>
5:13 pm - Tuesday April 18, 3978

የጀግናው ስም ህያው ነው …[ነቢዩ ሲራክ]

* የጀግናው ስም ህያው ነው  …
* ጀኔራል ለገሰ ተፈራ አልፋና ኦሜጋ በክብር ይዘከራሉ  !

Bergader Jenaral legese Tefera by Nebiyu Sirak 1የኢሬቻው እልቂት ሀዘን ከብዙዎች አንጀት አልወጣ ብሏል ፣ እልቂት ፍጅቱን በመቃወም በመላ አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍ ያለ ትዕ ይንተ ህዝብ በማድረግ ላይ ናቸው ። የኢሬቻውን እልቂት ፍጅት የፖለቲ ካውን ምህዳር አክርሮት ፣ የፖለቲካው ትኩሳቱ ግለት ሀገራችን እንዳይ ፈጃት በሀዘን ላይ ሆነን በጸሎት ምህላ ፈጣሪን እየለመንን  ባለበት ወቅት ላይ አንድ  የደብረ ዘይት አቢሸፍቱ  አየር ኃይል ያሳደቻቸው ጉም ቱ የሀገር አድባር ጀግናው ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተረፈ በስደት ባሉበት በሃገረ አሜሪካ በጠና መታመማቸውን ሰማን  … ብዙም ሳይቆይ መስ ከረም 25 ቀን 2009 ዓም በጠና ታነው በህክምና ሲረዱ የሰነበቱት ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በተወለዱ በ84 ዓመታቸው በክብር ህይዎታቸው የማለፉን መርዶ ከዋሽንግተን ዲሲ ተሰምቷ

ልባችን በሃዘን ተሰብሯል 🙁

በእሳት ተፈትነው ፣ ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር የሰጡት ጀግና የብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተፈራ መረዶ  በእርግጥም በሀዘን ላይ ላለን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያንንከመርዶም የከበደ መርዶ ሆነ ፣ የገዘፈ የተጋድሎ ታሪካቸው በመላ ሀገሪቱ ሲነገር  በቅርብ የማያውቃቸውና በዝና የሚያውቃቸው ሁሉም የሀገሬ ሰው በነቂስ አዝኗል  🙁

የፍቅርና የፖለቲካ መጻሕትን ከማንበብ  ይልቅ ጥናታዊ ዘገባዎችን ፣ ግለ ታሪኮችን ማንበብ ፣ በቅርቤ ካሉት አረብ አባቶች የቀደመውን የአረቦችና የኢትዮጵያ ታሪክ ማድመጥ የሚቀናው ነፍሴ ፣ የብርጋዴር ጀኔራል ለገሰን ተፈራ  የጀግንነት አኩሪ ጀብዱ ከባለሙያዎችና ከታሪክ ዘካሪ መዛግብትና መጣጥፎች ፣ ብሎም ከአይን እማኞች ብዙም ሰምቻለሁ … ዛሬ ህልፈተ ህይዎታቸውን ተከትሎ በክብር የማዘክራ ቸውን ጀግናዬን መረጃ ያሰባሰብኩት ከሰማሁ ፣ ካየሁና ካነበብኳቸው ዝክረ ታሪኮች በመነሳት ይሆናል   !

የጀግናውን ባለ ንስር አይን የጦር ጀት አብራሪ የጀኔራል ለገሰ ተፈረ  አስደናቂ ታሪካቸውን መረጃ ከሰጡኝ መካከል  የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባልደረባ የነበሩና አሁን ላይ  ሳውዲ የከተሙ ወዳጆች ብዙ ያካፈሉኝ ትዝታ አይዘነጋኝም  ። ስለ አየር ኃይል በረራው ድንቅ ውስጠ ታሪክ ሲነሳ ደጋግመው በስሜት ሲያጫውቱኝ ከማልሰለቻቸው ታሪኮች ውስጥ አንዱ የጀኔራሉን የጦርነት የጀግንነት ውሎ ነው ። የጀግኖችን ገድል የደርግ ጦር በፈረሰ ማግስት ወደ ሳውዲ ተሰደው ከመጡት  የምድር ጦርና የአየር ኃይል ከዝቅተኛ እሰከ ከፍተኛ መኮንኖችን  የማግ ኘት እድል አጋጥሞኝ ” እህ !” ብዬ አዳምጫለሁ  ፣ ከበረራው ውስብስ ብነትና ከባድ ኃላፊነትና ዲሲፕሊን ጋር በዝና ስመቸ አደንቃቸ ው ከነበ ሩት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል ከቅድመ መፈንቅለ መንግስትና በግን ቦት 8 ቀን 1981 ዓም መፈንቅለ መንግስት ያለቁትን ጨምሮ የብዙዎቹ ታሪክ ተሰ ምቶ አይጠገብም ፣  ከሰማሁት ሁሉ ታሪክ በእሳት የተፈተ ኑት ፣ በሶማሊያው እብሪተኛ መሪ የፕሬዚደንት ዚያድባሬ ጦር እጅ የወደቁትና በኋላም በምርኮኛ ምልልስ ሀገራቸው ቀይ ምንጣፍ አን ጥፋ ፣ ጉንጉን አበባ ስለ ክብራቸው አጥልቃ የተቀበለቻቸው የላቀ ጀብዱ ባለቤት ሽኝት በእርግጥን ቢያሳዝነንም የጀግናችን መለየት ተጎድተን በኩራትና በክብር እያዘከርን እንሸኛቸዋለን   !

ባለ ንስር አይኑ ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰን ተሰማ ማን ነበሩ  ?

ጀኔራል ለገሰ ተፈራ አባት አቶ ተፈራ ወልደ ስላሴና  ከእናታቸው ከወ/ሮ ተናኛ ተክለ ወልድ ይባላሉ ፣ ጀኔራል ለገሰ ተፈራ ውልደታቸው አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሾላ ተብሎ በሚጠራው ቦታ እንደሆነ  ዝክረ ታሪካቸው ያስረዳል ።   ህፃን ለገሰ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ  በተለመደው የባህል የቄስ ትምህርትን የተማሩ ሲሆን ከዚህ ም በኋላ ቤተሰቦቻቸው ጋር ቅርበት ባላቸው ወዳጅ በነበሩት ጀኔራል አቢይ እርዳታ ኮተቤ ደጃዝማች ወንድ ይራድ ትምህርት ቤት በማስገባት ባለ ብሩህ አዕምሮውን ለገሰን ከልጆቻቸው ሳይለዩ ፍፁም በሆነ ፍቅር እንዳሳደጓቸው ይነገራል። ሐረር አካዳሚ እና አየር ሃይልም ውስጥ ለለገሰ እንዲገቡ የተመረጠላቸው በግርማዊ ጃንሆይ አማች በጀኔራል አቢይ አበበ አማካኝነት ሲሆን ወቅቱም በ1956  ዓም  እንደ ነበር ዝክረ ታሪካቸው ያስረዳል  !

ለገሰ የተቀላቀሉት  የሐረር አካዳሚ በልዩ ባለሙያዎች የተዋቀረና የተደራጀ ብቸኛ የላቀ ወታደራዊ መቅሰሚያ ማዕከል መሆኑ ይነገራል ። ማዕከሉ እንደ እንግሊዙ ”  ሳንድኽረስት ሮያል አካዳሚና”  እንደ አሜሪ ካኑ ስመጥር “ዌስት ፖይንት ” ወታደራዊ አካዳሚ የጠለቀ የውጊያ ስልት፣ የአመራር እና የአስተዳደር ችሎታ፣ የአካል ብቃት በኮሌጅ ደረጃ የሚሰጡ የቀለም ትምህርቶችን፣ የወታደራዊ ሳይንስ ስነ ምግባር በማስተማር ልዩና አይነተኛ የሆኑ መኮንኖችን ከአካዳሚው ይፈጠሩ እንደነበርም ከተጻፉ ድርሳናትና በስልጠናው ካለፉ መኮንኖች በሰፊው ይጠቀሳል ። ለገሰ በሐረር አካዳሚ ስልጠና ላይ በወቅቱ የመከላከያ ሚኒስትር አየር ሃይል ለበረራ የሚቀበላቸው እጩ መኮንኖች በቂ የሆነ የወታደራዊ ስልጠና ያገኙ መሆን አለባቸው የሚል መመሪያ አወጣ ።  ይህን መመሪያ ተከትሎ የአየር ሃይል ትምህርት ክፍል ሐረር የጦር አካዳሚ እየሄደ ሲመለምል የያኔው ተራ መኮንን ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሚፈልገውን መስፈርት አሟልተው ከተመረጡት መኮነንኖች መካከል አንዱ ሆኑ ።  የአየር ሃይል የበረራ ት/ቤት ተቀላ ቅለው በቀጣይ አመታትም የበረራ ትምህርታቸውን ጨርሰው ክንፋቸ ውን አገኙ ፣  ለገሰም ጀት አብራሪ እና የበረራ አስተማሪ ሆነው ተመረቁ  !

ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በሀገር ውስጥ ካገኙት የበረራ ትምህርት በተ ጨማሪ ህይዎታቸው መጨረሻ ወዳረፈችበት ሀገረ አሜሪካ ተጉዘው ከፍ ያለ ወታደራዊና የበረራ ትምህርት ቀስመዋል። በተለይም በአሪዞና የአየር ሃይል ማሰልጠኛ ተቋም ከበረራ ጋር የተያያዘ መሳሪያ አጠቃቀ ምን አጥንተዋል  ።  በወታደራዊ ትምህርት የላቁት ለገሰ ራሳቸውን ጠብቀው የሚመገቡ በመሆናቸው ሽንቅጥ ያሉ ደልዳላ አብራሪ እንደ ነበሩ ይነገራል ።  ጀኔራል ለገሰንና የየሚያውቋቸው  ትከሻው እና ደረቱ ሰፊ  የአየር ኃይል  ደልዳላው መኮንን እያሉ ይጠሯቸው ነበር ።  ለገሰ ራሳቸውን ከመጠበቅ ባከፈ በትምህርታቸው ምጡቅ ከሚባሉት ምስጉ ን ተማሪዎች መካከል አንዱ እንደነበሩ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ !  ለገሰ በወታደራዊ የላቀ  ትምህርት ብቻ ሳይሆን  በሙዚቃ ፣ በስፓርት እና በሌሎችም እንቅስቃሴዎች ተሰጥዎ የተካኑ ነበሩ ።

የ ጀኔራል ለገሰ ዘመን ተሻጋሪ ገድል …

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የግዛት ዘመን ጀምሮ እስከ ደርግ አገዛዝ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ጉልህ እንቅስቃሴን በማደረግ በቀዳሚነት ከሚጠሩት ጀግኖች መካከል  ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በፈጸሙት ገድል ከቀሩት ለየት ያደርጋቸዋል ።  ከፈጸሟቸው አን ጸባራቂ ገድሎች መካከል በብዙዎች ህሊና የማይጠፋው በፕሬዚደ ንት መሐመድ ዚያድባሬ የምትገዛው ሶማሊያ ኢትዮጵያ የወረረችበት ወቅት ነበር ።  ጃንሆይን አሽቀንጥሮ የጣለውን አብዮት ገና የለጋ እድሜ እያለ ሀገር በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምና ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ በወደቀች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ከውስጥና ከውጭ ችግሮች ፈጠው መጡ  ፣ በተለይም በሰሜን የመገንጠል ጥያቄ  የሚያቀነቅኑት የለኮ ሱት ጦርነት ፣ በመካከልና በቀረው የሀገራችን ክፍል ደግሞ በተለያዩ የፖለቲካ ደርጅቶች ሽኩቻ ደርቶ አለመረጋጋት ይስተዋል ነበር ። ወቅቱም  ወርሃ ሃምሌ 1969 ዓም ነበር ።

በዚህ ወቅት ነበር የሶማሌው ፕሬዚደንት መሀመድ ዚያድባሬ አለመ ረጋጋትና ውጥረቱን እንደ ድክመት በመቁጠር በውጭ ጠላቶቻችን ”  አይዞሽ ”  ባይነት  ሶማሊያ ኢትዮጵያን ወረረች …  ሶማልያ አውጥታና አውርዳ እጅግ ብርቱ የጦር መሰናዶ አድርጋ በዘመተችበት ዘመቻ የተደ ራጀ የአየር ኃይልና የምድር ጦር ስለመኖሯ እንጅ ከኢትዮጵያ አንጻር የሚጠብቃትን ምላሽ ያሰበችው አልነበረም ።  እናም ያላሰበችው ፈተና ገጠማት ፣ ባለ ንስር አይኖቹ ጀግና የአየር ኃይል አብራሪዎች ከሰማይ ፣ አነጣጥሮ ተኳሾቹና ቁጡ አንበሶቹ  የምድር ጦር ጀግኖች በአጭር ታጥቀው እስከ አፍንጫዋ የታጠቀችውን ሶማሊያን ገጠሟት ፣ ቆፍጣ ኖቹ እንደ አንበሳ እያጓሩ እንደ ነበር እየተፈነጠሩ የሶማሊያን ወራሪ ልክ ልኳን ሰጧት ፣ ሶማሊያ የሃፍረት ማቅ ለብሳና ዋጋዋን አግኝታ ፣ አከርካ ሪዋ ተሰብሮ ወደ መጣችበት ተባረረች  ! የሶማሌን ወራሪ አከርካሪ ይሰብሩ ከነበሩት ጀግኖች መካከል ደግሞ በአየር ላይ ዘመቻው የብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራና የጓዶቻቸው ውሎ ፍጹም ወደር ያልተገኘላቸው ነበር . ..

በወቅቱ በብዛትና ጥራት ከፍ የበላይነት ይዛ የተሰለፈችው ሶማሊያ ብትሆንም ፣ በምጡቅ ልጆቿ ተጋድሎ የነበረው እንደልነበረ በተደረገ በት አገርን ከወራሪ የመታደግ ተጋድሎ የጀግናው አየር ሃይል ዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረባ የነበሩት ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ እና ጥቂት ጓዶቻቸው ሰማዩን ተሚቆጣጠሩ ፣ የማይያዙ የማይጨበጡ ተዋጊ ጄት አብራሪዎች ነበሩ ።  የብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ የዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረባጓዶቻቸው በሶማሊያው ጦርነት በፈጸሙት ተጋድሎ እሰከ ድሬድዋ ዘልቆ የገባውን እብሪተኛ የሶማሌ ጦር ዶግ አመድ ማድ ረግ ችለው ነበር ። በተለይ ጀኔራሉ ለገሰ ከዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረቦቻቸው ጋር በቅንጅት ተዋግተው ወራሪው የሶማሌ አየር ኃይል ጀት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት አደርሰው ጠላት እንዲያፈገፍግ አድርገዋል ። ብ/ ጀኔራል ለገሰ በዚህ የጦር ውሏቸው  እስከ አምስት የሚደርሱ ጀቶችን ያወደሙበት የጦር አውድማ ታሪክ ድንቅ ከተባሉት መካከል ይጠቀሳል …

ዘጠነኛው ስኳድሮ ተዋጊ ባልደረባ አብራሪው ብ/ጀኔራል ለገሰ በተከታታይ ድብደባ የተሰጣቸውን ኢላማን በማደባየት ላይ እንዳሉ በአንዱ ቀን በጠላት ኢላማ ውስጥ ወደቁ ፣  ጠላትን ያደባዩባት ጓዳ ቸው ያች የሚወዷት ጀት ተመታች ፣  በታጠሩና በጨነቀው ሰአት ጀቶ ችን እርስ በእርስ በማጋጨት የሚያወድሙት አሻግረው በሚሳየል የሚ ያደባዩት ጀግና ጀታቸው ተመታ ስትወድቅ እርሳቸው በዣንጥላ በጠላት መሬት አረፉ  ! ጀግናው በጠላት እጅ ወደቁ  ፣ የጀኔራል ለገሰን ጀት አል መው መትተው ፣ ጀኔራሉን በምርኮ የያዙ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስ ልጣናት ጮቤ ረገጡ ፣ እናም  ከተያዙበት ቀን ጀምሮ ለ11 ዓመታት የጦር ምርኮኛ ሆነው በሶማሊያ ወህኒ  ለእናት እትዮጵያ ፍዳን የተቀበሉ ጀግና ቢኖሩ ባለ አንጸባራቂ ድሉ ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ ናቸው !

የቀድሞ የአየር ኃይል አባላት ጀኔራሉ ባሳለፉት የውጊያ ጥበብና ስለአየር አብራሪነት ድንቅ የተጋድሏቸው  ጊዜያት በቅርብ ሲመሰክሩ ባለ ነስር አይን ፣ ብሩህ አዕምሮና ደፋር  ልብ ያላቸው ጀግና ስለ መሆ ናቸውን ይመሰክራሉ” ከሰማይ ሆነው መሬት ላይ ያለውን ዝንብ ማየት ይችላሉ  ፣ ፈጣን አእምሮ አላቸው። የግምት ምናባቸው ሊታመን አይ ቻልም፣ ለገሰ የተለየ የአየር ላይ መገለባበጥን ቢችሉም ኢላማ ማስገ ባት ቢቀናቸውም አውሮፕላንን በአጠቅላይ አጠቃቀሙን እና አያያዝ የሚወዳደራቸው የለም ። ”  ሲሉ ያወድሷቸዋል  !

” ሱማሌን ጦርነት እንደ ተራ ውጊያ እንደ አዋጊ በመሆን ወር ባልሞላ ጊዜ አለ የሚባለውን የሱማሌ የአየር እና የምድር ጦር ሾቅ እንዲል አድ ርገዋል ።በግላቸው ስድስት የሱማሌ አውሮፕላኖች በአየር ላይ ውጊያ መጣላቸውን ከቀድሞ አየር ኃይል አባላት ማህበር ያገኘሁት ዝክረ ታሪካቸው ያስረዳል ።

በአውደ ውጊያው እለታት  ባንዱ ቀን በጀኔራል ለገሰ መማረክ ዙሪያ የተጻፈው ዝክረ ታሪክ እንዲህ ይላል ” ለገሰ ለጓዳቸው  የጠላት ጦር ምን ዓይነት አሰላለፍ እንዳለው ለማየትና ለመንገር እጅግ ዝቅ ብለው ወረዱ ። የወታደሮቹን ጭንቅላት የመንካት ያህል ዝቅ ብለው በረሩ። ያዩትን ለመስፍን ተናገሩ ። ስፍራው የዋቤ ጅረት ነበረና ጠመዝማዛ ነው ። ወታደሮች ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ የዕውር ጭፍናቸውን ተኮሱ ። ለገሰም ወደ ላይ ለመነሳት የአውሮፕላናቸውን አፍንጫ አነሱ ። አውሮ ፕላኗም 75% ተነሳቸ ። በዚህ ጊዜ ወደ ኋላቸው ( ሬዳር ) አካባቢ ከፍተኛ ’ ጓ ‘ የሚል ድምፅ ሰሙ ። በደንብ ነቀነቃቸው። የተመቱ ግን አልመሰላቸውም ። ሁኔታውን ላሸናፊ ለመንገር ሬድዮናቸውን ቢሞክሩ እምቢ አለ ። ግንኙነት ማድረግ የደም ዝውውር ነው ። አሁንም ሞከሩ እምቢ አለ ። የአደጋ ጊዜ የመጠቅሚያን ሞከሩ አልሰራም ። ወደ ኋላ ዞር ብለው ሲመለከቱ ጭስ በጭስ ሆኗል ። ጭሱ እሳቸውን ለመዋጥ እየተሳበ እየመጣ ነው ። አደገኛ ጭስ ፣ ሙቀትም ተከሰተ ። አውሮ ፕላኗ ኃይሏ እንዳለ ነው ። ትንሽ ትሂድና ከጠላት እይታ ልዳን ብለው በረራ ቀጠሉ ። አውሮፕላኗ ከዳቸ … እንድ ጊዜ-ለገመቸ- ክደት አመ ጣች ። መውረድ ጀመረች። በለገሰ ላይ ተለወጠቸ ።ለገሰም ዘለሉ ። ከአውሮፕላኑ ጋር አብሮ ላላመቃጠል እንጂ ፓራሹቱ በደንብ የሚዘረጋ በትና የሚሰራበት ተገቢ ከፍታ ላይ አልነበሩም ። እጅግ ዝቅ ብለዋል ። በድፍረት ግን ዘለሉ ። ከፍታ ስላልነበረው የጠላት ወታደሮች ፓራሹቱ ሲወርድ አላዩትም ። የአውሮፕላኗ ሬድዮ ባለመስራቱ አሸናፊና መስፍን ተገቢውን እርዳታ ሊያደርጉላቸው አልቻሉም ።(  መስፍን ኃይሌ የለገሰ የልብ ጓደኛ ናቸው ።) … አየር ላይ ብዙ ሳይቆዩ ወረዱ ። ከጠላት አካባ ቢ ይውደቁ እንጂ ሲወድቁ ጠላቾች አላይዋቸውም … ወዲያውኑም ሊይዟቸው አልመጡም  ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ወድቀው በማግ ስቱ አራት ሰዓት ገደማ ነበር ስድስት የታጠቁ የሶማሌው ኰሎ ኔል አብዱላሂ ዩሱፍ ወታደሮች እጅ ወደ ላይ ብለው የማረኳቸው ።” ሲል በጠላት እጅ ስለወደቁበት ታሪክ ያዘክራል !

ብርጋዴር ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በሶማሊያ ጦርነት ለከፈሉት የመስዋዕ ትነት ታላቅ ተጋድሎ ከኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም እጅ የህብረ ተሰባዊት ኢትዮጲያ የመጨረሻ ከፍተኛ ኒሻን ከተሸለሙት ጥቂት ኢት ዮጵያውያን መካከል አንዱ ለመሆን የበቁ ድንቅ ሀገር ወዳድ አርበኛ ነበሩ  !  የኪውባው የአሁን መሪና የቀድሞ ጀኔራል የአሁኑ የኩባ ፕሬዚ ደንት ራውል ካስትሮ ሌላ የጀግንነት ኒሻን ተበርክቶላቸዋል  ። ጀግናው ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል በተደረገ የጦር ምርኮኞች ምልልስ መሰረት በክብር ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ወደ አሳደጋቸውና ወደ አስተማራቸው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተመል ሰው የበረራ አስተማሪ በመሆን ትውልድን በማነጽ ግልጋሎት ለሀገራ ቸው ታላቅ መስዋዕት የከፈሉ ጀግና ነበሩ  !

የመንግስት ለውጥ መምጣቱን ተከትሎና ከህመም እክል ጋር ወደ ምድረ አሜሪካ ያቀኑት ጀግናው ጀኔራል በቀድሞው የአየር ኃይልና በመላ አለም የሚገኙ አድናቂ አፍቃሪዎቻቸው ለምንወዳት ሀገራችን  ለከፈሉት ከባድ መሰዋዕትነት ተደጋጋሚ ምስጋናና የክብር ሽልማት የተሰጣቸው ጀግና ነበሩ  !  አኩሪ ገድልን የፈጸሙት ብ/ጀኔራል ለገሰ  ከወጣትነት እስከ ጎልማሳነት እድሜ የእናት ኢትዮጵያን የአየር ክልል ሳያስደፍሩ ካቆዩን የቁርጥ ቀን ልጆች ጋር ሀገራችን ከነክብሯ አስረክ በውናል ፣ በተከፈለው ከባድ መስዋዕት ልክ ሃገርና ህዝብ ውለታ ካልከፈልናቸው ባለውለታዎቻችን አጋፋሪው የጦር ገበሬ ከሀገራቸው ርቀው በስደት እስከ ወዲያኛው አሸልቧል   !

የጀግናችን የመጨረሻ ስንብትና ሽኝት ሀገር በክብሯ ሆና ፣ ኢትዮጵያ የወራሪን ጦር አከርካሪ ለሰበረ ጀግናዋ ነገሪት ጎስማና ለክብራቸው መድፍ ተኩሳ  የምትከውንበት ጊዜው  ዛሬ ባይሆንም ጀግናችን አዘክ ረን እያለቀስን ሳይሆን እያመሰገንን እንሰነባበት ዘንድ ግድ ሆኗል … !

ክበር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን  ፣ ብ/ጀኔራል ለገሰ ተፈራ አልፋና ኦሜጋ ከትውልድ ትውልድ በክብር ይዘከራሉ  !

ነፍስ ይማር  !

መስከረም 27 ቀን 2009 ዓም

Filed in: Amharic