የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል

Danel Shibeshiየአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ጠዋት ሜክሲኮ አካባቢ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ከተያዘ በኋላ በአሁኑ ሰዓት አየር ጤና አካባቢ የሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየተበረበረ እንደሆነ፤የፍኖተ ነጻነት ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ በትዊተር ገጹ ገልጾኣል።

በዛሬው ዕለት ብቻ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ኣቶ ሃብታሙ ኣያሌው፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ  መታሰራቸው ታውቆኣል።

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.