ደንቁሩ በአዋጅ [ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም] October 19, 2016 እግዚአብሔር ዓይንን ፈጠረና እዩበት አለ፤ እግዚአብሔር ጆሮን ፈጠረና ስሙበት አለ፤ እግዚአብሔር አእምሮን ፈጠረና አስቡበት አለ፤ እግዚአብሔር አንደበትን ፈጠረና ተናገሩበት አለ፤ ወያኔ አይሆንም አለ! በዓይንህ አትይ፤ በጆሮህ አትስማ፤ በአእምሮህ አታስብ፤ በአንደበትህ አትናገር፤ አበሻ ተዋረደ! ዓለም እየሰማ ድንቁርና ታወጀበት! ማን ያሸንፋል? እግዚአብሔር አለ፤ ወይስ ወያኔ አለ?