>
6:45 am - Tuesday July 5, 2022

ትግራይ መርገም የበቀለባት የበረከት ምድር!!! (ሀይለ ገብርኤል አያሌው)

ትግራይ መርገም የበቀለባት የበረከት ምድር!!!
ሀይለ ገብርኤል አያሌው
ትግራይ የቅዱስ ያሬድ ትውልድ ስፍራ ሰማይ ከመሬት የሚገናኙበት : የጽድቅ መሰላል የተዘረጋበት የታቦተ ጽዮን ማህደር ቅዱሳን የፈለቁባት : የኢትዮጵያዊነት ምንጭ የተቀዳባት የበረከት ምድር ነበረች ::
ዛሬ ያ በጎ ታሪኳ ተለውጦ የደግነትና መክሊቷ ሰምጦ በረከቷ በመርገም ተበክሏል:: ሰው ሆነው ሰው የሚበሉ የጨካኝ ጭራቆች መፍለቂያ ሆናለች:: ሃገር የሚሰርቁ ሌቦች መሸሸጊያ :
የንጹሃን ሕይወት የሚያጠፉ አረመኔዎች ማድፈጫ የእርኩሰት ባህል አራማጅ የስዶማውያን ደቦቃ ሆናለች :: ቅድስናዋ ረግፎ ጸጋዋ ተንዶ የንጹሃን ልጆቿን ማዳን ትቃትታለች::
ያሬድን የመሰለ የጽድቅ ትሩፋቱ ሰማይ የደረሰ ከመላዕክት የሚነጋገር ጻድቅ እንዳላፈራች: በሰብዐዊ ፍጡር ላይ ወደር የለሽ ጭቃኔ ፈጻሚው የሰው አውሬ ጌታቸው አሰፋን ዛሬም ከፍ አድርጋለች:: በጥፍር ነቀላ በብልት ቅጥቀጣ በአሰቃቂ ግድያ የላቀውን መድባለች:: አስገድዶ በመድፈር የተካነው ብዙዎችን ያላሳዳጊ እንዲቀሩ የአልጋ ቁራኛ እንዲሆኑ ያደረጉትን መርጣለች:: የወላድ መካን ሆናለች::
ትግራይ መልካምነት መገለጫዋ እንዳልነበር : የጥላቻ ስብከት ምንጭ የክፋት መፍለቂያ ሆናለች::  ገዳይ አራጆች ምስኪኑን ሕዝብ ሰብዐዊ ጋሻ አድርገው ሃገር የማፍረስ እቅዳቸውን ለማስቀጠል የሚያደቡባት ምሽግ አድርገዋታል:: ዛሬ ሃገራችን ለገባችበት ሃገራዊ ቀውስ ያበቋት አረመኔዎች ማምለጫ ዋሻ ሆናለች ::ትግራይ የጥላቻ ፖለቲካ እንክርዳድ የዘሩትን የመለያየት ግንብን ያነጹት የቀን ጅቦች ከያሉበት ሲባረሩ እጉያዋ ገብተው ተደብቀዋል::
ከእንግዲህ ግን ሕዝቡ መሮታል የመከራው መርግ ከብዶታል :: ጥፍሩን የሚያስነቅል የዋህ የለም :: ለልጆቿ የምታለቅስ እናት እምባ ነጥፏል:: የዋይታው የሰቆቃው ጽዋ ሞልቶ በቀልን ወልዷል:: ይህ ምሬት እዚህ ከመድረሱ በፊት በሰላም በፍቅርና በእርቅ እንዲፈታ ብዙዎች ብዙ ጥረዋል::   በእኔ አቅም እንኳ ከሕወሃት መስራች ዶር አረጋዊና ሌሎች ባልደረቦቹ ጋር በቤተሰባዊ መንፈስ ስለ ሕዝባችን አብሮነትና ስለዘለቄታው አንድነቱ በጋራ ቆመን አልሆነም እንጂ ብዙ ጥረት አድርገናል::
                     አሁን ግን ብሶት የወለደው : በደል    ያስመረረው : መገፋት ያሳመመው ትውልድ ራሱን ሊመክት ጠላቱን ሊገዳደር ተነስቷል:: ይህ ብሶት የወለደው የአዲስ ትውልድ ሃይል ከትግራይ ሕዝብ ጋር ችግር የለበትም:: የትግራይ ሕዝብ ዛሬም እንደ ትላንቱ ወገኑ ነው:: ሕወሃት ግን የሕልውና ጠላቱ ነው:: ሕወሃት የትግራይን ሕዝብ ከወንጀሉና ከዘረፋው መሸሸጊያ ጫካ አድርጎታል:: የትግራይ ሕዝብ ለራሱ ዘለቄታዊ ሰላም ሲል ሃገር ዘርፈው ሕዝብን ገለው ሊሸሸጉበት የፈለጉትን የወያኔ መሪዎች ሊታገል ለፍርድ እንዲቀርቡም የማድረግ ሃላፊነት ይኖርበታል:: ይህ ደግሞ ከሞራልም ከሃይማኖትና ከፍትሕ አኳያ ግድ ይለዋል:: አለያ ደጋግ አባቶችን ያፈለቀችው የሃይማኖት አምድ የነበረችው ደጏ ትግራይ እንደ ሰዶምና ጎመራ እጣዋ እንዳይሆን ሽማግሌዎቿ  ሊያስቡበት ይገባል:: በግፍ የተወሰደ መሬት በስርቆት የተጋዘ ሃብት መመለስ ይኖርበታል:: ሕዝብን የበደሉ በወንጀል የተጨማለቁ ሃገር የዘረፉ ለሕግ እንዲቀርቡ የትግራዩ ማሕበረሰብ ሊተባበር ይገባል:: ትግራይ መርገሟ ሕወሃት ተወግዶ ኢትዮጵያዊነት በረከቷ እንዲመለስ ሳይመሽ ማሰብ የሚችል ልብ ያለው አሳቢ ይስጣት::
እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!
Filed in: Amharic