>

በአፋር ሰመራ በተደረገ ሰልፍ ላይ ልዩ ሀይሉ በርካታ ሰዎችን ቁስለኛና እስረኛ አድርጓል!!! (ጌታሁን ልጅአለም)

በአፋር ሰመራ በተደረገ ሰልፍ ላይ ልዩ ሀይሉ በርካታ ሰዎችን ቁስለኛና እስረኛ አድርጓል!!!
ጌታሁን ልጅአለም
 
* ዶክተር ጃቢር እና 3 ሰዎች ታፍነው የት እንደተወሰዱ አይታወቅም!
በአፋር ክልል እኛም የለውጡ ተጠቃሚ መሆን እንፈልጋለን ብለው አደባባይ ላይ በወጡ ወጣቶች ልዮ ሀይሉ ድብደባና ወከባ  እየፈፀመ ነው::
የአፋር ክልል  በሶማሌ ክልልና በሌሎችም  የአመራሮች ለውጥ እንደተደረገው  እኛም ይህ እድል ይድረሰን የተጫኑብን አመራሮች  ህዝቡን  ተጠቃሚ  የሚያደርጉ አይደሉም  እያሉ  ነው::
የፌድራል መንግስት እጁን አስገብቶ  መፍትሄ  እንዲሰጣቸው እየጠየቁ  ነው::
በዛሬው እለት በሰመራ አፋር እየተደረገ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ልዩ ሃይል በትኖታል:: በርካታ ወጣቶች ቁስለኛ ሆነዋል ቁጥራቸው 5 የሚደርሱ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት የደረሰባቸው. ሰልፈኞች ሆስፒታል ገብተዋል ::
ዶክተር ጃቢር እና 3 ሰዎች ታፍነው የት እንደተወሰዱ አይታወቅም! ከ50 በላይ ወጣቶች ታስረዋል:: የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ ስአት ልዩ ሃይል ቤት ለቤት አሰሳ ጀምሯል::
Filed in: Amharic