>

በዛሬ ጨቅላ እሳቤ የትናንቱን ገናናውን  ምኒልክን ማጠልሸት የድንቁርና ጥግ ነው!!!  (ዘመኑ ደረሰ)

በዛሬ ጨቅላ እሳቤ የትናንቱን ገናናውን  ምኒልክን ማጠልሸት የድንቁርና ጥግ ነው!!! 

ዘመኑ ደረሰ
አፄ ምኒልክ: – በበታችነት ስሜት የሰከሩት እንደ እነ  አሰፋ ወዳጆ፣ጃዋር መሀመድ ፣እዝቅኤል ጋቢሳ፣ በቀለ ገርባ ፣ ዶር ገመቹ፣ ፀጋዬ አራርሳ እንደሚሉት አሀዳዊነትን የሚያቀነቅኑ ሳይሆኑ፣ህዝብ ጨፍጫፊም ሳይሆኑ ፣ አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሀይማኖት ያላሉ ልዩነትን ጌጥና ሀይል አድርገው ታላቋን ኢትዮጵያ ከቅኝ ግዛት ነፃ የሆነች ሀገር የመሰረቱ ታላቅ ንጉስ ናቸው
የዓፄ ምኒልክ አኩሪ. ድል  ለአፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን በየትኛውም አለም ሚኖር ጥቁር ህዝብ ደረቱን ነፍቶና አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ ያደረገ ታሪካዊ ድል ነው። ጥቁሮች  በየትኛውም ዓለም አቀፍ መደረኮች  ላይ በጥቁርነታቸው ሳያፍሩ፣ ሳይሸማቀቁ፣ሳፈፍሩ በራሳቸው በመተማመን በልበ ሙሉነት ሀሳባቸውን አንዲገልፁ ያደረገ ታላቅ ድል ሆኖ ተመዝግቧል ። ይህ ድል ከምንም በላይ ለእኛ ለድሉ ባለቤቶች ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ድሉን ድርብ ድል ያደርገዋል። የዓፄ ምኒልክ ድል በቅኝ ግዛት ያለተገዛች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ባለቤት ኢ/ያን አጎናፅፎናል። ምስጋና ለምኒልክ። የንጉስ ምኒልክ ታሪካዊ ድል ጥቁሮች ከቀልባቸው እንዲሆኑ ከማድረጉም ባሻገር ቅኝ ገዥዎችም ጥቁር. ነጭን አ ንበርክኮ አሽንፎ በገሃድ ያሳየበት መሆኑን ስለተረዱ ቆም ብለው እንዲያስቡና ከቀልባቸው እንዲታረቁ ያደረገ ድል ነው። ምኒልክ ታላቅ እና ህያው ንጉስ ነው። የምኒልክ ድል  ለነጮችም ይሁን ለመላው ጥቁር ህዝብ ህያው ነው።  ምኒልክ በአመክንዮ የሚያሚን ፣ የቋንቋ ፣የሀይማኖት፣የባህል ልዩነትን ጌጥ መሆኑን የሚያምንና የሌሎችን ቋንቋና ባህል በሌሎች እንዳይዋጥና እንዳይጠፋ ጠብቆ ያቆዬ ባለውለታ ነው።  ታዲያ አቅመ ቢሶችቋንቋቸውን እና ባህላቸውን እንደማእድን ከመሬት ቆፍረው ያውጡት ይመስል ቋንቋችን ተቀብሮ፣ባህላችን ጠፍቶ፣አህዳዊ ተደርገን፣ ተውጠን፣ ወዘተ እያሉ የሚዘባርቁት ዓፄ ምኒልክ ጠብቀው ባቆዩላቸው ቋንቋ አሳቸውን ሰወርፉ መስማት አቅመ ቢስነት ብቻም ሳይሆን ባጎረሱ እጃቸውን እየተነከሱ መሆኑ አይደለምን?  በርግጥ  ይህ አስተሳሰብ ሊፈልቅ የሚችለው ደግሞ የመነሻ ነጥብ ከሌላቸው የመድረሻ ዓላማና ግባቸውን ከማያውቁ በበታችነት ስሜት / inferiority complex/  ካበደ፣ ራሱንም ሆነ ራሱ የተኘበትን ማህበራዊ ስሪት /social fabric/ ከሌሎች የእኔና የእኛ ያነሰና የበታች ነው ብሎ ከሚያምን የበታችነትሰ ስሜት /inferiority complex/ አዘቅት ውስጥ መውጣት ካልቸለ የአስተሳሰብ ነቅዘት የሚመነጭ የዝቅተኝነት በሽታ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮማ. ዓፄ ምኒልክን ባልተፈፀመ ፣ባለተፃፈ. በሬ ወለደ አሉቧልታ ለመኮነን ሞራላዊ ድፍረቱም ባልኖራቸው ነበር። ጥበት ሊመነጭ የሚችልባቸው ምክንያቶች በርካታ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹ : – 1ኛ  ከአስተሳሰብ ውሱኑነት የተነሳ ከሌሎች ጋር. አዳዲስ ነገሮችን መፍጠርና በሌሎች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወዳዳሪ ሆኖ ማሸነፍ ሲያቅት፣ 2ኛው ደግሞ የአስሳሰብ አድማስን አስፍቶ ሀሳብ አመንጭቶ እራስንና የተገኘበትን ማህበረሰብ ከገባበት የበታችነት ስሜትና ማህበራዊ ቀውስ /social crisis/ ውስጥ  ከማውጣት ይልቅ  መንጋነትን እንደግብዓት በመቁጠር  የሌሎችን ከመሻት የሚመነጭ የአስተሳሰብ አቀንጭራነት ነው።3ኛው የዘረኝነት ምንጭ ደግሞ. አወንታዊ የሆነና ህልውናን ለመጠበቅ ሲባል ተገዶ የሚገባበትና የሚደረግና አወንታዊነት ያለው ሲሆን  አንድ ማህበረሰብ በዘረኞ
ች፣ በጠባቦች እና በአቅመ ቢሶች ህልውን አደጋ ውስጥ የሚከትና የሚፈታተን አደጋ ሲያጋጥመው እስራኤሎች ከናዚ መዳፍ ለመውጣት እንዳደረጉት ፣ ቱሲዎቹ በሁቱዎቹ ከተረገባቸው የዘረኝት ዘጅምላ ጭፍጨፋ ለመዳን የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል ሁሉ ራስን መከላከል ተፈጥሯዊ በመሆኑ የዚህን አይነት  አስተሳሰብ ሊይዝ ይችላል። ለማንኛውም ዓፄ ምኒልክ ዛሬ በባትሪ ቢፈለግ የማይገኝ የዚያ ዘመን ተአምረኛ መሪ ነው።ዓፄ ምኒልክ ኢ/ያን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀ ባለ ራዕይ ድንቅ  ንጉስ ነው። ምስጋና ለዓፄ ምኒልክ። ዛሬ ላይ ሆኖ ምኒልክን መውቀስ አቅመቢስነት ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ምኒልክን ማውገዝ የጭንቅላት ምክነት ነው ። ዛሬ ላይ ሆኖ ብዙዎችን ከእንስሳነት ወደ ሰዋዊ ፍጡርነት የለወጠውን ዓፄ ምኒልክን ለማጠልሸት መፈለግ የድንቁርና ጥግ ነው። ከጫካ ውስጥ አውጥቶ ህንፃ ላይ እንዲኖር ያደረገ ስልጡን ንጉስ ሊወደስ እንጅ ሊወቀስ ከቶ አይገባውም።  ዓፄ ምኒልክ ስራው ህያው ገድል ነው። ዓፄ ምኒልክን አቅመ ቢሶች ፣ ሰንካሎች፣መንደርተኞች ዛሬም መንፈሳቸው ያርበደብዳቸዋል። ዓፄ ምኒልክ  ዛሬም እየገዙ ነው። ንጉሱ ዛሬም በህይወት አሉ።  ለማንኛውም ወደድንም ጠላንም ንጉስ ምኒልክ በሰራት ኢትዮጵያ መኖር የግድ ነው። ይህ የማይስማማው ብርቅዬ እንግዳ ወይም ሌላ  አካል ካለ ዓፄ ምኒልክ ያሰመሩትን የ ኢትዮጵያን  ድንበር ለቆ ለራሱ ወደሚመቸው ስፍራ መሄድ ይችላል። መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት።
Filed in: Amharic