>

“ሃይል በሚሰጥ በፈጣሪ ሁሉን እችላለሁ” (ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ)

Elias Gebru 15102006“”እኔና ዳንኤል ሺበሺ ባለቤት አልባ የግፍ እስረኞች ሆነናል። ታስረንም በምንገኝበት ቦሌ ፖሊስ መምሪያ የእናንተ ጉዳይ ከአቅሜ በላይ ነው፤ እናንተን መክሰስም ይሁን መፍታት አልቻልኩም” በማለቱ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ እንደምንሄድ ዛሬ ጠዋት ተነገረን። በተባልነዉም መሰረት በጠዋት እቃችንን ሸክፈን (ይዘን) ወደ ማእከላዊ ምርመራ ሄድን- ከመርማሪዎቻችን ጋር።ማእከላዊ እኛን አልቀበልም አለ።ወዲያው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (3ኛ) ተላክን። ይህም ኮሚሽን “አልቀበልም፣ አልችልም” የሚል ምላሽ ሰጠ።

በመጨረሻ ልደታ ፍርድ ቤት የሚገኘው የአቅቤ ሕግ ቢሮ ጉዳያችንን እንዲያየው መዝገባችንን የያዙት መርማሪ ፖሊሶች ማስረጃ የሚሏቸውን ሰነዶች (ስልኮችን ጭምር) ሰጥተው ተመልሰን ወደ ቦሌ ፖሊስ መምሪያ መጣን።

አምስት ወራት በግፍ መታሰራችን ሳያንስ፣ ለተጠረጠርንበት ጉዳይ እስካሁን መፍትሄ የሚሰጠን አካል በመጥፋቱ በሃገራችን በጣም አዝነናል። ግን ለተሻለች ሀገር ግንባታ ዛሬም ሆነ ነገ ጠንክሬ እንደምታገል ልቤ በጽኑ ያምናል።

“ሃይል በሚሰጠ በፈጣሪ ሁሉን እችላለሁ”

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

Filed in: Amharic