“እኛም ሰው ነን አላስፈላጊ እርምጃ እንድንወስድ አታስገድዱን” (ዶ/ር ዓቢይ አህመድ የመጨረሻ የሰላም ጥሪ) 

“እኛም ሰው ነን አላስፈላጊ እርምጃ እንድንወስድ አታስገድዱን”
ዶ/ር ዓቢይ አህመድ የመጨረሻ የሰላም ጥሪ 
ጆሮ ያለው ይስማ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለሚፈጥሩ የቀን ጅቦች ወደ ሰላም እንዲገቡ የመጨረሻ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም በሚያሳፍር ሁኔታ ሰዎች ይሞታሉ” በማለት ንግግር ያሰሙ ሲሆን ይህ እንዲያበቃም “እባካችሁ ወደ ሰላም ግቡ፤ ይህ የመጨረሻ የሰላም ጥሪዬ ነው” ብለዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ያለው የጥላቻ ግንብ መናዳን አንስተው በአንዳንድ ክልል ያለው “የሳር ቀጤማ ግንቦች ይፍረሱ” በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
–
የዛሬው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይዘው የመጡት ፍቅር በ50 ቢሊየን ብር የማይገዛ ውድ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም ዛሬ የተቀደደው ጥቁር መጋረጃ ነው የሚበጀን ፍቅርና ሰላም ብቻ ነው….፡፡
–
በተጨማሪም የሰላም ዋጋው ያልገባቸው አካላት በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እንደሚያስነሱ ጠቅሰው ዛሬ እንኳ ስለ ሰላም ተማሩ በማለት ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰዎች ሞት ማብቃት አለበት ያሉ ሲሆን የሰላም ጥሪያቸውን አጽንዖት በመስጠት አስተላልፈዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻም አልፎ አልፎ የምታውኩን ሰዎች ፍቅራችንን ባታበላሹት መልካም ነው ነገርግን ግጭቶች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ሰውነንና ወዳልተፈለገ ነገር እንዳታስገቡን አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.