>
5:14 pm - Thursday April 20, 5262

“ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች - አፍሪካ ማበር አለባት!”

ቅዱስ መሃሉ
“ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች – አፍሪካ ማበር አለባት!” 
ክዋሜ ንክሩማህ ግንቦት ወር 1963ዓ/ም አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ እና በንጉስ ኃይለሥላሴ ፊታውራሪነት በተቋቋመው የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ውስጥ ቆሞ የሚገኘው የክዋሜ ንክሩማህ ሃውልት ይህ ነው።

የአፍሪካ ሕብረት በግቢው ውስጥ ለሕብረቱ መመስረት ጉልህ ድርሻ ከተጫወቱ የአፍሪካ መሪዎች ውስጥ ዋናው ናቸው ያላቸውን ንጉስ ኃይለሥላሴን እና የጋና ፕሬዝዳንት የነበሩትን የክዋሜ ንክሩማህን ሃውልት ለማቆም በቀዳሚነት ሃሳብ ቢያቀርብም የኢትዮጵያ መንግስት የንጉስ ኃይለሥላሴ ሃውልት እንዳይቆም ባቀረበው ተቃውሞ  ምክንያት የክዋሜ ንክሩማህ ሃውልት ብቻውን ቆሞ ቆይቷል። በቅርቡ ግን የንጉስ ኃይለሥላሴ ሃውልት እና የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሃውልት አብሮ ይቆማል ተብሏል። ከክዋሜ ንክሩማ መዘከሪያ ሃውልት ስር  በእንግሊዝኛ የተጻፈው ጽሁፍ ይህ ነው። “Ethiopia Shall Stretch forth her hands unto God. Africa Must Unite.” Osag Yifo Kiwame Nkrumah, May 1963, Addis Ababa. 

የዚህ የአማርኛ ትርጉም ከላይ የጽሁፉ መጀመሪያ ያደረኩት እና የጋና የነጻነት ታጋይ እና ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ክዋሜ ንክሩማህ በግንቦት ወር 1963ዓ/ም በአዲስ አበባ አበባ ያደረጉት ንግግር ነበር። ንግግራቸውን እዚህም ደግሜው ጽሁፌን ልቋጭ። “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች።አፍሪካ ማበር አለባት!”

Filed in: Amharic