በአፋር ሰመራ በተደረገ ሰልፍ ላይ ልዩ ሀይሉ በርካታ ሰዎችን ቁስለኛና እስረኛ አድርጓል!!!
ጌታሁን ልጅአለም
* ዶክተር ጃቢር እና 3 ሰዎች ታፍነው የት እንደተወሰዱ አይታወቅም!
በአፋር ክልል እኛም የለውጡ ተጠቃሚ መሆን እንፈልጋለን ብለው አደባባይ ላይ በወጡ ወጣቶች ልዮ ሀይሉ ድብደባና ወከባ እየፈፀመ ነው::
የአፋር ክልል በሶማሌ ክልልና በሌሎችም የአመራሮች ለውጥ እንደተደረገው እኛም ይህ እድል ይድረሰን የተጫኑብን አመራሮች ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አይደሉም እያሉ ነው::
የፌድራል መንግስት እጁን አስገብቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው::
በዛሬው እለት በሰመራ አፋር እየተደረገ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ልዩ ሃይል በትኖታል:: በርካታ ወጣቶች ቁስለኛ ሆነዋል ቁጥራቸው 5 የሚደርሱ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት የደረሰባቸው. ሰልፈኞች ሆስፒታል ገብተዋል ::
ዶክተር ጃቢር እና 3 ሰዎች ታፍነው የት እንደተወሰዱ አይታወቅም! ከ50 በላይ ወጣቶች ታስረዋል:: የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ ስአት ልዩ ሃይል ቤት ለቤት አሰሳ ጀምሯል::
