>
9:08 am - Sunday January 29, 2023

ሐብታሙ አያሌው ሆስፒታል ገባ [ዳዊት ሰለሞን ]

Habtamu Ayalew- Andinet Party”የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ሐብታሙ አያሌው በግፍ እስር ወህኒ ቤት ከተወረወረ በኋላ በህገ ወጥ መርማሪዎች በደረሰበት ድብደባና ማሰቃየት ለህመም ተጋልጦ ጤንነቱ መቃወሱ ሲነገር መቆየቱ አይዘነጋም፡፡
ሐብታሙ ከወህኒ ቤት ከወጣ በኋላ ህክምና ለማግኘት ወደ ውጪ አገር ለመውጣት ሙከራ ቢያደርግም ስርዓቱ የመንቀሳቀስ መብቱን በማፈን ህክምና እንዳያገኝ አድርጎታል፡፡አሁን ሐብታሙ በድንገት ታምሞ ለሆስፒታል መዳረጉን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሐብትሽ የህዝብ ልጅ አምላክ መድሃኒቱን እንደሚልክልህ ተስፋ በማድረግ ፈውስን እመኝልሃለሁ፡፡” በማለት ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ሃብታሙ ኣያሌው የደረሰበትን ሁኔታ በፎቶ ኣስደግፎ በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ የገለጸ ሲሆን፤ ኢትዮ ሪፈረንስም ወጣት ሃብታሙ ኣያሌውን ፈጣሪ ምህረቱን ያወርድለት ዘንድ እንመኛለን።

 በዛሬው ዕለት (29.06.2016) ኤሊያስ ገብሩ ስለ ሃብታሙ ኣያለው

የወንድማችንን ሀብትሽን ህይወት ፈጣሪ ይታደጋት። ሀብትሽ ባላፉት 15 ቀናት ሁለቴ ህክምና ማድረጉን አውቃለሁ። የመጀመሪያውን ህክምና “ስቃዩ ተጀመረ” ሲል የትግል አጋሩ ዳንኤል ሺበሺ ያነሳውን ፎቶ ግራፍ በ inbox ልኮልኝ በድንጋጤ ተውጩ አይቸው በስልክ ስለህመሙና ህክምናው ረዘም ላለ ደቂቃ አውርተን ነበር። ሁለተኛውንም ህክምና ቅዳሜ አድርጎ እቤቱ ቢገባም ትናንት በጣም ሲያማው ሆስፒታል ገባ። አሁን ባልኝ መረጃ ሀብትሽ ከቤተዛታ ወደ ካስዲኮ ሆስፒታል ሄዷል። ቤተዛታ ሙሉ ቀዶ ጥገና እናድርግለት ቢሉም ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሃም አዛናው በዚህ አልተስማማችም። ሃብታሙም ሙሉ ቀዶ ጥገናው በጣም ለህይወት አስጊ መሆኑን ነግሮኝ ነበር። …ከኮማ ውስጥ አሁንም አልወጣም ተብያለሁ። እንጸልይለት ከማለት ውጪ ምን ልበል?

ኣቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ፤ ሃብታሙ ኣያሌው ያለበትን ሁኔታ እንደገለጹት

ያለ ጥርጥር ፀሎታችን ይስማል፡፡ በነገር የማይሳሳተው እግዚሐብኤር ወንድማችንን ምሮት ክፎዎችን ያሳፍርልናል፡፡ በስቃይ የሚደሰቱም አንገታቸውን ይደፋሉ፡፡ ወንድማችን ሀብታሙ አሁን ከድንገተኛ ከፍተኛ ክትትል ከሚደረግበት ክፍል ወጥቶ ወደ መደበኛ የክትትል ክፍል ገብቶዋል፡፡ ቀጠይ ህክምናውን ለማግኘት አሁን ከደረሰበት ጉዳት ማገገም እንዳለበት ሀኪሙ ነግሮናል፡፡ ጥሩ የሚባል ሀኪም እያየው ስለሆነ ፈጣሪያችን በሐኪሙ ላይ ጥበብን አውርዶ ፈፅሞ እንዲምረው ፀሎታችን መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በተረፈ በመረበሸ እና እርግማን የሚገኝ ነገር የለም፡፡ ተረጋግቶ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ሕክምናው የተሳካ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ከውጭ በተለይ ለባለቤቱ ስልክ የምትደውሉ ወዳጆች ሆድ ከሚያስብስ የሀኪምን ክትትል ከሚጎዳ አስተያየት ብንቆጠብ ጥሩ ነው፡፡ ደውላችሁ ማፅናናታችሁ ፍሬ የሚኖረው ቤቲ ስትጠነክር ነው እንጂ በሐዘን ስተጎዳ አይደለም፡፡ ቤቲ ለሀብታሙ ለልጇም ጠንክራ መገኘት ስለሚገባት በዚሁ መስመር ድጋፍ አድርጎላት፡፡ እስከ አሁን ከሁሉም መስመር ለምታደርጉት በጎ ነገር ሁሉ ፈጣሪ አብዝቶ ይባርካችሁ፡፡ ተባረኩልን፡፡ ኮርተንባችኋል እና ኩሩ!!!

(ዳንኤል ሺበሺ)

ስለ ሀብታሙ አያሌው የዛሬ ውሎ (30.06.2016)

በርግጥ በርካታ ወዳጆቻችን ዛሬ ሀብታሙን ሊጎበኙ ገርጂ ወደሚገኘው ካዲስኮ አጠ/ይ ሆስፒታል ሲተምሙ ነው የዋሉት። ሁሉም ያስተዋለውን ነገር ወዳልሰሙ ሲያደርስ እንደዋለ መረዳት ችየዋለሁ። ዛሬ ከሰዓት በፊት ነበር ትላንትና ካደረበት ዋሽንግተን ህክምና ማዕከል በሪፌር ስቴዲየም አከባቢ ወደሚገኘው ቤቴዛታ ሆስፒታል በከፍተኛ ፍጥነት ያመራነው። እዛ ስንደርስ የሰነቅነው ተስፋ እንዲሁም ጉም መጨበጥ ሆነብን። የመረመሩት ሀኪሞች በቃሬዛ ላይ እንደአስክረን ጠፍረው ወደ ሆስፒታሉ አሙቡላንስ ውስጥ አስገቡትና በአስቸኳይ ገርጂ ወደሚገኘው ካዲስኮ አጠ/ይ ሆስፒታል አድርሱ አሉን። አምቡላንሷ አስፓሊቱን፣ የአሙቡላንሷ ጩኸት አየሩን መቅዘፍ ጀመር። ይሄ ሁሉ ሲሆን ወንድሜ ሀብታሙ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የዘመድ አዝማድ፣ የጓደኛና የትግል አጋሮቹ ውሃ ያቆሩ አይኖችን ማየት ውስጥህን ያሸብራል።

ወደ ካዲስኮ ሆ/ል እንደረስን እንዲተኛ ታዘዘ። አሁንስ በምን ሁነታ ውስጥ ይገኛል የሚለው ጥያቄ ፣፣፣፣ ከትላንትናው ይሻላል ልበል?? አልፎ አልፎ ቢሆንም አይኖቹን የመግለጥ፣ እጆቹን የማንቀሳቀስ ሁኔታ አለ። በንፅፅር ዛሬ ሳይሻል አይቀርም። ህክምናውን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ማስታገሻዎችን ከመስጠት ውጭ ወደ ዋናው ህክምና ገና አልተገባም። ያ! መብረቅ፣ ዛሬ በአልጋው ላይ ውሃ እንዳራሰው ወፍጮ ልስልስ ብሎ ማዬት መንፈስን ምነኛ ያውካል መሰላችሁ??
ፀሎት! አምላካችን ለተበደሉት፣ ለተገፉት እውነተኛ ዳኛ፣ ትክክለኛ ፈራጅ ነው!!!

Filed in: Amharic