>
5:13 pm - Sunday April 20, 4955

በአስቸኳይ ውረዱ ላለ ሕዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምላሽ አይደለም! [ሃብታሙ ኣሰፋ]

awaj awajመጀመሪያ ሕወሃት በአስቸኳይ ተሰበሰበ።መመሪያ ሰጠ:፡የሚኒስትሮች ም/ቤት ተሰበሰበ እና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።ሀይለማሪያም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ በመግለጫ አወጁ።ከወረቀት ያልዘለለው ሕገ መንግስት አዋጁ አስቸኳይ አዋጅ አለ ተብሎ ሲታሰብ የሚኒስትሮች ም/ቤት ተሰብስቦ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል። የተወካዮች ም/ቤት አዋጁን ተገባራዊነቱን ባያቆመወም ያጸድቀዋል ይላል። በምርጫ 97 አቶ መለስ ለይስሙላም ቢሆን ሚኒስትሮቹን መጥራት ሳያስፈልጋቸው ከሕግ ውጭ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጁ።ወታደራዊ እዝ ስር አስገቡ።ህወሃት ዛሬም ያንኑ ደገመ።ሕገ ወጥ አዋጅ። ለውጥ ላለ ሰላማዊ ጥያቄ ላቀረበ ፣ ቄጤማ ለያዘ ሕዝብ በጥይትና በማሸበር ምላሽ ሲሰጥ ተው ሰከን በሉ ሲባል አልተሰማም። ዛሬም ያንን የአፈና መዋቅር ለማስቀጠልና በሕዝባዊ ተቃውሞ መተንፈሻ ላጣው ስርዓት የአስቸዃይ ጊዜ አዋጅን እድሜ ማራዘሚያ ለማድረግ የወጠነው ውጥን ተቀባይነት የለውም:፡ ጨዋታ ቀይሩ። ሳትዋረዱ ውረዱ። ተለጣፊ ተቃዋሚ ተለጣፊ የሲቪክ ማህበራት በማደራጀት ተመካከርን ልትሉ ማሰባችሁ ወድቀታችሁን አያስቀርም ።እድሜያችሁን ሊያረዝሙ የተሰበሰቡ የፓርቲው ታዛዥ ስመ የሐይማኖት መሪዎችና እነ ሐይሌ እንኳን በትንሹ ትላንት የመከሩትን ያልሰማ ስርዓት የቱን ንግግር ከማን ጋር ነው የሚነጋገረው? አንዴ የግብጽ ሌላ ጊዜ የሻዕቢያ ተላላኪ እያለ ሰለማዊ ጥያቄ ያቀረበውን ሕዝብ ዐየገደለ፣እየተሳደበ ከማን ጋር ነው የሚነጋገረው? ሳትዋረዱ በሌሎች አገራት እንደተደረገው ደም ማፍሰስ ይበቃል በሉና ከስልጣን ውረዱ ።በተጨማሪ ማስፈራራት ቀድሞ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የአወጃችሁትን አስቸኳይ አዋጅ ዛሬ ብሄራዊ መልክ ስለሰጣችሁት ውድቀትንም ውርደትንም አታስቀሩም።ይሰማል እሬቻ ላይ የፈጸማችሁት ጭፍጨፋ ለምን ሕዝባዊ ጥያቄ ቀረበ ነው:፡ ዛሬም ይደገማል <<ደውን ዳውን ወያኔ!>>…በአስቸኳይ ውረዱ ላለ ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምላሽ አይደለም!

Filed in: Amharic