>

ዛሬ የትችት ቀን ነው! ለምስጋና ገና ብዙ ቀናት ወደፊት አሉኝ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ዛሬ የትችት ቀን ነው! ለምስጋና ገና ብዙ ቀናት ወደፊት አሉኝ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
በኢሳያስ አቀባበል ስነስርአት ከቦሌ ጀምሮ እሰከ ሃዋሳ ድረስ የኦህዴድ ድርሻ በጣም የተጋነነ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። ጭራሽ አዋሳው ላይማ ከ9ኝ ክልል ፕሬዚደንቶች ለማ መገርሳ ብቻውን የተገኘበት ምስጢር ግልፅ አይደለም።
 ይሄ ነገር በቀጣይ በሚደረጉ አገራዊ ጉዳዮች በሚንፀባረቁበት መድረክ መደገም የለበትም ። እርግጥ አቢይም ሆነ ኦህዴድ ህውሃትን ገደል ውስጥ የጨመራትን ስትራቴጅ  መለሰው ተግባራዊ አድርገው ራሳቸውን ችግር ውስጥ ያስገባሉ ብዬ አልሰጋም። ነገር ግን መጠቆም ከአንድ ምከንያታዊ ሰው የሚጠበቅ ነው።
እዚህ ቁጭ ብዬ የምቸከችከው አንዱን አለቃ ሸኝቼ ሌላ አለቃ ለመቀበል ሳይሆን ለእኩልነት ነው። ብአዴኖችም  ጧትም ማታም ከቤተመንግስት መጥፋት የለባችሁም ከወንድም ከእህቶቻችሁ ከኦህደዶች ጋር ተመካከሩ ።
ሌላው ትችቴ  የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ የ 100 ሚሊዮን ጠ/ሚ እስከሆነ ድረስ ፕሮቶኮሉን መጠበቅ አለበት።
ውስጡ ቅን እንደሆነ ግልፅ ነው። ቅንነትና ጠ/ሚ ሆኖ አክት ማድረግ ይለያያሉ ።
አቢይ Humble መሆኑን ለማሳየት ከኩኪስ ማዞር እስከ አስተርጓሚ የሚደርስ ሰርቪስ መስጠት አይጠበቅበትም። ወይም ከመኪና ዘሎ በመውረድ ወደ ህዝብ ለመቀላቀል መሞከር የለበትም። ይሄ ሁሉ ተጓዳኝ አገራዊ ጉዳት ስላለው መጠንቀቅ አለበት።
እንኳን የአገር መሪ ሙሽራ እንኳን ጀነን ይላል።  በነገራችን ላይ ለስለስ ያለ መሪ ያላት አገር በውጭ ወራሪ የመደፈርና ትንኮሳን የማስተናገድ እድሏ ሰፊ ነው።   ይሄም ሊታሰብበት ይገባል። ሱዳንም ይሄን ተመልክታ ሊሆን ይችላል መለስ ቀለስ እያለች ጉዳት እያደረሰች ያለችው።
Filed in: Amharic