>
5:14 pm - Monday April 30, 0863

የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ 6 ተማሪዎችና አንዲት ወጣት በቄሮ ታፍነው ተወሰዱ!!! (ኢትዮ 360)

የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ 6 ተማሪዎችና አንዲት ወጣት በቄሮ ታፍነው ተወሰዱ!!!

ኢትዮ 360
ተማሪዎቹ የታፈኑት ከዩኒቨርስቲው በ2 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በሚገኘውና ሚኮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል። እንደ ምንጮቹ ከሆነ ተማሪዎቹ የታፈኑት ከዩኒቨርስቲው አምልጠው ወተው ራሳቸውን ለማዳን እየሞከሩ ባሉበት ሰአት መሆኑም ታውቋል።
ከ20 እስከ 25 ያህል ቁጥር ያለው የአፋኞቹ ቡድን ከአባቷ ጋር በመጓዝ ላይ ያለች አንድ ወጣትንም አፍነው መውሰዳቸው ታውቋል።የልጅቷ አባት ከአፋኞቹ አምልጦ መደበቁንም ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የሚገልጹት።
ከዩኒቨርስቲው አምልጠው የወጡት ተማሪዎች ቁጥር ብዙ ቢሆንም መታወቂያችሁን አሳዩ በሚለው የቡድኑ ትዕዛዝ ተለይተው እንዲታፈኑ የተደረገው ግን ከአማራ ክልል የመጡት ተማሪዎች መሆኑ ታውቋል።
ምንጮቹ እንደሚሉት ከግቢው የሚያመልጡ ተማሪዎች መኖራቸውን ከውስጥ ሆኖ ለአፋኙ ቡድን መረጃ የሚያቀብል ሃይል አለ። በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሃይል ስለታፈኑት ተማሪውችም ሆነ ስለ ታፈነችው ወጣት መረጃው ከደረሰው ጀምሮ ፍለጋውን ቢቀጥልም ይሄ መረጃ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ ምንም ፍንጭ ማግኘት አለመቻሉን ነው መረጃው የገለጸው።
እንደ ምንጮቹ ከሆነ በዩኒቨርስቲው ካለው ችግር ጋር በተያያዘ ከግቢ ወተውና በአካባቢው ራሳቸውን ደብቀው የሚገኙ ተማሪዎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው።ከዩኒቨርስቲው ሰላሳና አርባ ኪሎሜትር አቋርጠው የሸሹ ተማሪዎችን የአካባቢው ነዋሪ ገንዘብ እያዋጣ ወደ መጡበት እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑንም መረጃው ጠቅሷል።በዩኒቨርስቲው ያለው ችግር ከባድ እንደሆነ ቢገለጽም ተማሪዎች ግን ከግቢው እንዳይወጡ የዩኒቨርስቲው በሮች መዘጋታቸውንና ጥበቃ መመደቡ ታውቋል።
ከዩኒቨርስቲው ለማምለጥ ሲሞክር የተያዘ ተማሪ የሚጠብቀው ከባድ ድብደባ መሆኑንም የመረጃ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። የኢትዮ 360 ምንጮች ለታፈኑትም ሆነ በአካባቢው ተበትነው ለሚገኙት እንዲሁም በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ በር ተዘግቶባቸው እንዲቀመጡ ለተደረጉት ተማሪዎች የሚመለከተው አካል ካልደረሰላቸው ሁኔታዎች ከዚህ በላይ የከፉ ሊሆኑ ሲሉ ተናግረዋል።
Filed in: Amharic