዳዳ ያለው ነው፡፡ ለግጭት ፈች አስማሚዎች አስቂኝ የሆነ እና ችግሮችን ለመፍታትም አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጥር ነው፡፡

የመሬት ማከራየት ስምምነቱን ያረቀቁት ሰዎች የአቅም ክፍተት የሚታይባቸው እና ደንቆሮዎች በመሆናቸው በእራሱ/በእራሷ ሊያፍር/ልታፍር ይገባቸዋል እላለሁ፡፡

እጅግ ሰፊ የሆነ የኢትዮጵያዬ ግዛት የህግ መሳሪያዎችን ከዓለም አቀፍ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ልውውጦች አንጻር ምን እንደምታ እንደሚኖራቸው በማያውቁ እና ምንም ዓይነት ሀሳብ በሌላቸው በወሮበላ ዘራፊ የደናቁርት ስብስብ በድንገት ለሌላ ሀገር አሳልፈው ሲሰጡ ማየት አዕምሮን የሚበጠብጥ እና የሚያሳብድ ነገር ነው፡፡

ምን ዓይነት የሚያናድድ ነገር ነው!

(ዘ-ህወሀት የኢትዮጵያን አንጡራ ግዛት እየቆረጠ ለሱዳን ለመስጠት በሚስጥር ያደረገውን ስምምነት ወይም ደግሞ ከዓባይ ግድብ ጋር በተያያዘ መልኩ ከግብጽ ጋር እየተደረገ ያለውን አግባብነት የሌለው ስምምነት በማስብበት ጊዜ ያንቀጠቅጠኛል፡፡ ስለመጋዝኑ ማንም ጉዳዩ አይደለም፡፡ ስለሀገሪቱ ማለቴ ነው፡፡)

ያም ሆነ ይህ ግልጽነት ከሌለ ወይም ደግሞ ስለትርጉም አሰጣጥ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች አጠቃላይ የህግ መስፈርቱ ግልጽ ያለመሆኑ እና በጥርጣሬ የተሞላ መሆኑ ስምምነቱን ያረቀቁት ክፍት ለሆነ ትርጉም እንዲጋለጥ አድርጓል፡፡

የዘ-ህወሀት የህግ ባለሙያዎች እጆቻቸውን በአየር ላይ እያወዛወዙ እና ግልጽ ያልሆነ ትርጉም ያላቸውን ቃላት እየወሰዱ በመለጠፍ ስለመሬት ኪራይ ስምምነት አዘጋጅተው እንዳቀረቡ አስባለሁ፡፡

የካሩቱሪ የህግ ባለሙያዎች ቃላቱ ከወረቀቱ ላይ እስከሚጠፉ ድረስ ስምምነቱን እየቆረጡ እና እየቆራረጡ የሚመረምሩት ይሆናል፡፡

ከመሬት ከራይ ስምምነቱ ጋር በተያያዘ መልኩ በርካታ የቴክኒክ እና የትርጉም ችግሮች ያሉበት ቢሆንም መቁጠሩን አቁሚያለሁ፡፡

በካሩቱሪ እና በዘ-ህወሀት/በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት መካከል በስምምነቱ ላይ መጥፎ አሻራ ሊያሳርፉ እንደሚችሉ ከዚህ በታች ጥቂት ቀላል፣ ግልጽ የሆኑ የመለኪያ ጉዳዮች ይቀርባል፡፡

1ኛ) ስለጋምቤላ ፕሮጀክት ጉዳይ ስንት ስምምነቶች ይኖራሉ? ካሩቱሪ ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት እና ሌላ ደግሞ ከዘ-ህወሀት ጋር በግዳጅ እንዲፈረም ለተደረገው ለ300 ሺ ሄክታር መሬት አንድ ስምምነት አለ ይላል፡፡ ከግዳጅ ሕግ አንጻር ትክክለኛው ስምምነት የትኛው ነው?

2ኛ) በእርግጠኝነት መሬቱን በባለቤትነት የያዘው ለማከራየት ስልጣኑ ያለው ወይም በኮንትራት ለመስጠት የሚችለው ማን ነው? በክልሎች ውስጥ የሚገኝን መሬት በሊዝ ማከራየት ወይም ደግሞ በኮንትራት ለመስጠት ስልጣኑ ለፌዴራሉ መንግስት ነው ወይስ ደግሞ በክልሎች? በክልል መንግስታት ስር የሚገኝን መሬት የፌዴራል መንግስት የክልሎችን ስልጣን በመጣስ እጅግ ግዙፍ የሆኑ መሬቶችን ለሌለ ሀገር እየሰጠ ከመሆኑ አንጻር የፌዴራላዊ መንግስት ሕገ መንግስታዊ ስልጣን ምንድን ነው? የክልል መንግስታትም ሆኑ የፌዴራሉ መንግስት ስምምነት ለማድረግ መቻላቸው ህገ መንግስታዊ አይደለምን?

3ኛ) የመሬት ኪራይ ስምምነቱ የመሬት ሊዝ ኪራይ ነውን? የመሬት ኪራይ ስምምነት ሁለቱን ሀረጎች በተለዋዋጭነት ይጠቀማል፡፡ ካሩቱሪ የረዥም ጊዜ የሊዝ ስምምነት ፈረምኩ ይላል፡፡

4ኛ) የመሬት ኪራይ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ግልጽ አይደለም፣ እናም በበርካታ ክፍሎች ስለሁለቱ አጋሮች ዓላማ ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ ከካሩቱሪ ቃለመጠይቅ መግለጫ መገንዘብ እንደሚቻለው ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ጋር በርካታ መብቶችን እና ጥቅሞችን በማካተት የሊዝ ስምምነት ለመዋዋል ዓላማ ነበረው፡፡ የዘ-ህወሀት የመሬት ኪራይ ስምምነት ካሩቱሪን እንደ አንድ ተራ ጭሰኛ ተከራይ አድርጎ የሚያስተናግድ ሲሆን በትንሽ ማስታወቂያ ማባረርም ይችላል፡፡ የተዋዋይ አጋሮቹ ዓላማ ከስምምነት ሰነዱ ላይ ያልተወሰነ ከሆነ እነዚህ ስምምነቶች በአጋሮቹ መካከል የህጋዊ የተፈጻሚነት ግዴታ አለባቸውን?

5ኛ) ካሩቱሪ ከእርሱ አቅም በላይ የሆነ መሬት በግዳጅ እንዲወስድ የተገደደ መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡ ስለሆነም አንድ ወይም ሁለት ዓይነት ስምምነቶችን ከፈቃዱ ውጭ በግዳጅ እንዲፈርም የተደረገ መሆኑን ግልጽ አድርጓል፡፡ ካሩቱሪ በህገ ወጥ መልኩ፣ ተገዶ ወይም ደግሞ በጎ ያልሆነ ተጽዕኖ ተደርጎበት የሊዝ ስምምነቱን ወይም ደግሞ የመሬት ኪራይ ስምምነቱን ነው የፈረመው? ይህ ከሆነ አንዱን ወይም ሁለቱንም ለማስወገድ ህጋዊ ድጋፍ ያለው እና ከዘ-ህወሀት እና ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ለደረሰበት ጉዳት በህግ መጠየቅ ይችላልን?

6ኛ) ስምምነቱ በሚረቀቅበት ወይም ደግሞ በሚፈረምበት ጊዜ የጋራ ስህተት ነበርን? ለምሳሌ ዘ-ህወሀት እነርሱ የመሬት ከራይ ስምምነት የገቡ ሲል ካሩቱሪ ደግሞ በሊዝ የኪራይ ውል ስምምነት እንደገባ ያምናል፡፡ ሁሉቱም ወገኖች የተሳሳቱበት ስምምነት የግዳጅ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይችላልን?

7ኛ) በዋናዎቹ ስምምነቶች ሁለቱም አካሎች መካከል የማቴሪያል አለመግባባት ችግር ነበርን? ለምሳሌ ካሩቱሪ ያለመግባባት ግጭቶች በመጨረሻ በድርድር ይፈታሉ ብሎ ሲያምን ዘ-ህወሀት ደግሞ የአካባቢ ፍርድ ቤቶች የተለየ ስልጣን እንደሚኖራቸው ያምናል፡፡

8ኛ) የህግ ግጭቶች በሚኖሩበት ጊዜ (አሁን በእጅ ላለው ጉዳይ የትኛው ህግ ነው መተግበር የሚኖርበት? መፈጸሙ ምናልባትም የማይቀር እንደመሆኑ በማን እና እንዴት ነው ግጭቱ መፈታት የሚችለው?

9ኛ) በሁለትዮሹ ስምምነት መሰረት ዘ-ህወሀት የቀረበለትን የግጭት ማስወገጃ ዕርቅ አልቀበለም በማለት ቢቃወም (እኔ እንደምገምተው መንግስት በሲቪል ፍርድ ቤት አልዳኝም በማለት የሕግ ከለላ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደሚያቀርብ ስለምገምት) ካሩቱሪ ነጻ ዳኝነት ሊያገኝ ይችላልን? (ዘ-ህወሀት በሁለትዮሹ ስምምነት መሰረት የግጭት ማስወገጃ ድርድር አላደርግም ብሎ ቢቃወም ወደፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ላለማድረግ ቻው በማለት ምክንያቱም በዓለም ላይ በግጭት ማስወገጃ ስምምነቱ መሰረት አልገዛም የሚል ማንም አካል መኖር ስለማይችል እና ሁሉንም የኮንትራት ግጭቶችን ለመጨረሻ ውሳኔ ለሀገር ውስጥ ፍርድ ቤቶች የሚቀርብ ይሆናል፡፡ (የይስሙላ የዝንጀሮ ፍርድ ቤት አላልኩም፡፡)

አስረኛውን ጉዳይ እዚህ ላይ አልገልጸውም ምክንያቱም ለብዙ ጊዜ ለተደረገ ትንተና እና ስምምነት ይኸ ጉዳይ ሌሎችን ጉዳዮች ሁሉ ዋጋቢስ እንደሚያደርጋቸው አምናለሁ፡፡ እናም በነጠላ በስምምነት ጉዳዩን በመጣስ የህግ አሸናፊነት እንዲወሰን ወይም ደግሞ አንዳቸው ወይም ሁለታቸውም እንዲያሸንፉ ያደርጋል፡፡ ይህንን አባባል የማቀርበው በሰለጠነ ሁኔታ ነው፡፡

ስለካሩቱሪ- ዘ-ህወሀት የሕግ ውጤት ጉዳይ ደንታ የለኝም ስል ስለቆየሁ እና ግጭቱ በአሁኑ ጊዜ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ለመግለጽ ለእኔ የማስመሰል ስራ ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡

የሕንድ ኃያልነት፣

የካሩቱሪ የፖለቲካ የመጫወቻ ካርድ የህንድ ኃያልነት ነው፡፡

ካሩቱሪ ግራ ለተጋበው ለእርሱ ክፍያ መፈጸም ኃጢያት ነው ይላል፡፡ እኔን ልታስፈራራኝ እንደምትችል ታስፈራራኛለህን? ሂድ እና ከሌላ ቦታ ሞክረው፡፡ ህጉ እስከቀረበ ድረስ መገደድ እንደሌለብኝ መብት አለኝ፣ ሆኖም ግን በጥቂት ፌዘኞች ተታልያለሁ፡፡ በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሹ የክልከላ ስምምነት እኔን ይጠብቀኛል፡፡ እስኪ ትንሽ ንካኝ፣ከዚያ በኋላ የህንድን ኃያልነት ታያለህ፡፡  ይኸ ማስፈራራት ነው ምክንያቱም በቃ በቃ ነው፡፡ እራሴን መከላክል ይኖርብኛል፡፡

ህንድ እና ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ሀምሌ 5/2007 የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

እንደ አንድ የዘ-ህወሀት ይፋ የሆነ ሰነድ ህንድ በኢትዮጵያ 4.8 ቢሊዮን ዶላር በማፍሰስ ሁለተኛዋ ታላቅ የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ሀገር ናት፡፡ በሁለትዮሹ ሀገሮች የጋራ የንግድ ስምምነት መሰረት እ.ኤ.አ በ2013 1.082 ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡ ከዚህ ውስጥ 1.053 ቢሊዮን ዶላር ህንድ ወደ ኢትዮጵያ የምትልከው ንግድ ነበር፡፡ ህንድ 28.210 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው በግማሽ የከበሩ ድንጋዮች፣ ቆዳ፣ ጥጥ እና ሌሎች ሸቀጦችን ያካተተ ነበር፡፡ እንደዚሁ የመረጃ ሰነድ ኢትዮጵያ ከአፍረካ ብቸኛዋ ትልቅ የህንድ ብድር ተቀባይ ሀገር ናት፡፡ ይህም ማለት 65 ሚሊዮን ዶላር ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ለኃይል ማሰራጭ እና ማከፋፈያ፣ 640 ሚሊዮን ዶላር ለ3 የስኳር ፋብሪካዎች ልማት እና 300 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለባቡር ሀዲድ ዝርጋታ ፕሮጀክት (ከአሳኢታ ኢትዮጵያ እስከ ታጁራ ጅቡቲ ወደብ) ሰጥታለች፡፡

ገንዘብ ይናገራል ይላሉ፡፡ የቀረበውን የመረጃ ዳታ በመያዝ ካሩቱሪ “ እስቲ ትንሽ ንካኝ፣ እናም የህንድን ኃያልነት ታያለህ“ ሲል የተሳሳተ እንዳልሆነ አምናለሁ፡፡

የህንድ መንግስት ከውጭ ዜጎቹ መካከል አንዱ በውጭ ሀገር መዋዕለ ንዋይ አፍስሶ በጠራራ ጸሐይ የማፍስስ ስራዋን በማስፋፋት ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የህንድ ኩባንያዎች በዓለም ላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር አፍስሰዋል፡፡ የህንድ መንግስት የካሩቱሪን ጉዳይ ወደ ጎን የሚለው ከሆነ በዓለም በተለይም በአፍረካ ላይ ባሉ የህንድ ኢንቨስትመንቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል፡፡ በሁለትዮሹ ስምምነት መሰረት የህንድ መንግስት የካሩቱሪን መብት በሚያስጠብቅ መልኩ መንቀሳቀስ አመክኖያዊነት ያለው ይመስላል፡፡ በተለዋጩ በህንድ በኩል የማድረግ ውድቀት ከቀጠለ በሌሎች ሀገሮች ላይ ባሉት መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ስሜትን እንዲይዙ ያደርጋቸዋል፡፡

በትክክል ለማስቀመጥ ዘ-ህወሀት ካሩቱሪን እንደተነቃነቀ ጥርስ በመምታት ያጎረሰውን እጅ ይነክሳል፡፡ ሆኖም ግን የደናቁርት ስብስብ የሆነው የዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች የህንድን ኃያልነት የሙቀት መለኪያ ያለጥርጥር ይለካሉ፡፡

ካሩቱሪ በጆቢራዎች እና በቀልደኞች መካከል ተጣብቋልን?

ካራቱሪ ዘ-ህወሀትን እንደ ጆቢራዎች እና ቀልደኞች አድርጎ መቁጠሩ የሚያስደስተኝ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

ይህ ድርጊት “በመካከል ከእራስህ ጋር ተጣበቅ“ የሚለውን የግጥም ስንኝ አስታወሰኝ፡፡ ደህና፣ ዛሬ ማታ ወደዚህ ለምን እንደመጣሁ አላውቅም፡፡ አንድ ነገር ትክክል እንዳልሆነ የሚሰማኝ ስሜት አለ፡፡ አስቂኝ ኮሚኮች ከግራ ጎኔ ቀልደኞች ደግሞ ከቀኝ ጎኔ፣ እኔ ደግሞ እዚህ አለሁ፡፡ ከአንተ ጋር በመካከል ተጣብቂያለሁ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ካሩቱሪ በአሁኑ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ለምን እንደመጣ ያስገርማል፡፡ ከአጋሩ ከዘ-ህወሀት ጋር ከፈጸመው ስምምነት ጋር ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳለ የሚሰማው ስሜት አለ፡፡ አዝናለሁ! እርሱ በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት ቀልደኞች እና አስቂኝ ኮሚኮች መካከል ተጣብቀዋል፡፡ በእነርሱ ላይ እየሳቁባቸው ነው፡፡ (እንደሚስከመከሙ ጅቦች አላልኩም፡፡)

ካሩቱሪንን ሊጠብቀው የሚችለው ብቸኛው ነገር የህንድ ኃያልነት ነው፡፡ ያ ምን ማለት እንደሆነም በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን የህንድ መንግስት በካሩቱሪ ላይ ለተፈጸመበት ማጭበርበር በዘ-ህወሀት ላይ የብቀላ እርምጃ ይወስዳል፡፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች ስለዚህ ጉዳይ ደንታቸው አይደለም፡፡

ህዝባዊ አመጽ በጠቅላላ በሀገሪቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ባለበት ሁኔታ የእራሳቸውን የፍጻሜ ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከሰይጣን እና ከሸፍጠኛ ጋር ስምምነት ማድረግ፣

ቀደም ሲል እንዳልኩተ ሁሉ ካሩቱሪ ለውድቀት የተዘጋጀ አልነበረም፡፡ ስምምነቱን ከዘ-ህወሀት ጋር ባደረገበት ጊዜ መጥፎ ዕድል ገጥሞት ወድቋል፡፡

ከሰይጣን ጋር ስምምነት ስታደርግ ሊከሰት የሚችለው ነገር ይኸው ነው፡፡ ሁልጊዜ ታጣለህ፡፡

በሌላ አባባል ግልጽ ለማድረግ ካሩቱሪ ቤቱን በላስ ቬጋስ ውስጥ ገነባ እናም አጣ፡፡

እንደገና እለዋለሁ፡፡ በዘራፊ ወሮበሎች እና ከዘራፊ ወሮበሎች ጋር ቢዝነስ በሚሰሩ ሰዎች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ ካሩቱሪ እና ዘ-ህወሀት እያንዳንዳቸው ምን እንዳደረጉ ለእኔ ጉዳየየ አይደለም፡፡ እውነታው አልጋቸውን በአንድ ላይ አደረጉ፣ እናም በአሁኑ ጊዜ በአንድ ላይ ይተኙበታል፡፡

ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነት ለማድረግ የጎቴ ፋውስትን ቀስቃሽ ቃላት በመጠቀም መግለጽ ይቻላል፡፡ (በእርግጥ እ.ኤ.አ በ2006 ባዘጋጀሁት ቀዳሚ ትችቴ ላይ የፋውስትን ተመሳስሎ ለማንሳት ሞክሪያለሁ፡፡ ፋውስት ከሰይጣን ጋር ስምምነት አደረገ፡፡ እንደዚሁም ነብሱን ወሰን ለሌለው እውነት እና ከልብ የሆነ ደስታ ማግኘት ነው፡፡ ፋውስት የሚፈልገውን ነገር አገኘ፡፡ ሰይጣን ነብሱን አገኘ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ፋውስት በታላቅ ክብር ተጠበቀ፡፡

ካሩቱሪ በጋምቤላ ላለ ለሁሉም መሬት ነብሱን ሸጧል፡፡ መሬቱን አግኝቷል፡፡ ለአስር ዓመታት ያህል ከዘ-ህወሀት ጋር በጥንካሬ ለሰራው አሁን ነብሱን መቀየር አለበት፡፡ በህንድ ኃያልነት ሊጠበቅ ይችላልን?

ካረሩቱሪ በአሁኑ ጊዜ ሙዚቃውን መስማት አለበት፡፡ የዘ-ህወሀት ጆቢራዎች ላገኛቸው እና ላላገኛቸው ለእያንዳንዷ ሳንቲም ኪሱን ያነሳሉ፡፡ ከዘ-ህወሀት ኢትዮጵያ ባዶ እጁን ይዞ ይሄድ ይሆን?

የቆሰለው የጋምቤላው አንበሳ በጅቦች መመገቢያ ሳህን ውስጥ ይጠናቀቃልን? (ይቅርታ ጆቢራዎች ለማለት ነው፡፡)

የቀረው ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡

ካሩቱሪ ህይወት ፍትሀዊ ያለመሆኑን ማሰብ አለበት፣ አይደል? ምናልባትም የካሩቱሪ ፕሮጀክት ተግባራዊ እንዲደረግ እና የመንደር ምስረታ በሚል በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ጋምቤላውያንን ጥያቄ ማንሳት የተሻለ ነው፡፡

ካሩቱሪ መጥፎ ሰው ነው ብዬ አላስብም፡፡ ሆኖም ግን የዓለም የጽጌረዳው ንጉስ በእንደዚህ ያለ ማጭበርበር ሊወድቅ ይችላል፡፡ በአንድ በቃለ መጠይቁ ወቅት ካሩቱሪ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ደደብ መሆን ነበረብኝ፡፡“ እንደዚህ አላስብም፡፡ በእርግጥ ትንሽ ገብጋባ ነገር ነው፡፡ መለስ እና ግበረ አበሮቹ 100 ሺ ሄክታር በትንሽ ገንዘብ በሸጡለት ጊዜ በምራቅ መሞላበት አለበት፡፡

ስግብግብበት አውዳሚ ነገር ነው፡፡ ሁሉንም ነገር ያወድማል፡፡ ካሩቱሪ ዘግይቶ የተማረው ነገር ይኸው ነው፡፡ ፡፡

ካሩቱሪ በተለይም በአፍሪካ እንደማንኛውም እንደዚህ ያለ ታላቅ የንግድ ኩባንያ እንዳለው ሰው ሁሉ በመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ተግባሩ ላይ ጉዳዮች ነበሩት፡፡ ካራቱሪ አጭበርባሪ ሰው አይደለም ብዬ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን የማይፈልገውን በመቶ ሺዎች ሄክታር የሚቆጠር መሬትን በ5 ወይም በ6 ዓመታት እንዲያለማ እንደሚጠበቅ በማለት መሬቱን እንዲቀበል ከመደረጉ ጋር በተያያዘ መልኩ ተታሏል ብዬ አምናለሁ፡፡

ካሩቱሪ የቢዝነስ ሰው ነው፣ እናም እንደሌሎች የቢዝነስ ሰዎች ሁሉ ትርፍ ማትረፍን ይፈልጋል፡፡ እኔ በዚህ ነገር ላይ ካሩቱሪንን አልወቅስም፡፡ እውን፣ እውን… የተራቡ የኢትዮጵያ ህዝቦችን እና ሌሎችን ለመመገብ ይፈልጋል?

ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ ሊካድ የማይችለው ነገር ካሩቱሪ የእራሱን በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመመደብ የጋምቤላ ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ወጭ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱን የወሰደው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለመክሰር አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ሊካድ የማይችለው ነገር ወደ ኢትዮጵያ የመጣው አንዱ እና የመጀመሪያወ ነገር ትርፍ ለማግኘት ነው፡፡

ካሩቱሪ “ኢትዮጵያን እወዳለሁ“ ብሎ ሲናገር ለማስመሰል ነው ብዬ ለማመን ምንም ዓይነት አመክንዮ አይኖረኝም፡፡ ወይም ደግሞ ይህንን ያለው እራሱን ከህዝቡ ጋር ለማግባባት ነው፡፡ ካሩቱሪ ማለት የፈለገውን ይላል እናም የሚለውን ይላል ብዬ አስባለሁ፡፡ የተናገረው ነገር በፖለቲካ እይታ ትክክል ቢሆንም እንኳ ደንታ የለኝም፡፡

በእርግጥ ካሩቱሪ በጋምቤላ ውስጥ መሬቱን ለማግኘት የሄደበት መንገድ ላይ ግዙፍ የሆኑ ችግሮች አሉኝ፡፡

ካሩቱሪ ወገኖቼን በጋምቤላ ባስተናገደበት፣ ባፈናቀለበት መንገድ ላይ እና በገባው ቃል መሰረት ለወገኖቼ ትምህርት እና የመሰረተ ልማት ባለማቅረቡ ምክንያት ግዙፍ የሆኑ ችግሮች አሉብኝ፡፡ ስለጋምቤላ ህዝቦች ምንም ዓይነት ደንታ የሌለው ሰው በመሆኑ በጥልቅ አዝኛለሁ፡፡

ባለፉት ትችቶቼ እንዳቀረብኩት ካሩቱሪ ፕሮጀክቱን ለማልማት ከጋምቤላ ህዝቦች ጋር መነጋገር ቢችል ኖሮ፣ እነርሱ የሚሉትን ቢሰማ ኖሮ፣ የእነርሱን ችግሮች እና ፍላጎቶች ለማሟላት ግማሽ መንገድ በመጓዝ በጥሩ መንፈስ እና እምነት ጥረት ቢያደርግ ኖሮ ቀላል እና ምቹ ጊዜ ይኖረው ነበር፡፡ ካሩቱሪ ከጋምቤላ ህዝብ ጋር ቢሰራ ኖሮ (ከሌባው ከዘ-ህወሀት ጭፍሮች ጋር ሳይሆን) ስኬታማ ይሆን ነበር፡፡ ሆኖም ግን የጋምቤላን ህዝቦች ዝቅ አድርጎ በማየት፣ ችላ በማለት እና እምነቱን በዘ-ወሀት ላይ በማድረግ ለመዝለቅ ሞክሯል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እራሱን ታስሮ አግኝቶታል፡፡

ካሩቱሪ ከዘ-ህወሀት ጋር ስምምነት ለማድረግ ሲወስን ደፋር ሰይጣን ነበር፡፡ አሁን ግን ሰይጣንን ከደፈርክ፣ ከሰይጣን ጋር አብረህ ብይ የምትጫወት ከሆነ ሁልጊዜም ቢሆን ታጣለህ፣ ትሸነፋለህ የሚለውን ትምህርት ተምሯል!

ካሩቱሪ እንዲህ በሚለው የመልአክት ትምህርት የአዕምሮ ጭንቀት ሰላም ያገኛል፡ “ማንም ጠንክሮ የሚሰራ እና በጥንካሬ የሚኖር ሁሉ አሁንም የልፋቱን ዋጋ ያገኛል፡፡“

ካሩቱሪ በጋምቤላ ለ10 ዓመታት ያህል ላቡን ያፈሰሰበትን አምላካዊ ካሳ ላያገኝ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በህንድ ኃያልነት ካሳ ሊያገኝ ይችላል፡፡

ስለፈሰሱ እንባዎች ከተነሳ ዘንድ በጋምቤላ በእርሱ ፕሮጀክት ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ወደ ድህነት አዘቅት ውስጥ እንዲዘፈቁ ለተደረጉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች አሁን ሀዘን እንደሚሰማው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በጉዳዩ ላይ በጨዋታው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ምንም ዓይነት ምርጫ ሊያኖረው የማይችል ቢሆንም የጉዳቱ ሰለባ የሆኑትን ሰዎች በጋምቤላ የጎርፍ መተኛ ቦታዎች ላይ በዝረራ እንደማይጥላቸው (ቀልድ አይደለም) ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ፋውስት ከሜፊስቶፌለስ ጋር ያደረገውን ስምምነት ካጣ በኋላ በመጨረሻ መኖር እና ማደግ ጀመረ፡፡

ስለሆነም ካሩቱሪም እንደዚሁ ይሆናል!

የደስታ ምንጭ በመሆን ይጠቅም ይሆን በሚል እሳቤ በጌታ ክሪሽና እና በተዋጊው አርጁና መካከል በሂንዱ ቅዱስ መጽሐፍ ያደረጉት ንግግር እንዲህ ይቀርባል፡

“በዚህ ዓለም ላይ ስራን ስራ፡፡ አርጁና እንደ ሰው ምንም ዓይነት ስግብግብነትን ሳያስከትል እራሱን መሰረት አደረገ፡፡ እናም ተመሳሳይ ነገር በማድረግ ስኬታማ ሆነ እና ድል ተቀዳጀ፡፡“

በዘ-ህወሀት ጨዋታ ባልተጠበቀ መልኩ መለያ ካናቴራቸውን ያወለቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጉዳት ሰለባዎች ማን እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡ ጥቂቶች አታላይን ልታታልለው አትችልም በማለት ግኝታቸውን ከባድ በሆነ መልኩ ያስቀምጣሉ፡፡

ካሩቱሪ ለ10 ዓመታት ያህል በጋምቤላ የንግድ እርሻ ልማቱን ለማካሄድ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በ10 ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንዲያጣ ሆኗል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ነገሮች ወደተሳሳተ አቅጣጫ ይሄዳሉ፣ እናም እጅግ በጣም ምርጥ የተባሉት የአይጦች እና የሰው ዕቅዶች አብዛኛውን ጊዜ ከዕቅድ ውጭ ይሆናሉ፡፡ አመንኩ ገበርኩ!

ካሩቱሪ የኢትዮጵያን ህዝቦች ከመውደድ የበለጠ ገንዘብን በመውደድ መዋዕለ ንዋዩን እንዳፈሰሰ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አንድን ነገር ለማግኘት አንድ ነገር ለመስራት ፍቅር ክሪሽማ ለአርጁና የሰጠው ምክር መገለጫ ባህሪ እንደሆነ አምናሁ፡፡ ካሩቱሪ ምንም ዓይነት ስግብግብበነት ሳያስከትል እና የኢትዮጵያን ህዝብ ከማፍቀር አንጻር የሰራውን የሰራ መሆኑን የሚያምን ከሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር አጥቷል፡፡ ሆኖም ግን የመጨረሻውን ሽልማት ለማግኘት በጽናት ይቆማል፡፡ በዘላለማዊ እውነታ ሰነዱ ላይ የወደፊቱን ሁኔታ የሚወስኑ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይኖርበት ነበር፡፡“

ድህረ ጽሑፍ፡

በካሩቱሪ -ዘ-ህወሀት በጩኸት የታጀበ ደስታ ይህ ግጭት ወደፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ መዋዕለ ንዋይ የመጨረሻ ፋይዳ ሊኖረው እንደሚችል ማንም ሊረሳው አይገባም፡፡

ካሩቱሪ ዘ-ህወሀት ማንኛውንም የውጭ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ከሀገር ውስጥ እያባረረ ነው ይላል…

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!         

የካቲት 9 ቀን 2008 .

 

Filed in: Amharic